በቴሌግራም ቴራባይት የብልግና ምስሎችን ያግኙ »

Commercial Bank of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ commercialbankofethiopian — Commercial Bank of Ethiopia C
የሰርጥ አድራሻ: @commercialbankofethiopian
ምድቦች: ቁማር
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.11K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1700 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-07 13:29:08 በሲቢኢ ብር መተግበሪያ እንዴት በቀላሉ ነዳጅ መቅዳት ይችላሉ?
========================
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ወደ Play Store ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን ያዘምኑ (Update)!

1.  የሲቢኢ ብር መተግበሪያውን ይክፈቱ፣
2.  ‘Quick Pay’ ‘ክፍያ ለመፈፀም’ የሚለውን አማራጭ ይጫኑ፣
3.  ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ ይምረጡ፣
4.  የነዳጅ ቀጂውን የተመዘገበ ስልክ ቁጥር ያስገቡ፣
5.  የሚገዙትን የነዳጅ ክፍያ መጠን ያስገቡ፣
6.  የነዳጅ አይነት ይምረጡ፣
7.  የታርጋ ቁጥርዎን ያስገቡ፣
8.  የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ፣
9.  ‘PROCESS PAYMENT’ ‘ክፍያውን አከናውን’ የሚለውን ይጫኑ፣
10.  ነዳጅ ቀጅው ክፍያውን አረጋግጦ ሲቀበል፣ ክፍያውን ማከናወንዎን የሚገልፅ መልእክት ይደርስዎታል፡፡ 

የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
4.1K views10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 13:28:54 በቅርቡ በአዲስ አበባ የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቶች ይተገበራል!
****

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እና በሲቢኢ ብር
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያዎን በቀላሉ መክፈል ይችላሉ!
3.4K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 13:28:42 የ”ነዳጅ” መተግበሪያን በመጠቀም ነዳጅ መቅዳት ይቻላል።
===================================================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአማራጭነት ያቀረበው Nedaj የተሰኘው መተግበሪያ ተሻሽሎ ቀርቧል። ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግዎ ከሞባይል ባንክ ሒሳብዎ ጋር በቀጥታ በማስተሳሰር  አልያም የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ካልሆኑ በቀጥታ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ያለምንም ተጨማሪ ወጪ እና አገልግሎት ክፍያ አሁኑኑ ይመዝገቡ።
በተጨማሪም በሲቢ ብርም  ሆነ በ”ነዳጅ” መተግበሪያዎች ተጠቅመው ነዳጅ ሲቀዱ ምንም አይነት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም።

አሁኑኑ ከ play store እና app store በማውረድ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!
“ነዳጅ” መተግበሪያን ለማውረድ
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

ለአይፎን ስልኮች፦ https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#CBE #CBEbirr #Nedaj #nedajapp
2.9K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 13:28:31 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየኢፌድሪ  የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መ/ቤት ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ግብይትን በዲጅታል ክፋያ ለማካሄድ የሚያስችል የትግበራ መርሃ ግብር አካሄደ።
በመርሃ ግብሩም በሲቢኢ ብር እና በ”ነዳጅ” መተግበሪያዎች በቀላሉ የነዳጅ ክፍያ መፈጸም እንደሚቻል ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚሁ ሥነ-ስርዓት ላይ የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት በዲጂታል የነዳጅ ገንዘብ  መክፈያ ዘዴዎቹ በሁለት አማራጮች የተዘጋጁ ሲሆን የመጀመሪያው የባንኩ የነዳጅ ክፍያ መፈፀሚያ መተግበሪያ (Fuel  App)  በሲቢኢብር  መተግበሪያ  የሚሠራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ  "ነጃጅ"  በተሰኘው  መተግበሪያ  ከአበልፃጊው ድርጅት ጋር በመተባበር የሚተገበር እንደሆነ ተቁመዋል ፡፡  እነዚህም መተግበሪያዎች  ደህንነታቸውን በተመለከተ በተለያየ ደረጃ የተሞከሩና በሙከራ ወቅትም በአግባቡ የሚሠራ አስተማማኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢፌድሪ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ  ባሪኦ  ሐሰን በበኩላቸው ሃገሪቱ በምታከናውናቸው  ስራዎች  የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነዳጅ ግብይቱን በዲጅታል መንገድ ለማድረግ የልማትለሚሰራቸው ስራዎች ሚኒስቴር መ/ቤቱ እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
የናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ጥላሁን እንደገለፁት የኢትዮጵያ  ንግድ  ባንክ የጀመረው የነዳጅን በዲጂታል ክፍያ  ዘዴ ማገበያት በዘርፉ ዘመናዊና የተሳለጠ ሥራ እንዲከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡
የኢንባ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች  ቁጥር ከ 18 ሚልዮን በላይ የደረሰ ሲሆን ባለፉት 9 ወራት 549 ሚልዮን ክፍያዎችን  በዲጂታል ባንክ ማስተናገድ እንደተቻለ በመርሃ ግብሩ ተገልጿል
2.5K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 13:28:20 በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ብቻ ሊደረግ ነው::
 
ይህንንም ተከትሎ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያቀረበውን “ነዳጅ” የተባለ መተግበርያ በመጠቀም ከ 1074 በላይ የሚሆኑ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ግብይት መፈፀም የሚያስችል አሰራራር አስተዋውቋል።
 
የ”ነዳጅ” መተግበሪያን በመጠቀም እንዴት መገበያየት ይቻላል
 
በመጀመሪያ የነዳጅ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ያውርዱ
ሙሉ መረጃዎን በማስገባት መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ ወዲያውኑ የነዳጅ መለያ ቁጥር በ አጭር የጽሁፍ   መልዕክት ይደርስዎታል።
በመቀጠል መተግበርያው ላይ የተሽከርካሪዎን የሰሌዳ ቁጥር በማስገባት ተሽከርካሪዎን ይመዝግቡ።
  የነዳጅ መለያ ቁጥርዎን በመጠቀም በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።
 
ከዚህ በኋላ ቀጥታ ከሂሳብ አካውንትዎ ግብይት መፈጸም ብቻ!!!!
 
ነዳጅ ለመቅዳት ማደያ በሚሄዱበት ወቅት የነዳጅ ቀጂ ባለሙያው የሰሌዳ ቁጥርዎን ፣  የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን በ(ነዳጅ ቀጂው)መተግበሪያ ላይ በማስገባት ግብይቱን ያስጀምራል
 
ወዲያውኑ በሚደርስዎት የአጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ የሚስጥር ቁጥሩን(OTP) ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው በመንገር ግብይቱን ያጠናቅቁ።
 
ነዳጅን ለየት የሚያደርገው
 
አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት መሆኑ!
በአቅራቢያዎ ያሉ ነዳጅ ማደያዎችን እንዲሁም ነዳጅ መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋግጠው መሄድ የሚያስችሎትን አማራጭ ይዞ መምጣቱ!
አንዴ በመተግበሪያው ላይ ከተመዘገቡ በኋላ የስማርት ስልክ አለማስፈለጉ!
 
መተግበሪያውን ለማውረድ ?
 
ፕላይ ስቶር: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
 
አፕስቶር : https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
 
2.6K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 13:28:03 በሲቢኢብር መተግበሪያ ነዳጅ መቅዳት ይችላሉ።
================================================
  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመዘገቡ 1074 የነዳጅ ማደያዎች ጋር በመቅረብ
  የሚፈልጉትን የነዳጅ ዓይነትና መጠን በመቅዳት
  ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር፤ የመኪናዎን ታርጋ ቁጥር፤ የቀዱትን የነዳጅ ገንዘብ መጠን ለነዳጅ ማደያው አስተናጋጅ ማሳወቅ፤
  በስልክዎ አጭር የጽሁፍ መልዕክት /USSD/  መልዕክት ሲደርስዎ የሚከፋለውን የገንዘብ መጠን እና የነዳጅ ቀጂውን ኩባንያ ሥም ማረጋገጥ፤
  የመልዕክቱን ትክክለኝነት ካረጋገጡ በኋላ የሚስጥር ቁጥሮዎን ማስገባት፤
  የቀዱትን የነዳጅ ገንዘብ መጠን መክፈልዎን ወዲያው ማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል።
ጨረሱ!
ያለተጨማሪ መተግበሪያ፤ በማንኛውም የስልክ ዓይነት  ቀላል፤ ፈጣን እና አስተማማኝ በሆነው ሲቢኢ ብር ነዳጅዎን ይቅዱ! የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ለመጫን የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
3.5K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 11:44:00 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ በዓላትን አስመልክቶ እያደረገው ያለውን የማዕድ ማጋራት ተግባር ሌሎች ሊከተሉት የሚገባ በጎ ስራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
==============
ይህ የተገለፀው ባንኩ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ለሚሹ 25 የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና የባንኩ የቀድሞ ሰራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

በማዕድ ማጋራት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ማርቆስ ማቲዎስ እደተናገሩ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የሚየው የኑሮ ውድነት በርካታ ወገኖች ለችግር እንዲጋለጡ ማድረጉን ገልፀው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህን ወቅታዊ ችግር በመረዳት ለተቸገሩ ወገኖች ለመርዳት በተለያዩ አከባቢዎች እያደረገ ያለው ተግባር ሊደነቅ የሚገባ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ባንኩ በተለይ በዓላትን አስታኮ እያደረገ ያለውን በጎ ምግባር ሌሎች ተቋማትና ባለሀብቶች ሊከተሉት ይገባል ብለዋል፡፡

ባንኩን በመወከል ለተረጂዎች የበዓል መዋያ ድጋፍ ያበረከቱት የወላይታ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ መቆያ ጌታቸው በበኩላቸው በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ በማስታወስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ ረገድ አርአያ የሆነ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አውስተዋል፡፡ ባንኩ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚያደርገውን አርዳታ ከሌሎች የማሕበራዊ ኃላፊነት ስራዎቹ ጎን ለጎን አጠናክሮ እንደሚቀጥልበትም አቶ መቆያ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪና ለረጅም ዓመታት አገልግለው በጡረታ ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱ የቀድሞ የባንኩ ሰራተኞችም በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውንና የማዕድ ማጋራቱ የትንሳኤ በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ ለማሳለፍ እንደሚያግዛቸው ገልፀዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የተመረጡና ከሰባት ቀበሌ አስተዳደር የተውጣጡ 20 እጅ ያጠራቸው ወገኖች እና ባንኩን ለረጅም ዓመታት አገልግለው በጡረታ ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱ 5 የቀድሞ የባንኩ ሰራተኞች ሲሆኑ ስጦታው 4 ሺህ ብር ፣ ዘይትና ዱቄትን ያካተተ ነው፡፡

ባንኩ ከአሁን በፊት በተለያዩ አከባቢዎችም በበዓላት ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ የማአድ ማጋራት መርሀ-ግብሮች ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
3.1K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 13:36:51 ፈጣን መረጃ ለማግኘት
ወደ 951 የደንበኞች ግንኙነት ማእከል በነፃ ይደውሉ!
======================
• የኤቲኤም ካርድዎ ሲጠፋብዎ፣
• የሞባይል ባንኪንግ እና የሲቢኢ ብር አገልግሎቶች የሚስጥር ቁጥርዎን ሲረሱ፣
• ስለእለቱ የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ለማወቅ፣
• ስለሲቢኢ ብር፣ ሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶች አጠቃቀም ለማወቅ፣
• የአየር ቲኬት ግዥን ጨምሮ የውሃ፣ የስልክ፣ የመብራት እና ስለሌሎችም የአገልግሎት
ክፍያዎች አፈፃፀም ለመረዳት፣
• በአጠቃላይ ስለነባር እና አዳዲስ የባንኩ አገልገሎቶች መረጃ ሲፈልጉ

ለ24 ሰዓት ወደ 951 ነፃ የጥሪ መስመር በመደወል ፈጣን መረጃ  ያግኙ፡፡
768 views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 13:15:40 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጉምሩክ ኮሚሽን የታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የልዩ መብት ፈቃድ አገኘ።
================
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በዓለም አቀፍ ገበያ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ተሳትፎ ላላቸው እንዲሁም የጉምሩክ እና የታክስ ሕግና አሠራርን አክብረው ለሚሠሩ 195 ድርጅቶች መጋቢት 26/2015 ዓ/ም የታማኝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የልዩ መብት ፈቃድ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ይህንን የልዩ መብት ፈቃድ ካገኙ 195 የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች አንዱ ሆኗል።

ድርጅቶቹ ባላቸው የህግ ተገዥነት ታሪክ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ያላቸው አስተዋፅኦ፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማታቸው፣ በፋይናንስ አቅምና ደህንነት እንዲሁም በሌሎች መስፈርቶች ተመዝነው ሊመረጡ መቻላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾቹ በመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
982 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 20:55:13 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያን በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
=======================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነዳጅ ግዥ ክፍያን በሲቢኢ ብር አገልግሎት እና ‘ነዳጅ’ ‘Nedaj’ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ መፈፀም የሚያስችል ዲጂታል የክፍያ አሠራር በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ነው እየሠራ የሚገኘው፡፡

የነዳጅ ግዥን በዲጂታል የክፍያ አማራጭ መፈፀም የሚያስችለውን አሠራር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጅታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳህላክ ይገዙና የናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰር አቶ ታደሰ ይገዙ አዲስ አበባ ቄራ በሚገኘው የኖክ ነዳጅ ማደያ ጣቢያ  መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር አገልግሎት እና ‘ነዳጅ’ ‘Nedaj’ በተሰኘ መተግበሪያ ተግባራዊ  ያደረጋቸው  ዘመናዊ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አማራጮች የጥሬ ገንዘብ ክፍያን በዲጂታል አሠራር በመተካት የአሽከርካሪወችንና የባለማደያዎችን የጊዜ እና ጉልበት ብክነት እንደሚቀንስ አቶ ዳህላክ በወቅቱ አብራርተዋል ።

አዲሱን ዲጂታል የክፍያ አማራጭ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ 901 ማደያዎች ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ እስካሁን ባለው ሁኔታም በመላ ሃገሪቱ ካሉት ማደያዎች 60 በመቶ ማዳረስ መቻሉን ገልፀዋል ።

የናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ይገዙ በበኩላቸው አዲሱ ዲጅታል የነዳጅ ክፍያ አሰራር የነዳጅ ግብይት ስርአቱን የሚያሳልጥ፣ መተማመንን የሚፈጥር እና የመጭበርበር ስጋትን የሚቀንስ ነው ብለዋል።

ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ወደ ስራ መግባታቸውም ሃገራችን የጀመረችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አንደሚያጠናክረውም ነው አቶ ታደሰ የገለፁት።
2.1K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ