በቴሌግራም ቴራባይት የብልግና ምስሎችን ያግኙ »

Commercial Bank of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ commercialbankofethiopian — Commercial Bank of Ethiopia C
የሰርጥ አድራሻ: @commercialbankofethiopian
ምድቦች: ቁማር
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.11K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1700 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-02 14:49:01 Call for Written Exam Architect Electrical Engineer Senior Electrical Engineer

Dear Applicants, Thank you for your application for the positions of Architect, Electrical Engineer and Senior Electrical Engineer for Commercial Bank of Ethiopia. We are pleased to invite you to take a written exam on Wednesday Oct 19, 2022 at 03:00 local time (morning) at CBE Zagwe Building conference room, Lideta, Addis Ababa. N.B. You are required to provide your ID card or Passport. Using a mobile phone is prohibited. Please check name lists of applicants to seat for the written exam using the following links: https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Electrical_Engineer_1dea28a655.pdf https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Senior_Electrical_Engineers_109d3f48a3.pdf https://combanketh.et/cbeapi/
4.4K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 17:56:46 ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓቶች ይፈፀማል!
==========================================
በአዲስ አበባ ከሰኔ 1 ጀምሮ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ወርሃዊ የድህረ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ  ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ የሚፈፀም ይሆናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት አመታት ባከበተው ልምድ  በሲቢኢ ብር እና በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች ደንበኞች የተቀላጠፈ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ እንዲያገኙ አሁንም የአገልግሎቱን ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል።
እስካሁን በርካታ የመብራት ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያቀርባቸው እና ፈጣን እና አስተማማኝ በሆኑት የሲቢኢ ብር ፥ ሞባይል ባንኪንግ እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶች በመጠቀም የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያቸውን በመፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡

እርስዎስ የኤሌክትሪክ ፍጆታዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ለመክፈል ተዘጋጅተዋል?

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆናችሁ ደንበኞች አቅራቢያቹ በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ ሲሆን፣ የሲቢኢ ብር አገልግሎት መጠቀም ካልጀመሩ ደግሞ
• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ተመዝግበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ነጻ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ።
5.7K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 17:26:14 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህብረተሰቡ ከዘመናዊ የክፍያ ስርአት ጋር እንዲላመድ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
•  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ቂርቆስ ዲስትሪክት የባንኩን የነዳጅ ግብይት አማራጮች የሚያስተዋውቅ መርሃ-ግብር አካሂዷል፡፡
===============
ቅዳሜ ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም በቡልጋሪያ አካባቢ ቶታል ማደያ የተካሄደውን መርሃ-ግብር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዕከላዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኪዳኔ መንገሻ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የባንክ አገልግሎትን በማስተዋወቅና ህብረተሰቡ ከዘመናዊ የክፍያ ስርአቶች ጋር እንዲላመድ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በባንኩ 63 በመቶ ያህል የገንዘብ እንቅስቃሴ በዲጂታል የክፍያ አማራጮች አማካይነት የሚፈፀም ነው ያሉት አቶ ኪዳኔ፤ ባንኩ 18 ሚሊዮን ያህል የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞችና የተለያዩ የዲጂታል ባንክ አማራጮች ባለቤት መሆኑ የነዳጅ ግብይቱን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

መርሃግብሩ የባንኩን የነዳጅ የክፍያ አማራጮች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የተናገሩት የቂርቆስ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሸምሱ በርጌቾ በበኩላቸው አገልግሎቱን የበለጠ ለማጠናከር የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የሽያጭ ባለሞያዎችና የባንኩ ሰራተኞችና ቅርንጫፎች እስካሁን ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና እና እውቅና ስነ-ስርዓትን ጭምር ያካተተ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

በዕለቱ በቂርቆስ ዲስትሪክት የባንኩን የነዳጅ ክፍያ አማራጮች በመጠቀም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ማደያዎች፣ የሽያጭ ባለሞያዎች፣ የባንኩ ባለሞያዎችና ቅርንጫፎች የተበረከተላቸውን የማበረታቻ ሽልማቶች ተቀብለዋል፡፡ ከቂርቆስ ዲስትሪክት ጋር የስራ ግንኙተት ፈጥረው እየሰሩ ለሚገኙ 20 ማደያዎችም የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አማራጮችን ማስተዋወቅ አላማ ባደረገው መርሃ-ግብር ላይ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የባንኩ ደንበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የማዕከላዊ ሪጅን የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የቂርቆስ ዲስትሪክት አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡
5.3K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 22:27:12 የኢትየጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ሀላፊዎች ከሐምሌ ወር ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የሚተገበረው የዲጂታል ክፍያን አስመልክተው ተወያዩ።
==========================
በአገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል ሥርዓት የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል፡፡

ይህንን አስመልክቶ የኢትየጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች በአተገባበሩ ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይቱም እስካሁን የመጡበትን የትብብር መንገድ በመገምገም በቀጣይ አብረው በሚሰሩበት እና መሻሻል በሚያስፈልጋቸው ዘርፎች ላይ መክረዋል።

እስካሁን 30 በመቶ ብቻ የሚሆኑ ተገልጋዮች በዲጂታል የክፍያ አማራጭ ክፍያቸውን የሚፈፅሙ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከግንቦት መጨረሻ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ወርሃዊ የድህረ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ   ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ የሚፈፀም ይሆናል።

አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማገዝ ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ቀላል ለማድረግ እንዲሁም የበለጠ ለማስፋት በሁሉም ማዕከላት የዲጂታል አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

የኢትየጵያ ንግድ ባንክ  ከመብራት፣ ውሃ እና ሎሎች የዲጂታል ክፍያዎች በተጨማሪ በቅርቡ የነዳጅ ክፍያን በሲቢኢ ብር አማካኝነት እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡
4.7K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 17:02:24 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ለተቀጠሩ ሠራተኞች ለ11 ወራት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
===========================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በማኔጅመንት ትሬኒ የሥራ መደብ አዲስ ለተቀላቀሉ 76 የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች የባንኩን አሠራር እና የሥራ ባህል የሚያሳይ የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ሥልጠና ከግንቦት 15 ቀን 2015 ጀምሮ በባንኩ የልሕቀት ማዕከል መስጠት ተጀምሯል፡፡

የባንኩ የሰው ኃይል ምልመላ እና ዕድገት ባለሙያ አቶ ዘይኑ ከማል እንደገለፁት ለአዲሶቹ ሰልጣኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ጊዜያት ያሳለፋቸው የእድገት ጉዞዎች፣ በፋይናንስ ገበያ ውስጥ ያለው ድርሻ፣ በባንኩ መሪ እቅድ እና የለውጥ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ትምህርታዊ ገለፃ ይደረግላቸዋል፡፡

ሰልጣኞቹ በባንኩ የልህቀት ማዕከል ከሚሰጣቸው የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በተጨማሪ የሥራ ላይ ሥልጠና በአጠቃላይ ለ11 ወራት እንደሚሰጣቸው አቶ ዘይኑ አክለው ገልፀዋል፡፡

ከስልጠና ተሳታፊዎች መካከል የሆነው ብሩክ ልዑልሰገድ በሰጠው አስተያየት ለባንክ ሥራ አዲስ መሆኑን ገልፆ ስልጠናው ስለባንክ ሥራ የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር እውቀት ለማግኘት እንደሚረዳው ተናግሯል፡፡

ሌላዋ የሥልጠናው ተካፋይ ብስኩቴ መሐመድ በበኩሏ፣ ስልጠናው በሥራ ላይ የሚሰጣትን ኃላፊነት በተገቢው መንገድ ለመወጣት እንደሚያስችላት ገልፃለች፡፡
6.5K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 19:29:35 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን በማስፋት የ “ዲጂታል ኢትዮጵያ”ን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።
============
ባንኩ በዲጂታል ነዳጅ ክፍያን ለማቀላጠፍ ከ1074 በላይ ከሚሆኑ ማደያዎች ጋር  እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።


በመላው አገሪቱ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ብቻ እንዲከናወን በተወሰነው መሰረት  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል ነዳጅ ክፍያን ለማቀላጠፍ የሚረዱ መተግበሪያዎችን በማቅረብ ቀልጣፋ ፤ፈጣን  አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን ዛሬ በተከናወነው የማበረታቻ መርሃ ግብር ተገለጸ።


በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ዶ/ር አለሙ ስሜ እንደገለጹት የአገሪቱን ሀብት  እና በየአመቱ ከ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያስወጣውን ነዳጅ በአግባቡ ለመጠቀም የዲጂታል የግብይት ስርአት ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳለው ጠቁመው ይህም የ “ዲጂታል ኢትዮጵያ”ን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል።


በባንኩ በቦሌ ዲስትሪክት ስር በሚገኘው ቶታል ማደያ ስር በተከናወነው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የባንኩ የሪቴል እና ብራንች ባንኪንግ  ኤክስኪዩቲቭ  ም/ፕ አቶ ፍቅረስላሴ ዘውዱ እንደተናገሩት ወደ 40 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞች ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱን ተደራሽነት እያስፋፋ መሆኑን ጠቁመው በያዝነው የስራ ዘመን ብቻ ከ 2.5 ትሪሊየን ብር በላይ የዲጂታል ገንዘብ እንቅስቃሴዎች እንደነበር ገልጸዋል።


የነዳጅንም ክፍያ ባንኩ ባቀረባቸው የሲቢኢ ብር እና “ነዳጅ” በተሰኙ መተግበሪያዎች ተጠቃሚዎች እየተገለገሉባቸው መሆኑን የገለጹት አቶ ፍቅረስላሴ ከጥሬ ገንዘብ ነጻ የሆነ ማሕበረሰብን ለመፍጠር ለሚደረገውን ጥረት የጎላ አስተዋጽዎ እንደሚኖረው እና ወደ ባንክ የሚገባው ገንዘብ በመጨመሩ ትልልቅ ሃገራዊ ልማቶችን ለማጠናከር እንደሚረዳም ገልጸዋል። በአገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ነዳጅ ማደያዎችም ፈጣን፤ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ የሆኑየክፍያ አገልግሎቶችን እያስፋፋ እንደሚሄድ ተቁመዋል።   


የቦሌ ዲስትሪክት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሌንሴ ገለታ በወቅቱም እንደገለጹት የባንኩ ሰራተኞች በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በመገኘት የሲቢኢ ብር እና የ”ነዳጅ” መተግበሪያዎችን አጠቃቀም በማስረዳት እና ደንበኞችም ችግር ሲያጋጥማቸውም ፈጣን ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው። በዚህም በነዳጅ ማደያዎች ላይ የነበረው መጨናነቅ በማስቀረት የባንኩ ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ጠቁመው አሁንም በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች እስከ ምሽት ሰዓት በመገኘት ፈጣን ድጋፍ እያረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።
5.5K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 14:01:02 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን በ54 ነጥብ እየመራ ነው፡፡
==========
ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመቀላቀል ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች ብቻ የቀሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን፣ ቀጣይ  ጨዋታውን  በሊጉ በአራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ጋሞ-ጨንቻ ጋር ያደርጋል፡፡

ጨዋታው አርብ ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የሚከናወን ሲሆን፣ ቡድኑ ይህን ጨዋታ በድል ካጠናቀቀ አንድ ጨዋታ እየቀረው ፕሪምየር ሊጉን መቀላቀሉን ያረጋግጣል፡፡ 

የቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ መመለስ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞችና ለሌሎች የቡድኑ ደጋፊዎች ታላቅ የምስራች እንደሚሆን አልጠራጠርም ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ፣ የስፖርት ቡድኑ ተጨዋቾች፣ አሰልጣኞችና አመራሮች ቀሪዎቹን ጨዋታዎች በድል በማጠናቀቅ ወደ ፕሪምየር ሊግ የሚያደርገውን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ጠንክረው መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ 

እንደ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ገለጻ ባንኩ የእግር ኳስ ቡድኑን ወደ ቀድሞው መልካም ስሙ ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ነው፡፡ በመጪው ዓመት የፕሪምየም ሊግ ጨዋታዎች ቡድኑ በተሻለ ብቃት ተሳታፊ እንዲሆንም አስፈላጊው ዝግጅትና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ላይ በአዲስ አበባና ዙሪያው የሚገኙ የባንኩ ሰራተኞች፣ የቡድኑ ደጋፊዎችና የስፖርቱ ቤተሰቦች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመገኘት ቡድኑን እንዲያበረታቱ አቶ አልሰን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቡድኑ የሚያካሄዳቸው ሁለት ቀሪ ጨዋታዎችም በብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ላይ በቀጥታ ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡
152 views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:52:17 Commercial Bank of Ethiopia Vacancy 2023 (01 IT Officer Jobs)

Commercial Bank of Ethiopia Vacancy 2023 (01 IT Officer Jobs): Recently Commercial Bank of Ethiopia has drafted a job vacancy announcement Addis Zemen notification on May 15, 2023. Ethiopian Jobseeker may apply for this job on or before May 26, 2023.
The Commercial Bank of Ethiopia (CBE) is the largest commercial bank in Ethiopia. As of June 2015, it had about 303.6 billion Birr in assets and held approximately 67% of deposits and about 53% of all bank loans in the country. The bank has around 22,908 employees, who staff its headquarters and its over 1000+ branches positioned in the main cities and regional towns.


Commercial Bank of Ethiopia Vacancy 2023
Hiring OrganizationCommercial Bank of Ethiopia Trade UnionPost NameIT OfficerTotal Vacancy01Opening DateMay 15, 2023Closing DateMay 26, 2023Job CategoryBank Jobs
Commercial Bank of Ethiopia Job Vacancy 2023 Details
Organization Type: Private Jobs
Employment Type: Full Time
Department: HR Department
Salary Offer: As per the bank salary scale
Workplace: Addis Ababa
Position: IT Officer
Official website:

Key Duties & Responsibilities
Manage, Design, develop, update and maintain the Union’s database, web site, portals, applications, social media channels, and other communications vehicles
Plan, organize, implement and report all IT activities of the Union periodically
Set up workstations with computers and necessary peripheral devices (routers, printers etc.)
Check computer hardware to ensure functionality
Install and configure appropriate software and functions
Manage regular servicing of computers in use at offices
Develop and maintain local networks in ways that optimize performance
Ensure security and privacy of networks and computer systems
Perform troubleshooting to diagnose and resolve problems
Maintain records/logs of repairs and fixes and maintenance schedule
Provide technical assistance to employees in computer and other IT equipment issues across the office
Performs other related duties given by president/ office manager
Job Requirement
Qualification: B.A. degree in computer science, Information technology, information
science and related subjects from a recognized higher educational institution
Experience: zero years of work experience required Year of graduation starting from June 2021G.C
Additional skill and competence
In depth understanding of diverse computer systems and networks
Certification as IT Technician will be an advantage (e.g. CompTIA A+, Microsoft Certified IT Professional)
Knowledge of digital camera operation
Excellent in written and verbal communication in Amharic, English and other languages (if possible);

Application Process
Interested applicants are required to submit your application letter, non-returnable photocopies of your credentials and CVs physically to our office or in PDF through
our email address within 10 consecutive working days from the date of this announcement.
Address: Email: cbetradeunion@gmail.com; Tel. phone no. 8679
Our office is in Addis Ababa- Legahar at the back of CBE Head Office or Finifine Branch
Only short-listed candidates will be contacted.
Contact Details
Commercial Bank of Ethiopia Trade Union
Addis Ababa, Ethiopia
Tip: Before you start looking for jobs and completing online job applications, you’ll need an updated version of your resume ready to upload. You may also need a cover letter to apply for some jobs.

#cbe #cbenews
2.2K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 19:05:18 የስራ ማስታወቂያ በቅርብ ቀን ይወጣል ተከታተሉን ። ያልሰማ ካለ እንዲቀላቀሉ አድርጉ።
2.7K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 19:03:43 Live stream finished (3 minutes)
16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ