Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @yefkrtarik
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.01K
የሰርጥ መግለጫ

🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹
➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1
Since 2011 E.C.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-03-08 20:03:57 ​​❦ ​​​​​​══•⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             የፍቅር ንቅሣት

                                     ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ



የጓደኛዬ ብዬ የነገርኩሽ ታሪክ ሁሉ ያንቺ ነበር አለችኝ። እንዴት ያስቃል ለካ የራሴን ጉድ ነበር ምክር ስሰጥበት የቆየሁት ሁሌ ክፍል በመጣች ቁጥር ቅድስት እኮ አብርሽ እንዲህ አርጓት እያለች የራሴን ታሪክ ትነግረኛለች፤አንቺ ብትሆኚ ምን ታደርጊ ነበር እያለች ስለምትጠይቀኝ እኔም ራሴን በቦታው አድርጌ እያሠብኩ እነግራት ነበር።የነገረችኝ ታሪክ<አብርሽ ቅድስትን ሳያዋራትም ሳያገኛትም እነሡ ት/ቤት ምትማረዋን ልጅ ግን ሁሌ ጠዋት ጠዋት ት/ቤት ድረስ ይሸኛታል፤እና የtg profilun የልጅቷን ፎቶ ነው እያቀያየረ ሚያረገው ቅድስት ግን ይሄን አታቅም ብነግራት ምን ታስቢያለሽ> ስትለኝ <ብትነግሪያት ጥሩ ነው ግን እኔ እሧን ብሆን የምልሽ ምናልባት የtg profile ማድረጉ የgame ትዕዛዝ ይሆናል፤ት/ቤት መሸኘቱም ቢሆን በአጋጣሚ እየተገናኙ ይሆናል።ግን ሮቢ እኔ ምማርበት ት/ቤት ድረስ እየመጣ ባያገኘኝ ስለ እውነት በጣም ነው ቅር የሚለኝ>አልኳት።እሧም እንደመናደድ እያለች<ይሄን ያህል ማመንም በኀላ ሚጎዳው ራስሽን ነው፤ትንሽ ተጠራጠሪ>ትለኝ ነበር።እኔም በሀሳቧ ስላልተስማማው የሁል ጊዜ ጭቅጭቃችን ነበር።እና የነገርኩሽ ታሪክ ያንቺ ነው ያለችኝ ይሄ ነበር፤እኔ እያለቀስኩ ከዚ በላይ እንዳትነግረኝ በአይኔ ከመለማመጥ ውጪ ምንም አላደረኩም።እሧ ቀጠለች<የገና ጊዜ ተዘጋጅቶ ሁሉም ተማሪ ሄዶ አንቺ ብቻ ያልሄድሽበት ፓርቲ ላይ እዛው አብሯት ሲጨፍር ከነበረችው ልጅ ጋ ሲሳሳም ነበር>አለችኝ።ከዚ በላይ መስማት አልቻልኩም፤በጣም አመመኝ። እረፍት ሠአት ደርሶ ስለነበር እንደ ምንም ጓደኞቼ አረጋግተውኝ ስላላመንኳቸው ስልኩን ነግሬያቸው tg ላይ search አድርገው profilun አሣዩኝ፤ከዚ በላይ ለሡ ምከራከርበት አቅም አጣው።profilu ላይ የሧ በዛ ያሉ ፎቶዎች እና ሁለቱ የተፃፃፉትን screenshot ተደረጎ ነበር፤ፅሁፉ የሚለዉ
<ፍቅሬ
ወዬ
አሸነፍኩሽ አይደል
ላንተ ስለሆነ ነዋ
እሺ አፈቅርሻለው
እኔም በጣም እወድሀለው አፈቅርሀለው>
ነበር።ፓርቲው ላይ የነበሩ ከግማሽ የማያንሱ የክፍላችን ተማሪዎችም ሲሳሳም እንዳዩት ነገሩኝ።ግን በጣም የሚገርመው እስካሁን የሇነ ስህተት እንዳለ እንጂ ሮቢ ይሄን ያደርጋል ብዬ መቀበል አልቻልኩም።አለማመኔ የገባቸውም ጓደኞቼ በምሳ ሠአት ላይ እውነቱን ሁሉ እሧ እንድትነግረኝ የልጅቷ ክፍል ይዘውኝ ሄዱ።ልጅቷን ጠርተናት ከመጣን በኀላ ጓደኛዬ ሁሉን ነገር እንድትነግረኝ ጠየቀቻት፤ልጅቷ መጀመሪያ ልትሸፋፍነው ብትሞክርም ጓደኛዬ አፋጣ ስለያዘቻት ሁሉንም ነገረችኝ ጓደኞቼ ከነገሩኝም ሌላ ብዙ ነገር ነገረችኝ አሁንም ካላመንሽ ደሞ እደውልለታለው ብላ ደወለችለት፤መቼም እኔ ከሣምንት የበለጠ ጊዜ ስደዉልለት ሣያነሳ ለሧ እንደማያነሳ እርግጠኛ ሆኜ ነበር፤ግን እሡ ምን በወጣው ብዙም ሣይጠራ አንስቶላት በኅላ ት/ቤት መጥቶ እንደሚያገኛት ተነጋግረው ስልኩ ተዘጋ።እኔም ጉዴን አውቄ እንባዬን እየዘራው ወደ ክፍል ሄድኩኝ፤ምንም ሣልናገር ሣልጋገር ወደ ቤት መሄጃ ሠአታችን ደረሠ።ልጅቷ መጥታ ለምን አሁን ሲመጣ ሁለታችን አብረን ሆነን አናፋጥጠውም አለችኝ፤ምንም አልመለስኩላትም ጓደኛዬ ግን በሀሳቧ ተስማምታ ውጪ ሆነን መጠበቅ ጀመርን።

✎ ክፍል አስራ ስድስት (16) የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል... 
ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
        ••●◉Join us share
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
11.3K views , 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 21:15:38 ​​❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             የፍቅር ንቅሣት


                                     ክፍል


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ



       ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።በዛ ላይ እኔም ስልኬ ጠፍቷል እንደ በፊቱ አናወራም፤አሁን ገና ርቀታችን እየተሠማኝ መጣ።ሮቢን እንደ በፊቱ ባላገኘውና ባላወራውም ለሡ ያለኝ ፍቅር ቅንጣት እንኳን አልቀነሠም ነበር፤እንዲያውም ከነሠፍቆቱ ጋ ተደምሮ ፍቅሩ እጅግ በረታብኝ።ከ9 ወደ 10ኛ ክፍል ያለፍኩት ያው እንደተለመደው በደረጃ ቢሆንም የዘንድሮ ግን ያሳስባል፤ጥር ወር ውስጥ የ1st semester final exam ስለነበር ለማጥናት ብሞክርም አልቻልኩም፤ሀሣቤ ሁሉ ሮቢ ሆኗል።አሁንማ በስልክ እንኳን ካወራን 1 ሳምንት ከ3ቀን ሆኖናል።ጥር 14/2010አ.ም ማክሰኞ ቀን ከጊዜ በኀላ እንዳመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ክፍል ውስጥ ቆዝሜ ተቀምጬ አንድ ጓደኛዬ መጥታ አጠገቤ ተቀመጠችና<ኧረ ምንሼ ርብቂ ሮቢ ሚሠራው ስራ ምንም አይነፋም fb ላይ ሚለቃቸው ፎቶዎች እና ሚሠጣቸው comment አንቺን ሲያፈቅርሽ ከነበረው ሮቢ አይጠበቅም>አለችኝ።ለራሴ ግራ ገብቶኝ ብቻዬን እያወራው መሄድ ነው የቀረኝ እሧ እንደዛ ብላኝ አዞረችብኝ።ግን ለሮቢ ያለኝ እምነት እንዲህ በቀላሉ ሚበገር ስላልነበር<በሮቢ account ሌላ ሠው እየተጠቀመ ይሆናል አልኳት፤እሺ እራስሽ አይተሽ ፍረጂ ብላ ከእናቱ ጋ ሆኖ የለቀቀው ፎቶ ላይ የተሠጠውን comment አሳየችኝ።ልጅቷ እኛ ት/ቤት ናት ስለኛ ግንኙነትም በደንብ ነው ምታውቀው የሠጠችው comment የኔ ብቻ ነበር ሚለው የድንጋጤና የፌዝ ሣቅ እየሣኩኝ ወዲያው እሡ መልሶ የሠጣትን ለማየት ከፈትኩት።የሡ ብሶ ቁጭ ፍቅሬ እናቴ ህይወቴ ነበር ሚለው ስልኩን ለቅቄው እየተንቀጠቀጥኩ<አይ አይ ውሸት ነው እሡ አይደለም> እያልኩ ጮክ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ።በዚ ጊዜ አጠገቤ ተቀምጣ ዞራ ስታወራ የነበረችው የልብ ጓደኛዬ የነገረችኝ ልጅ ላይ እንዴት ከፈተና በፊት ትነግሪያታለሽ እያለች ጮኸችባት።ስለዚህ እውነት እያልኩ ለራሴ የተቀመጥኩበት ወንበር ላይ ተቀምጬ መንሠቅሠቅ ጀመርኩ።<በቃ ርብቂ ማወቅሽ ካልቀረ ሁሉንም እነግርሻለው>አለችኝ ጓደኛዬ እኔም እጇን ጥብቅ አድርጌ ይዣት እያለቀስኩ<ውሸት እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ>አልኳት በሚለማመጥ ድምፅ በሠአቱ የነበረን free period አልቆ አስተማሪ እየገባ ስለነበር አሟት ነው ብላ ከክፍል ይዛኝ ወጣች።ግቢ ውስጥ ምሳ ለመብላት ምንጠቀምበት ቦታ ሄድንና ተቀመጥን።ምትነግረኝ ነገር ሮቢን እንደሚያሣጣኝ ስለማውቅ ንገሪኝ ብዬ መጠየቅ ፈራው።ለብዙ ደቂቃዎች ከኔ ለቅሶ ውጪ ሌላ ድምፅ ሳይሰማ ከቆየ በኀላ በረጅሙ ተንፍሣ መናገር ጀመረች።<ርብቂዬ ብዙ ጊዜ ሆኖታል፤ቢያንስ ወር ከምናምን ግን አንቺ ሮቢን ከምታፈቅሪው ይልቅ ሁሌ ምትነግሪን እንደምታምኚው ነው ስለዚህ ሁላችንም ልንነገርሽ አልደፈርንም>በመሀል አቋርጫት አሁንም ቢሆን አምነዋለው ምትሉትን አላምንም አልኳት።ባታምኚኝም ልነግርሽ ይገባል ብላ ንግግሯን ቀጠለች።<የጓደኛዬ ብዬ የነገርኩሽ ታሪክ ሁሉ ያንቺ ነበር> አለችኝ።

✎ ክፍል አስራ አምስት (15) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
        ••●◉Join us share
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
9.7K views , 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 19:37:15 የቀለሟ ባል

ክፍል 2



“ቆይ...... እኔ እዛ ጋር ልሂድ" ብዬ ጎንበስ ብዬ፣ መሬት የነበረውን ቦርሳዬን ሳነሳና ቀለሟ ከተጨማሪ ድንጋይ ዳቦ ጋር ወደ ሳሎን ስትመለስ አንድ ሆነ፡፡

ዘመነኛ ነኝና ዘመነኛ ነገር ለብሼያለሁ፡፡ ከዳሌዬ የሚጀምረው ጠባብ ሱራዬ፣ ጎንበስ ካልኩ : ከመቀመጫዬ | ክፍተት መሀል ገብቶ የሚጠፋውንና እያለ የሌለ የሚመስለውን የክር ውስጥ ሱሪዬን ቁልጭ አርጎ አደባባይ ያወጣል፡፡ ዐይኖቹ ከክሩ ጋር አብረው እንደገቡ አውቄያለሁ፡፡

“ደህና ዋልክ የኔ ጌታ?" አለች ወደ መሬት ባልዋ እያየች፡፡ “ርቦኛል' ወደኔ እያየ ወደርስዋ ተናገረ፡፡ እየተጣጠፈች ወደ ጓዳ ገባች፡፡

“አንቺ… እዛ ኢዩ" መንገድ ላይ አይደል የምትሠሪው…?" አለኝ፣ ፈገግታ የሚመስል ነገር እያሳየኝ፡፡ “አዎ

“ከዚህች ጋር ደሞ በምን ገጠምሽ…?"

ከዚህች ጋር የሚለው፣ “መሬት” የምትለውን ባለቤቱን መሆነ

ነው፡፡

ምን እንዳገናኘን ነገርኩት፡፡

“ነው እንዴ…? ጥሩ"
ቀለሟ እንጀራ የተነጠፈበት ትሪ ይዛ ስትመጣ ሰበብ ፈጥሬ ተሰናብቼያቸሁ ወጣሁ፡፡ ማታ አራት ሰዐት ተኩል ላይ ለቢዝነስ ከቆምኩበት ቦታ መኪና ቆመ፡፡ እንደ ልማዴ መስኮቱን ደገፍ ብዬ ላነጋግር ጎበጥኩ፡፡

ውስጥ ገባሁ፡፡

“ከኔ ምትገናኚ ከሆነ ከሚስቴ መገናኘት አትችይም!... ገባሽ?” በቁጣ ተናገረኝ፡፡

“ገብቶኛል”

የቀለሟን “መሬት” ባል ስረግጠው ላድር ነው፡፡

ለራሱ ጉዳይ ሳይቀር አካልቦ አግኝቶኝ፣ ከከተማችን ውድ ከሆነ ምግብ ቤት፣ “ምሳ እንብላ" ኪስን ከሚያደርቅ ኬክ ቤት፤ “ቁርስ እናድርግ" ገቢን ከሚፈታተን ሻሂ ቤት፣ “ሻይ ቡና እንበል" ብሎኝ፤ ከመግደርደር በቀር፤ ከማስፈራራት በቀር ከፍሎ የማያውቀው አንድ ወዳጄ፣ ዛሬም እኔ ኪሴን አካለሁ አንቺ ትክፍያለሽ' በተሰኘችው የተበላች ብልጠቱ ሲያነፍረኝ አንድ ሰሞን “መንገደኛ” ከተሰኘ መጽሐፍ ውስጥ የተዋወቅኳቸውን አቶ ከበደን መሆን አማረኝ። ለመሆኑ አቶ ከበደ ማን ናቸው? አቶ ከበደ የአቶ ደበበ ወዳጅ ናቸው፡፡

አቶ ከበደ በቀበሌ መዝናኛ መጠጥ ቤት በተደጋጋሚ ሒሳብ ሲከፍሉ፣ አቶ ደበበ _ ደግሞ፣ “በእኔ ልክፈል" ማግደርደር በደረታቸው በኩል ካለው የኮታቸው የውስጥ ኪስ እየገቡ መበርበራቸውን አላቆሙም።

አቶ ከበደ ዘወትር ይከፍላሉ፡፡ አቶ ደበበ ዘወትር ያችኑ ቦታ ይበረብራሉ፡፡
ከፍለው ግን አያውቁም፡፡ ሁኔታው ያስመረራቸው አቶ ከበደ አንድ ቀን፣ “ደበበ፣ እሱ ነገር ብር ተሆነ ክፈለው፡፡ ተባይ ተሆነም ግደለው" አሏቸው::


ይህች ታሪክ በይሉኝታ እግረ ሙቅ ተይዘን ለደበበዎች ከበደ መሆን ላቃተን ደህና አደፋፋሪ ናት።

ተፈፀመ

ምንጭ : ፍቅፋቂ ወጎች

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
    @Yefkrtarik    @Yefkrtarik


        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
1 view16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 19:37:00 ሳቄን መልስልኝ


ተግባር ላይ ያልታየ
                    ቃልህን አምኜ
         እንተን ብቻ እያሰብኩ
              ሰማይ ምድር ሁኜ
                 ፊደል አሳምረክ
                  የሰጠከኝ ተስፋ
               ድንገት ስትለይኝ
                ሳቄን ይዞት ጠፋ፡፡

                   ሳቄን መልስልኝ
                   ልቤን ትቸዋለሁ
                 ልብ ማለት ቀርቶ
             መስማት ጠልቻለሁ።

ምንጭ bewketuseyoum19

                  
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!

  ይከታተሉን | Follow us፡
    @Yefkrtarik    @Yefkrtarik


        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
6 views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:15:46 የቀለሟ  ባል

  ክፍል 1

         እናቴ ትሙት መሬት እኮ ነው፣ መሬት ታውቂያለሽ…?
በቃ መሬት፡፡ እረግጠዋለሁ፤ ዝም፡፡ በትዳር መባረክን የመሰለ ምን ነገር አለ አንቺ….?'

“ደስ ይላል፣ በጣም ዕድለኞች ናችሁ" አልኩኝ፤ በድርቀቱ ለመበላት ሳይሆን ሰው ለመፈንከቻነት የቀረበውን ድፎ ዳቦዋን በሁለት እጆቼ ትብብር ለመስበር እየሞከርኩ፡፡

“በጣም እንጂ፡ ለነገሩ ትዳር ዕድል አይደለም፤ አያያዝሽ ነው….. ገባሽ..?" በፊት በፊት ከትምህርት ቤት ስመጣ ባለጌ ጎረምሶች እንደሚጠቅሱኝ ጠቀሰችኝ፡፡

“እህ... ገባኝ” ብዬ መለስኩ፡፡

“አይ... አልገባሽም... ምንድነው _ መሰለሽ... ወንድ ልጅ የሚፈልገውን ቤቱ ካገኘ እግር አያወጣም፤ ገባሽ አይደል…?”

“እህ…ገባኝ!” አልኩኝ፣ ተጨማሪ  ማብራሪያ እንዳትሰጠኝ በመስጋት

“አይ..... አልገባሽም...... የሴትነት ሥራሽ ኩሽና ብቻ አይደለም፡፡ ወንድ ልጅ ንጹሕ….. ራስዋን የምትጠብቅ…. ነብር ሴት ነው የሚወደው ገባሽ....?"

የማይመቸው ሶፋዋ ተከፍቶ ቢውጠኝ ደስ ባለኝ፣ አልውጥ ሲለኝ፤ ዝም አልኩ፡፡ እንዳልገባኝ በማመን ቀጠለች፡፡
አየሽ ሆና ባህል ሴት ይጨቁናል፤ እና' ሴት ልጅ አልጋ ውስጥ እንዲህ ይሁን እንዲህ እናድርግ ስትል፤ ብልግና ነው ይሉናል ባልሽ ግን እንቺን ጥሎ ሄዶ የሚማግጠው ከወንድ ነው እንዴ?
አይ በስማም - ኸረ ኣይደለም አልኩኝ የሷን መልስ ሳልጠብቅ፡፡

"አም.. እንዳንቺው ካለች ሴት ነው፡፡ ያቺ ሴት ካንቺ በምን

በለጠች………” ወንድ መያዝ ታውቅበታለች፣ ገባሽ?"

ሠራተኛዋ ሻይ ይዛ ስትገባ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈስኩ፡፡

በዚህ መሀል፣ ዳቦ ይጨመር ብላ መዐት ሰውነትዋን ይዛ

ጓዳዋ ገባች። ሠራተኛዋ፡ ስኳር ብርጭቆው ውስጥ ጨምራ ቀና ከማለትዋ መሬቱ የቀለሟ ባል፤ ዐይን የማይጎረብጥ መልኩን ይዞ ወደ ቤት ገባ።

በሰርግ ፎቶዋቸው እንጂ በአካል ዐይቼው አላውቅም፡፡

ሰላም እንዴት ነህ? አልኩ፣ ዳቦውን ለመቁረስ በተደረገው ትግል ጭኔ ላይ የተራገፉትን የዳቦ ስብርባሪዎች በአንድ እጄ እያራገፍኩ።

ለብ ያለ ሰላምታ ሰጥቶኝ፤ ካልጠፋ ቦታ ሁለት ሙሉ ሰው በቅጠ የማያስቀምጠው ጠባብ ሶፋ ላይ ካጠገቤ ተቀመጠ፡፡ የምንቀራረብ ሰዎች ብንሆንና የኔ መማቀቅ ባይጨመርበት፣ እንደ ልጅ ቢያቅፉ ሳይመኝ አይቀርም፡፡

                  
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
    @Yefkrtarik    @Yefkrtarik

        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
934 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 18:15:37 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

ሰላም ቤተሰቦች ቃል በገባነው መሰረት አዲስ ታሪክ ለቀናል !!! የናንተን አስተያየት እና ድጋፍ እንሻለን ።

@Rominya_1
        
  ይከታተሉን | Follow us፡
    @Yefkrtarik    @Yefkrtarik


        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
898 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 20:12:02
ውድ ውድ የ ፍቅር ታሪክ  ተከታዮቻችን

እንደሚታወቀው እስከዛሬ ድረስ ቻናላችን የ ተለያዩ የ ፍቅር ነክ ፖስቶችን እና ታሪኮችን ሲያካፍለን እንደቆየ ይታወቃል

- አሁን ላይ ደሞ ከ ቀድሞውኑ ይበልጥ ተሻሽሎ የቀረቡ አጫጭር እና አስተማሪ የፍቅር ታሪኮች ሊያካፍላቹ ዝግጅቱን ጨርሷል !

- እናም በዛው ለ ፍቅረኛችሁ ፣ ለዘመድ ፣ ለጓደኛ ፣ ለቤተሰብ ታሪኮችንን ያጋሩ  ።

በመጨረሻም የኛ የቻናላችን የ ጀርባ አጥንት የሆናችሁት እናንተ ተከታዮቻችን በእናንተ እገዛና ብርታት እዚ መድረሳችን ይታወቃል አሁንም ድጋፋችሁ እንዳይለየን እያልን እኛም በቅርቡ ከችችችች እንላለን

@Rominya_1 contact ማድረግ ትችላላችሁ

ሰላም ቆዩን ጎናችንን ናቹ

@Yefkrtarik @Yefkrtarik

        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
​​​​
672 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 21:14:22
ህጋዊ የሆነ ለ 11ኛ ና የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተከፈተ ና ከ ትምህርት ሚኒስተር እንዲሁም የፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው የተማሪዎች የፈተና መዘጋጃ ቻናል።

ትምህርት ሚኒስቴር
1 view18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 21:01:22 ቤቲንግ ለምትመድቡ ሁሉ ይህን ምርጥ ቻናል እናስተዋውቃቹ

ብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው ቀማሪዎች የተከፈተ ብችኛ ታማኝ ቻናል ነው ከኛጋ በመሆን ከሳምንት እስከ ሳምንት አሸናፊ ለመሆን ቻናሉን JOIN ያድርጉ
64 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 20:57:45
ገራሚ የፍልስፍና ቻናል ልጋብዛችሁፍልስፍናን ከኛ ጋር
74 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ