Get Mystery Box with random crypto!

የቀለሟ ባል ክፍል 2 “ቆይ...... እኔ እዛ ጋር ልሂድ' ብዬ ጎንበስ | የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

የቀለሟ ባል

ክፍል 2



“ቆይ...... እኔ እዛ ጋር ልሂድ" ብዬ ጎንበስ ብዬ፣ መሬት የነበረውን ቦርሳዬን ሳነሳና ቀለሟ ከተጨማሪ ድንጋይ ዳቦ ጋር ወደ ሳሎን ስትመለስ አንድ ሆነ፡፡

ዘመነኛ ነኝና ዘመነኛ ነገር ለብሼያለሁ፡፡ ከዳሌዬ የሚጀምረው ጠባብ ሱራዬ፣ ጎንበስ ካልኩ : ከመቀመጫዬ | ክፍተት መሀል ገብቶ የሚጠፋውንና እያለ የሌለ የሚመስለውን የክር ውስጥ ሱሪዬን ቁልጭ አርጎ አደባባይ ያወጣል፡፡ ዐይኖቹ ከክሩ ጋር አብረው እንደገቡ አውቄያለሁ፡፡

“ደህና ዋልክ የኔ ጌታ?" አለች ወደ መሬት ባልዋ እያየች፡፡ “ርቦኛል' ወደኔ እያየ ወደርስዋ ተናገረ፡፡ እየተጣጠፈች ወደ ጓዳ ገባች፡፡

“አንቺ… እዛ ኢዩ" መንገድ ላይ አይደል የምትሠሪው…?" አለኝ፣ ፈገግታ የሚመስል ነገር እያሳየኝ፡፡ “አዎ

“ከዚህች ጋር ደሞ በምን ገጠምሽ…?"

ከዚህች ጋር የሚለው፣ “መሬት” የምትለውን ባለቤቱን መሆነ

ነው፡፡

ምን እንዳገናኘን ነገርኩት፡፡

“ነው እንዴ…? ጥሩ"
ቀለሟ እንጀራ የተነጠፈበት ትሪ ይዛ ስትመጣ ሰበብ ፈጥሬ ተሰናብቼያቸሁ ወጣሁ፡፡ ማታ አራት ሰዐት ተኩል ላይ ለቢዝነስ ከቆምኩበት ቦታ መኪና ቆመ፡፡ እንደ ልማዴ መስኮቱን ደገፍ ብዬ ላነጋግር ጎበጥኩ፡፡

ውስጥ ገባሁ፡፡

“ከኔ ምትገናኚ ከሆነ ከሚስቴ መገናኘት አትችይም!... ገባሽ?” በቁጣ ተናገረኝ፡፡

“ገብቶኛል”

የቀለሟን “መሬት” ባል ስረግጠው ላድር ነው፡፡

ለራሱ ጉዳይ ሳይቀር አካልቦ አግኝቶኝ፣ ከከተማችን ውድ ከሆነ ምግብ ቤት፣ “ምሳ እንብላ" ኪስን ከሚያደርቅ ኬክ ቤት፤ “ቁርስ እናድርግ" ገቢን ከሚፈታተን ሻሂ ቤት፣ “ሻይ ቡና እንበል" ብሎኝ፤ ከመግደርደር በቀር፤ ከማስፈራራት በቀር ከፍሎ የማያውቀው አንድ ወዳጄ፣ ዛሬም እኔ ኪሴን አካለሁ አንቺ ትክፍያለሽ' በተሰኘችው የተበላች ብልጠቱ ሲያነፍረኝ አንድ ሰሞን “መንገደኛ” ከተሰኘ መጽሐፍ ውስጥ የተዋወቅኳቸውን አቶ ከበደን መሆን አማረኝ። ለመሆኑ አቶ ከበደ ማን ናቸው? አቶ ከበደ የአቶ ደበበ ወዳጅ ናቸው፡፡

አቶ ከበደ በቀበሌ መዝናኛ መጠጥ ቤት በተደጋጋሚ ሒሳብ ሲከፍሉ፣ አቶ ደበበ _ ደግሞ፣ “በእኔ ልክፈል" ማግደርደር በደረታቸው በኩል ካለው የኮታቸው የውስጥ ኪስ እየገቡ መበርበራቸውን አላቆሙም።

አቶ ከበደ ዘወትር ይከፍላሉ፡፡ አቶ ደበበ ዘወትር ያችኑ ቦታ ይበረብራሉ፡፡
ከፍለው ግን አያውቁም፡፡ ሁኔታው ያስመረራቸው አቶ ከበደ አንድ ቀን፣ “ደበበ፣ እሱ ነገር ብር ተሆነ ክፈለው፡፡ ተባይ ተሆነም ግደለው" አሏቸው::


ይህች ታሪክ በይሉኝታ እግረ ሙቅ ተይዘን ለደበበዎች ከበደ መሆን ላቃተን ደህና አደፋፋሪ ናት።

ተፈፀመ

ምንጭ : ፍቅፋቂ ወጎች

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
    @Yefkrtarik    @Yefkrtarik


        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄