Get Mystery Box with random crypto!

Purity Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ puritytube — Purity Tube P
የሰርጥ አድራሻ: @puritytube
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 13.94K
የሰርጥ መግለጫ

መፅሀፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያላቸው
👉 የስነ-ፆታ (sexual )
👉 ወሲባዊ ንፅህና
👉 የእጮኝነት
👉 የትዳር
👉 ወጣት ተኮር ጉዳዮች ይዳሰሳሉ
We discuss sexual , family and relationship issues from biblical point of view

Contact us @Appeal4purity_bot
💯 #ቅድስና_ለእግዚአብሔር 💯

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-15 22:46:09 ለምን ተበሳጨች??

󾠬እውነት ነው ፤ ብዙ ጊዜ ወንዶች ሴቶቻቸው ለምን እንደሚበሳጩ ማወቅ ይሳናቸዋል፡፡
ለምን

ሴቶች በፍጥረታቸው ውብ ፣ ማራኪ ፣ መስህብ ያላቸው እና ሌሎች መልካም ነገሮች ብቻ አይደሉም፡፡
ይልቁንም በአብዛኛው ውስብስብ ፍጥረቶች ናቸው ፡፡

አንዳንድ ጊዜ በተለይም ምንም ባልተጨበጠ ነገር ሲበሳጩ እነሱን መረዳት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ወንድ ሚስቱ ወይም ፍቅረኛው ስትበሳጭ ማድረግ የሚችለው በጣም የተሻለ ነገር ከራሷ ጋር ጊዜና ቦታ አንዲኖራት መተው ነው፡፡

ይህም ሲባል ለረዥም ጊዜ ወይም ቀኑን ሙሉ መዝጋት ማለት አይደለም፡፡ በፍፁም
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ ለብቻዋ ተዋት ከዛም ተመለስና እሷ በምትወደው መልኩ ፍቅርህን አሳያት ፡፡

ከዛም ራሷ"ምን እነደነካኝ አላውቅም ፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት ተበሳጭቼ ነበር፡፡ አሁን አንተ ስላለህልኝ ተረጋጋሁ፡፡" ልትልህ ትችላለች፡፡

ይሄን መንገድ መጠቀም ካልፈለግክ ፤ በቃ መፍትሔ ፍለጋ ቢያንስ 12 መፅሃፍትን ማገላበጥህ ነው፡፡

󾠬እዚጋ አንድ ምክር ፦ አልበርት አንስታይንም ቢሆን ሁሉም ወንዶች ሴቶቻቸውን መረዳት የሚችሉበት አንድ ጥሩ ቀመር ሊያዘጋጅ አይችልም፡፡
አሁን አሁን ሁሉም ፈላስፎች እና ሳይንቲስቶች በዚህ በእግዚአብሔር ቃል እየተሰማው መጥተዋል፦
"ሚስትህን እስከ ሞት ድረስ ውደዳት እናም ቀሪ ዘመንህን በደስታ ኑር፡፡" አራት ነጥብ፡፡

" ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25-26)

#couples #married

@PurityTube
@PurityTube
2.2K views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 09:15:31
ስለ ፖርን ( Porn ) ያለው እውነታ

" ምናልባት የኢንተርኔት ሂስትሪ ( browser history ) ስላጠፋህ ማንም አላየኝም ትል ይሆናል ግን እግዚአብሄር ያይሀል "

https://instagram.com/reformedbychrist

#General

@PurityTube
@PurityTube
481 views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:13:27 ' #ፍርሃት '

ስሜታቸውን አሸንፈው እግዚአብሄርን ለማስደሰት የቆረጡ ብዙ ወጣቶች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት የግብረስጋ ግንኙነት ፈፅመው ስለማያውቁ የሚጋሩት አንድ የጋራ ስሜት አላቸው

እሱም 'ፍርሃት' ነው

በወንዶቹ በኩል "ምናልባት ባላረካት እንደወንድ አትቆጥረኝ ይሆን?" የሚለው የብዙዎች ፍርሃት ነው፡፡

ሴቶች ደግሞ "ምናልባት ብዙ ቢያመኝ ደስታችንን ወደ ሰቀቀን እቀይረው ይሆን?" የሚለውን ፍርሃት ይጋሩታል፡፡

እውነቱ ግን እነዚህ ፍርሃት የሚመስሉ ስሜቶች አንድ ህፃን ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ከሚሰማው ፍርሃት የተለዩ አለመሆናቸው ነው፡፡

እግዚአብሄርም ቤተሰብም 'ይሁን' ባለው ነገር መጨናነቅ ተገቢ አይደለም፡፡

አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር በሁለት ተጋቢዎች መሃል የግብረስጋ ግንኙነት መጣጣም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የሚሄድ ነገር መሆኑን ነው፡፡

ይልቁንም እግዚአብሄርን በማያከብርና ጊዜያዊ ስሜትን ለማርካት ሲሉ ብቻ ከጋብቻ ውጪ የግብረስጋ ግንኙነትን የተለማመዱ ሰዎች ከእርካታ ይልቅ የፍርሃት ሰለባ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡

ምክንያቱም ገና ከመጀመሪያው ነገሩን የሚጀምሩት"ወይኔ ሃጢያት ነው እኮ!" ፣ "አረግዝ ይሆን?" ፣ "ታረግዝብኝ ይሆን?" ፣ "ቤተሰብ ቢያውቅብንስ?" ፣ "HIV ብያዝስ?" ፣ "ለጓደኞቹ/ቿ ስለእኔ መጥፎ ነገር ቢያወራስ/ብታወራስ?" እና ከመሳሰሉ አስፈሪ ሁኔታዎች ጋር ፊትለፊት በመጋጠም ነው፡፡

ስለዚህ እስከ ጋብቻችሁ ቀን ድረስ በድንግልናና ስሜታችሁን በመግዛት የቆያችሁ ተጋቢዎች ሁሉ ፍርሃታችሁ ተፈጥሮአዊና የሚጠበቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን "You will be fine "

በቅርቡ ለሚያጋቡ ወዳጆቻችዎ #ሼር ያድርጉ

#couples
#General

@PurityTube
@PurityTube
911 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 09:34:50
በህይወታቸው የልብ ሰላም እንዲኖራቸውና ሰዎች በማማከር መርዳትን የሚሹ የሚወስዱት ስልጠና

6 ቀናት ብቻ ቀሩት።መጋቢት 1-3/2015
ፈጥነው ይመዝገቡ
+251980494342
+2519425236531
1.2K viewsedited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 08:57:46 ፍፁም የሆነ ትዳር እንዲኖርህ መጣርህን አቁም!!

በእውነቱ ከሆነ 'የተሻለ ትዳር' እንዲኖርህ ባትጥርም መልካም ነው!!

ይልቁንም ለራስህ የተሻለ ማንነት ለመፍጠር ትጋ!!

ትኩረትህ እግዚአብሄር አንተ እንድትሆን
የሚፈለግውን አይነት ሰው መሆን ከሆነ የዚህ ነገር ውጤቱ ይህ ነው
ሚስትህ የተሻለ ባል ይኖራታል የተሻለ ትዳርም ይኖራችኋል

እርግጥ ነው ከሚስትህ ጋር የተሻለ ተግባቦት መፍጠር መቻል አለብህ፡፡

ግጭቶች በሚኖሯችሁ ጊዜ ለራስህ ተሟጋች ልትሆንና ጭራሽ እሷን ላታዳምጣት ትችል ይሆናል፡፡

መፅሀፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ያስተምርሃል፡፡

" ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤" ያዕ 1: 19

መልስ ለመስጠት ሳይሆን ሚስትህን ለመረዳት የምታዳምጣት ከሆነ የተሻልክ ሚዛናዊ ሰው ሆነሃል ማለት ነው፡፡ የዚህ ነገርም ውጤት ከሚስትህ ጋር የሚኖርህ መልካም ተግባቦት ነው ማለት ነው፡፡

#Married


@Appeal4purity
@Appeal4purity
1.3K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 22:07:07
773 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 21:11:38 ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1 ( 13-14 )

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።


መልካም ሣምንት ።
3.3K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 21:49:55
https://www.youtube.com/channel/UC3o789QG7_d_3kmBx4z0LHA

share and subscribe
557 viewsedited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 14:11:47 መዝሙረ ዳዊት 27

4 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።

መልካም አዲስ ዓመት ።
840 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 00:46:23 ስለ ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አመሠራረቱ፥ በኦሪት ዘፍጥረት 1፥28 ላይ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ
እንደፈጠረው ይገልጻል። ምዕራፍ 2፥18ደግሞ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለምና
ሴት እንፍጠርለት ይላል። በምዕራፍ 2 ስአዳም እርሱን የምትመስልና የእርሱን ኑሮ የምትካፈል
ፍጥረት ሌላ አልተገኘስትም ይላል።

እነዚህ አባባሎች አንድ ብቸኛ የሆነውን ሰውን አንድ ሌላ ረዳት እንዳስፈለገው፣ ያለዚያች ረዳት
ደግሞ ከባድ እንደሆነ ያስተምረናል። እነዚሁ ዓረፍተ ነገሮች በደምብ ሲመረመሩና ሲታዩ ሰው
ከሌላው ፍጥረት ለየት ያለና ብርቱ ጥንቃቄ የተደረገለት መሆኑንም ያስተምራሉ። ከዚህ በተጨማሪ
የአዳምን ብቸኝነት በዙሪያው ያሉ የእንስሳትና የአራዊት ክምችት፣ የገነት መዓዛና ፍራፍሬዎች
ባዶነቱን ሊሞሉ ወይም ደስታ ሊስጡት አልቻሉም። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ሁሉም
ፍጥረታት ከተቃራኒ ጾታ ጓደኞቻቸው ጋር ሲጫወቱ ለአዳም ምንም ዓይነት የደስታውም ሆነ የኃዘኑ
ተካፋይ ሊሆኑለት አልቻሉም። እነሱን ትክ ብሎ ከማየት በስተቀር ምንም አልፈየዱለትም። በዚያ
ፈንታ ይልቅ እነዚያ ሲጫወቱና እሱን ሲያስደስቱት የዋሉት ፍጥረታት ሁሉ ወደየማደሪያቸው ሲጓዙ
አዳም ብቻውን ፈገግ ብሎ መቅረት ብቻ ሆነ። ይሄ ብቸኝነት ነው እንግዲህ እግዚአብሔር
እንዲያስብለት ያደረገው። ይህ አኗኗር ለአዳም መልካም አልነበረም፤ ለአዳም መልካም የሚሆን
ረዳትና አጫዋች እርሱን የሚመስልና የእሱን ኑሮ የሚካፈል ሊኖር አስፈለገው። ያ ካልሆነ በቀር
አዳም ደስተኛ ሊሆን አይችልም። ስለሆነም እግዚአብሔር የፈጠረውን አዳምን በላዩ ላይ እንቅልፍ
እንዲመጣ አድርጎ ከእርሱ ከጎኑ ረዳት የምትሆነውን ሴትን ሰጠው። ይህ እንግዲህ የመጀመሪያው
ጋብቻ ስለሆነ አዳምና ሔዋንን የገነት ሙሽሮች ብለን ልንጠራቸው እንችላለን። የአዳምና የሔዋን
አባት የሆነው እግዚአብሔር በብቸኝነት ጠውልጎና ተስፋ ቆርጦ ለነበረው አዳም የሔዋንን እጅ ጎትቶ
ሲሰጠው ከየት እንደመጣች ስለተረዳ «ሥጋዋ ሥጋዬ አጥንቷ አጥንቴ» በማስት ደስ ብሎት ኑሮውን ጀመረ።
ስለዚህ ነው ጋብቻ የተፈጠረ እንጂ የተፈለሰፈ አይደለም የምንለው።

#General

@PurityTube
@PurityTube
3.6K views21:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ