Get Mystery Box with random crypto!

የቀለሟ  ባል   ክፍል 1          እናቴ ትሙት መሬት እኮ ነው፣ መሬት ታውቂያለ | የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

የቀለሟ  ባል

  ክፍል 1

         እናቴ ትሙት መሬት እኮ ነው፣ መሬት ታውቂያለሽ…?
በቃ መሬት፡፡ እረግጠዋለሁ፤ ዝም፡፡ በትዳር መባረክን የመሰለ ምን ነገር አለ አንቺ….?'

“ደስ ይላል፣ በጣም ዕድለኞች ናችሁ" አልኩኝ፤ በድርቀቱ ለመበላት ሳይሆን ሰው ለመፈንከቻነት የቀረበውን ድፎ ዳቦዋን በሁለት እጆቼ ትብብር ለመስበር እየሞከርኩ፡፡

“በጣም እንጂ፡ ለነገሩ ትዳር ዕድል አይደለም፤ አያያዝሽ ነው….. ገባሽ..?" በፊት በፊት ከትምህርት ቤት ስመጣ ባለጌ ጎረምሶች እንደሚጠቅሱኝ ጠቀሰችኝ፡፡

“እህ... ገባኝ” ብዬ መለስኩ፡፡

“አይ... አልገባሽም... ምንድነው _ መሰለሽ... ወንድ ልጅ የሚፈልገውን ቤቱ ካገኘ እግር አያወጣም፤ ገባሽ አይደል…?”

“እህ…ገባኝ!” አልኩኝ፣ ተጨማሪ  ማብራሪያ እንዳትሰጠኝ በመስጋት

“አይ..... አልገባሽም...... የሴትነት ሥራሽ ኩሽና ብቻ አይደለም፡፡ ወንድ ልጅ ንጹሕ….. ራስዋን የምትጠብቅ…. ነብር ሴት ነው የሚወደው ገባሽ....?"

የማይመቸው ሶፋዋ ተከፍቶ ቢውጠኝ ደስ ባለኝ፣ አልውጥ ሲለኝ፤ ዝም አልኩ፡፡ እንዳልገባኝ በማመን ቀጠለች፡፡
አየሽ ሆና ባህል ሴት ይጨቁናል፤ እና' ሴት ልጅ አልጋ ውስጥ እንዲህ ይሁን እንዲህ እናድርግ ስትል፤ ብልግና ነው ይሉናል ባልሽ ግን እንቺን ጥሎ ሄዶ የሚማግጠው ከወንድ ነው እንዴ?
አይ በስማም - ኸረ ኣይደለም አልኩኝ የሷን መልስ ሳልጠብቅ፡፡

"አም.. እንዳንቺው ካለች ሴት ነው፡፡ ያቺ ሴት ካንቺ በምን

በለጠች………” ወንድ መያዝ ታውቅበታለች፣ ገባሽ?"

ሠራተኛዋ ሻይ ይዛ ስትገባ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈስኩ፡፡

በዚህ መሀል፣ ዳቦ ይጨመር ብላ መዐት ሰውነትዋን ይዛ

ጓዳዋ ገባች። ሠራተኛዋ፡ ስኳር ብርጭቆው ውስጥ ጨምራ ቀና ከማለትዋ መሬቱ የቀለሟ ባል፤ ዐይን የማይጎረብጥ መልኩን ይዞ ወደ ቤት ገባ።

በሰርግ ፎቶዋቸው እንጂ በአካል ዐይቼው አላውቅም፡፡

ሰላም እንዴት ነህ? አልኩ፣ ዳቦውን ለመቁረስ በተደረገው ትግል ጭኔ ላይ የተራገፉትን የዳቦ ስብርባሪዎች በአንድ እጄ እያራገፍኩ።

ለብ ያለ ሰላምታ ሰጥቶኝ፤ ካልጠፋ ቦታ ሁለት ሙሉ ሰው በቅጠ የማያስቀምጠው ጠባብ ሶፋ ላይ ካጠገቤ ተቀመጠ፡፡ የምንቀራረብ ሰዎች ብንሆንና የኔ መማቀቅ ባይጨመርበት፣ እንደ ልጅ ቢያቅፉ ሳይመኝ አይቀርም፡፡

                  
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
    @Yefkrtarik    @Yefkrtarik

        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄