Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @yefkrtarik
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.01K
የሰርጥ መግለጫ

🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹
➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1
Since 2011 E.C.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-12 23:38:08 ​​በመስታወት እየተመለከተ ሚኪ ይቅር በለኝ ምን ማለት እንዳለብኝ እና እንደሌለብኝ መለየት አልቻልኩም ። ለምን ይሆን ስለምኞት ላንተ ለመንገር አቅም ያጣሁት። ይቅር በለኝ ሚኪ!"
አለ የራሱ ፊት ላይ አፍጥጦ ።ወደ ሚኪ በመመለስ ከሚኪ ጋር ስልክ ተለዋውጦ ከተረጋጋ በኋላ እንደሚደውልለት ነግሮት
ከሆቴሉ በመውጣት ወደ መኪናው ገብቶ ወደ ምኞት በረረ። ከምኞት ጋር አዲስ የተከራዩት ግቢ በር ላይ ሲደርስ ምኞትን
ሲያያት ምን ሊሰማው እንደሚችል ያውቀዋልና ወደ ውስጥ መግባት ፈራ። ለደቂቃዎች አዛው በሀሳብ ሲታመስ ከቆየ በኋላ ከመኪናው ወርዶ ወደ ውስጥ ዘለቀ የተዘጋውን በር በያዘው ቁልፍ ከፍቶ ወደ ቤት ሲገባ ፊልም እያየች የነበረችው ምኞት ብድግ ከማለቷ መሳይ ተንደርድሮ ተጠመጠመባት። ከእቅፉ እንዳትወጣ አጥብቆ እንደያዛት ቆየ ምኞት በሁኔታው ግራ ተጋባች ። በውስጧ በፍቅር አብረን እንሁን ጥያቄው ምላሹ ይቆይ ስላለችው የተረበሸ መስሎ ተሰማት ። እቅፉ ውስጥ እንዳለች እራሱን አዳመጠ። ናርዶስን አሰባት ማድረግ ያለበትን ወሰነ። ውሳኔውን ለመፈፀም ለራሱም ቃል ገባ ለሷ ግን ምንም አላላትም። በንጋታው በጠዋት ከሚኪ ጋር ተገናኝተው ናርዶስ ወዳለችበት
ከአዳስ አበባ 280 ኪሜ በላይ ወደሚርቀው ክፍለ ሀገር በሚቀጥለው ቀን ጥዋት ለመሄድ ቀጠሮ ያዙ።ወደ አንድ የቅርብ ጓደኛው በማምራት ከሚኪ ጋር በተቀጣጠሩበት በተመሳሳይ ሰዓት
ቀጠሮ ያዘ ያን ቀን ቀኑን ሙሉ ምኞትን ሲያጫውታት እና ሲንከባከባት ዋለ።
ማታ ላይ ነገ ጥዋት ከአባቱ ጋር ወደ ክፍለ ሀገረ ለአስፈላጊ ጉዳይ እንደሚሄዱ ነገራትና ተሰነባብተው ወደየ ክፍላቸው ገብተው ተኙ። በጠዋት ሊሄድ ሲነሳ ከሌላኛው ክፍል ድምፅ ሰማ ። ወደ
ማብሰያው ክፍል ሲሄድ ምኞት ቀድማው ተነስታ ቁርስ እያዘጋጀችለት ነበር። እስካሁን የተቆጣጠረውን እንባ ከዚ በላይ ሊገድበው አልቻለም። አነባ.. ምኞት እጅግ በጣም ተረበሸች ። መሳይ ላይ የምታየው ድንገት ስሜታዊ የመሆን ባህሪ ግራ ቢያጋባትም ምን ሆነሀል ብላ አልጠየቀችውም።ቀጣዩን ጥያቄ ፍራቻ።
ከቤት ወጥቶ በሄደ 20 ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ አባቴ ቶሎ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስና እኔ ግን እዛ ለጉዳይ እንደሚቆይ ስለነገረኝ ብቻሽን ከምትሆኚ ብዬ እንዲያመጣሽ ጓደኛዬ ጋር ደውዬለታለው ከደቂቃዎች ቡሀላ አንቺ ጋር ይመጣል ተዘጋጂና ጠብቂው ብሎ በስጦታ መልክ ወደ ሰጣት ሞባይል መልዕክት ላከ።
ምኞት መልክቱን እንዳነበበች ለምን እንደሆነ ባይገባትም ሆዷ ኣካባቢ የፍርሀት ስሜት ተሰማት። ቢሆንም መዘጋጀት ጀመረች ስትጨርስ የክላክስ ድምፅ ሰምታ ስትወጣ የመሳይ ጓደኛ ነበር እነ መሳይ ከሄዱ ከደቂቃዎች በኋላ ናርዶስ ከአባቷ ጋር ተደብቃ እምትኖርበት ቤት ደረሱ በሩን ሲያንኳኩ የከፈተችው. እራሳ ነበረች ስታየው ወደ ጀርባዋ ወደቀች መሳይ እሷ ላይ ተደፍቶ ሲያነባ
ሁሉም በሁኔታቸው ማለቀስ ጀመሩ።
ከቆይታ ቡሀላ መሳይ እየነዳ ናርዶስ አጠገቡ ጋቢና ውስጥ ተቀምጣለች ከኋላ ሚኪ እና ፅናት ተቀምጠው ይዟቸው በመውጣት ከአንድ ጭር ካለ ሰፈር ውስጥ ሲደርስ ከአንድ ግቢ በር
ላይ አቆማት ለምን እዛ አምጥቶ እንዳቆማት ከሱ ውጪ የሚያውቅ የለም። ከነሱ ፊት ለፊት ከሩቅ አንዲት መኪና ወደነሱ እየመጣች ነው። የመሳይ መኪና ጋር ከመድረሷ በፊት ራቅ ብላ ቆመች ። የመሲ ጓደኛ የሚነዳት መኪና ነች ውስጥ ደግሞ ምኞት ብቻዋን
ከውኻላ ተቀምጣለች። የመሳይ ጓደኛ ምኞትን " ያውልሽ የመሳይ መኪና እየሄድሽ ጠብቂኝ መኪናዋን አስተካክዬ ላቁማት።" አላት ለምን መጠጋት
እንዳልፈለገ ግራ እየገባት ለመውረድ ተዘጋጀች። መሳይ ሚኪን " ውረድ !" አለው ሚኪ "ለምን? አለ ። "እሺ በለኝና
በሩን ከፍተህ ውረድ" አለው።
"ወርጄ ምን ልስራ?
"ነው ሚኪ ተወው በቃ አትውረድ ከሰከንዶች በኋላ በሩን ከፍተህ
ሳይሆን ገንጥለህ ካልወረድክ መሳይ ምን አለ በለኝ !" አለው። ሚኪም " ይሄ ሰው ምንድነው ሚለው ናርዶሴ ገላግይኝ እንጂ!" ብሏት ቀና ሲል••• ምኞትን ፊት ለፊት ከቆመው መኪና ውስጥ ወርዳ ስትመጣ ተመለከታት። ያቺ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ጥሏት የሄደው ምኞት ሳትሆን
መጀመሪያ ፌስ ቡክ ላይ ያያት ውበቷ ልብ የሚንደው ምኞት ከላይ እስከታች መሳይ በገዛላት የሚያምር ልብስ ተሽቀርቅራ እነሱ ወዳሉበት መኪና ስትመጣ ተመለከተ። " ፅናቴ እኔ የማየው ላንቺም እየታየሽ ነው ያቺ የምትመጣው እውነት የኔ ምኞት ነች አለ ፍቅር በገደለው ድምፅ መሳይ አንባው
ግጥም አለ። መሪው ላይ ተደፋ።
ሚኪ የመኪናው በር እንዴት እንደሚከፈት ጠፋበት ለመክፈት ይሞክራል ሳይከፍተው መልሶ ይተወውና ምኞትን ይመለከታል ። የሚኪን ሁኔታ መግለፅ ፍቅርን በአካል ምን እንደሚመስል
የማሳየት ያኽል ይከብድ ነበር። መኪና ውስጥ ፈንጅ ጠምደው በሩን ከቆለፉበት ሰውም በላይ የቱን እንደሚይዝ የቱን እንደሚነካ ቤት በኩል እንደሚወጣ ግራ ገብቶት ሲርበተበት ለተመለከተው ሰው ከምንም በላይ የሚንበረከከው ለፍቅር ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል። ምኞት እየቀረበች ነው። በደመነፍስ በሩን ከፍቶ ከመኪናው ወረደ። ቆሞ ሲመለከታት አየችው። አይኖቹ እንባ እንዳዘሉ በፍቅር ፀሀይ በርተው ተመለከተች። በድንጋጤ ባለችበት ቀጥ ብላ ቆመች። ሮጦ በማቀፍ ሽቅብ አንስቷት እንደ እብድ መጮህ ጀመረ።

ከሶስት ወር ቡሀላ••

ለሁለቱ ጥንዶች ባንድ ላይ ድል ያለ ሰርግ ተደገሰ። በዛ ሰርግ ላይ ፅናት እራሷን ስታ ወደቀች ። ለሙሹሮቹ የፅናትን መውደቅ የነገራቸው አልነበረም። ፅናት ከተሻላት ቡሀላ ኢትዬጲያን ለቃ ወደ ሀገረ እንግሊዝ አቀናች። ፅናት በሄደች በሁለተኛው ወር
በመጀመሪያው እሁድ ። ሚኪ ፣ መሳይ፣ ምኞት እና ናርዶስ ወደ አማኑኤል የኧእምሮ ህሙማን

መታከሚያ ሆስፒታል ሰው ለመጠየቅ መጡ። ከሌሎቹ ህሙማን ጋር አልግባባ በማለቱ ለብቻው ተገሎ በአንድ ሰፊ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ ወደ ተፈረደበት አንድ የአይምሮ ህመምተኛ ( እብድ ) ክፍል እንደደረሱ ወደ መስኮት ተጠግተው ወደ ውስጥ ሲመለከቱ•••
ክፍሉ ሰፊና ባዶ ነው። እክፍሉ ግድግዳ ላይ ሁለት ስዕሎች አሉ። አንደኛው ስዕል የሴት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የወንድ ስዕል ነው። ከስዕሎቹ ፊት ህመምተኛው ቆሟል። የወንዱን ስዕል በቡጢና በቴስታ ይመታል ግንባሩና እጁ ተጋግጧል ። የሴቷን ስዕል እየደጋገመ በፍቅር ይስማል። ወንዱን ሚኪ ሴቷን ፅናቴ እያለ
ይጠራ ነበር ። .................ይሄው ሰው ያው ብሩክ ነበር።
.
.
.
.
****ተፈፀመ******"**

#ታሪኩ ይሄን ይመስላል...
አስቲ እንዴት ነበር #ምኞት ትልቅ ትምህር እንዳገኛችሁበት አልጠራጠርም ፡፡ አስቲ ስሜታችሁን እና ስለ #ቻናሉ ያላችሁን አስተያየት @Yefkrtarikbot በዚህ ግለፁልን ስለተከታተላችሁ እናመሠግናለን
10.5K views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 23:35:19 ​​#የመጨረሻ ክፍል#






ድንገት መካከላቸው ወጣ ገባ ስትል የነበረች አንዲት መኪና አቅጣጫ ቀይራ ከመሀላቸው ስትወጣ ሚኪ ዞሮ መኪናዋን የሚያሽከረክረው መሳይ መሆኑን ሲመለከት በድንጋጤ እየጮኽ
ፅናት መንገድ መንገድ ዘግታ እንድታስቆመው አደረገ። መሳይም በሁኔታው እየተደነባበረ ከመኪናው ወርዶ ሮጦ ከመጣው ሚኪ ጋር ተቃቀፈ። ተያይዘው ወደ አንድ ሆቴል በማምራት እንዴት ነገሮች ተቀይረው ለዚህ እንደበቃ እየጠየቀው በመሀል የፅናት ስልክ ጠራ ። ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ተመለከተችው። ፊቷ ተለዋወጠ።
" ይኼ የማያፍር ሰይጣን ደግሞ ስልኬ ይደውላል እንዴ!" ብላ ስልኩን በመዝጋት በንዴት ስትንጨረጨር ከመሳይ ጋር የጀመረውን ጫወታ አቋርጦ•••
hi"ማነው ፅኑዬ?
" ያ ብሩክ ተብየው ነዋ!"
"ተይው አትበሳጪ ስራው ካንቺ በላይ እኔን ማበሳጨት እንደነበረበት አውቃለሁ። ግን ደነዘዝኩ ባንዱ ጉዳት የተሰበረው ልብሽ ሳይጠገን በጉዳት ላይ ጉዳት ሲደራረብብሽ የመበሳጨትም
አቅም ያጥርሽና ትደነዝዣለሽ። እንደ ብሩኬ አይነት ሰዎች ብዙ ናቸው። ሲበዛ እራስ ወዳዴች ከመሆናቸው የተነሳ አንቺ ችግር ውስጥ ስትገቢ ከዛ ችግር እንድትወጪ ከመርዳት ይልቅ
-በችግርሽ
-በእጦትሽ
-በስጋት እና በፍርሀትሽ
ሁሉ ተጠቅመው አንቺን እንዴት አድርገው ለፍላጎትና ለጥቅማቸው መሳካት እንደሚጠቀምቡሽ ነው የሚያስቡት።
ብሩኬም እንደዚሁ ነው ያደረገው። በምኞት ላይ በፈፀምኩት ክህደትና በደል ከባድ ፀፀት ውስጥ መውደቄን በፀፀት ውስጥ ባገረሸው ፍቅሯ መጎዳቴንና የትም አለች ቢሉኝ እሷን ለማግኘት የማልወጣው ተራራ የማልፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ሲረዳ ሰው ቢሆን ኖሮ አጠገቤ ሆኖ ጉዳቴን በተጎዳ። ፍቅሬን ምኞቴን ፀፀቴን እንዳገኛት ከጎኔ ሆኖ በደከመ። ግን እሱ ሰው ቢሆንም
እንደሰው እየኖረ አልነበረምና የኔን መጥፎ አጋጣሚ እራሱን ጠቅሞ እኔን ለመጉዳት ተጠቀመበት አንድ ያለችኝ መፅናኛ እህቴን አንቺን ሊያሳጣኝ ተሯሯጠ። ፈጣሪም ሩጫውን ገታው። ሀሳቡ ሳይሳካ መንገድ ላይ አስቀረው። የኔ ምኞት ግን ጠፍታ አትቀርም!"
አለና እንባ ያቀረሩ አይኖቹን ጨምቆ አቀረቀረ። መሳይ ሚኪ ያወራውን ሲሰማ በተቀመጠበት ልቡ መምታት ያቆመች መሰለው ምድርና ሰማዩ ተገለባበጠበት።
በዛች ቅፅበት ምን እንደሚያወራ ፣ምን እንደሚል፣ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ተሳነው!። ምኞት ታየችው የሚያጣት ሚኪ የሚወስድበት መሰለው። ብድግ ብሎ ወደ ሽንት ቤት ለመሄድ አሰበና ጭንቅላቱ ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት፣ፍጭት እና ጩኸት ገና ከወንበሩ ሲነሳ አዙሮ የሚደፋው መሰለውና መነሳቱን አልደፈረም።
እዛው በተቀመጠበት በሁለት እጆቹ ፊቱን ሸፍኖ እሱም እንደሚኪ አቀረቀረ።
መሀላቸው ቁጭ ያለችው ፅናት ብሩክ ሲደውል የተንቀለቀለው ንዴቷ ጠፍቶ በረዶ ሆነች። የሁለቱንም ስሜት በየተራ እየተመለከተች ነበርና ሚኪ ባውራው
ነገር መሳይ ለእብደት የዳረገውን ያለፈ መጥፎ የፍቅር ሂወቱን አስቦ የተረበሸ መሰላት ። "እባክህ ሚኪ እንደዚህ አትሁን እሱንም ረበሽከው እኮ! እባክህ
ተረጋጋ!" ብላው ደሞ ወደ መሳይ ዞራ "ድንገት አግኝተንህ ማሰብ የማትፈልገውን መጥፎ ትዝታህን ስለቀሰቀስንብህ ይቅርታ እባክህ
አትረበሽ። መሳይ ለፅናት መልስም አልሰጣትም። ቀናም አላለም።
ግራ ሲገባት ወደ ሚኪ ተጠግታ ገና ሚኪዬ ብሏ እንደተጣራች ሚኪ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ድፍት ያለውን መሳይን እየተመለከተ•••
"ከሁሉም ነገር በፊት ትልቅ ይቅርታ እጠይቅሀለሁ መሳይ ወንድሜ! ይቅርታ የምጠይቅህ ግን ዛሬ ስለረበሽኩ ሳይሆን ለቆየ በደሌ ነው። በደሌ ምን እንደሆነና ለምን ይቅር በለኝ እንዳልኩህ ኑዛዜየን ስጨርስ ትረዳዋለህ። "አዋ ዛሬ ትክክለኛው ቀን ነው ከዚህ በፊት ብዙ ግዜ አግኝቼህ ሊሆን ይችላል። ፍቅርህን ናርዶስን ከማጣትህ በፊትም እሷን
አጥተህ ልክ እኔ ዛሬ ቀን እንደጨለመብኝ በቀን ጨለማ ተውጠኽም እንዳገኘሁኽ አስታውሳለሁ። ግን መጎዳትህን አየሁ እንጂ ጉዳትህን አልተጎዳሁትም ነበር።
በፍቅር ህመም ክፉኛ መታመምህን ተመለከትኩ እንጂ ህመምህን አልታመምኩትም ነበር። ካጠገብህ ዘወር ስል እረሳዋለሁ። ያንተ እንደዛ መሆን አይገባኝም፣ አያስጨንቀኝም፣ አይቆረቁረኝም። ዛሬ ግን ሕመምኽን ታምሜዋለሁና ጉዳትህን ተጎድቼዋለሁና ልክ እንዳየሁኽ ስላንተና ስለናርዶስ የማውቀውን ሚስጥር ሳልነግርህ
ማለፍ አልቻልኩም። አቃተኝ። ሚኪ ስለፍቅረኛው ናርዶስ እኔ የማላውቀውን ሚስጥር ይነግረኛል ብሎ አልጠበቀምና ስለምኞት እያሰበ እሱን ከማድመጥ ውጪ ቀናም አላለም።
"መሳይ ወላጅ አባትህ ጓደኛዬ ነው እሱን ይቅር የማለት እና ያለማለት ያንተ ፋንታ ነው ለኔ ግን ሁለቱም ጓደኛቼ አንድ አይነት
ሰይጣኖች ናቸው አባትህ እና ብሩኬ!" አለ። እኼን ግዜ እንኳንስ የመሳይ የፅናት የልብ ትርታ እጥፍ ሆነ ሚኪ ምን ሊያወራ ነው ብላ ሁሉ ነገሯ ስራ ፈትቶ ሚኪ ላይ ተተከለች። መሳይ "ይኼ ሰው ደሞ ምን ሊያሰማኝ ነው ፈጣሪዬ እባክህ የምችልበትን አቅም ስጠኝ። አለ አንገቱን እንደደፋ ፍርሀት ከላይ እስከታች እየናጠው። ሚኪ ቀጠለ••• " አባትህ ከናርዶስ ጋር የነበረኽን የፍቅር ግኑኝነት በጭራሽ አይፈልገውም ነበር።
ይኽን አንተም ታውቀዋለኽ። ናርዶስን ያልፈለጋት ያጠፋችው ወይ ያጎደለችው ነገር ስለነበር አይደለም። ጥፋቷም ጉድለቷም ድሃ መኾኗ : ከድሃ ቤተሰብ መፈጠሯ ብቻ ነበር። በአባትህ አይን ይቺ ያንተ ድሃዋ ናርዶስ እሱ ሊድርህ ለፈለገው ሰው እንዳይድርኽ መዃል የገባች የፍላጎቱ ፀር የእቅዱ ጠንቅ
ነበረች።

ይሄን ግዜ መሳይ ካቀረቀረበት ቀና እለና ሚኪ ላይ አፈጠጠበት ። አይኖቹ ደም ለብሰዋል። ፅናት መሳይን ስትመለከተው ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው እየተፋጩ ነው።
ፈራች መሳይ እብደቱ የጀመረው መሰላት "ሚኪ አብደሃል ምንድን ነው የምታወራው ተነስ በቃ እንሂድ !" አለች ብድግ ብላ ቀና ብሎ እየተመለከታት"የትም አልሄድምም! አላበድኩምም!
ያበድኩት ይሄን እውነት እያወቅኩ ሳልቃወም እውነቱን ደብቄ ለመሳይ እብደት ተባባሪ የሆንኩ እለት ነበር ፅናቴ ። እባክሽ አታቋርጭኝ! "ቀጠለ•••
" እናም ይቺን የእቅዱ ጠንቅ የሆነችውን ናርዶስን በዘበኝነት ተቀጥረው እየሰሩ እንደ እናትም እንደ አባትም ሆነው ባሳደጓት በአባቷ መጣባት። ለአቧታ ያላትን ፍቅር ለመግለፅ ቃላት ለሚያጥሯት ናርዶስ ! አባቷን በሸረበው ተንኮል ወንጀል ውስጥ መግባታቸውን መስማት ከባድ ነበር። አባቷ እስር ቤት ገብተው እንዲማቅቁ የማትፈልግ ከሆነ
አንተን እስከመጨረሻው ትታ እሱ ወደ ሚላት ቦታ ጨርቄን ማቄን ሳትል መሄድ እንዳለባት ሲጠይቃት ምርጫ አልነበራትምና ተስማማች። "
መሳይ በዛን ግዜ የነበረው የአባቱ ሁኔታ በሙሉ ፊቱ ተደቀነበት ከእናቱ ሞት ቡሀላ የህይወቱን መራር ለቅሶ እያለቀሰ " እባክህ ወዴት እንደወሰዳት የት እንዳስቀመጣት ንገረኝ ሚኪ!" ፅናትም ሚኪም አብረውት አነቡ። ሚኪ ብድግ ብሎ ወደ መሳይ በመሄድ "እራስህን አረጋጋ መሳይ ወንድሜ ከዚህ ሰአት ቡኻላ በፈለግከው ሰአት ያንተ ናርዶስ ወዳለችበት ልወስድህ ዝግጁ ነኝ!! አንድ ቀን እንዲህ በአጋጣሚ እኔንም የኔ ምኞት ወዳለችበት ቦታ የሚወስደኝ ሰው ይልክልኝ ይሆናል ፈጣሪ !!" አለው።
መሳይ ውስጡ ያለውን የተደበላለቀ ስሜት መረዳት ከበደው ተነስቶ ሚኪን አቅፎት ለሰከንዶች ቆየና ለቆት ወደ ሆቴሉ መታጠቢያ ቤት አመራ ። መታጠቢያ ቤት ገብቶ እራሱን
8.1K views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 18:20:51 ​​​ ምኞት

ክፍል 49





"ምኞትዬ" ወዬ መስ ምነው ?
"ሚኪ እንደው ምናልባት ባንቺ ላይ ያደረገው ነገር ስተት እንደነበር ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ይቅርታውን ተቀብለሽ ታርቀሽው አብረሽው ትኖሪያለሽ?•••
አይጠይቀኝም! ምክንያቱም ይቅርታ የሚጠይቀውን ስህተትን ተሳስቶ
የፈፀመ ብቻ ነው። ሚኪ ደሞ ለሱ ትክክል የሆነውን ነገር አስቦና ወስኖ ስላደረገ በምን ምክንያት ?ዛሬ ምን ተገኝቶ ይቅርታ ይጠይቀኛል!
መልሷ ያልተዋጠለት መሳይ " ምኞትዬ ሰው በመጀመሪያ ለራሱ ትክክል ነው ስህተት መፈፀሙን የሚያምነው ስህተት እንደነበር መቀበል ሲፈልግ አልያም ስህተት እንደነበር ሲረዳ ነው ። ትናንት
ትክክል መስሎን የሰራነው ወይም የወሰነው ውሳኔ ከቆይታ ቡሀላ ትክክል እንድዳልነበርን ሲገለጥልን ከአንዳንዶቻችን በስተቀር ስተት እንደሰራን ከተረዳንበት ቅፅበት አንስቶ የህሊና እረፍት እናጣለን ስህተቱን ወደ ዃላ ሄደን ማስተካከል ባይሆነልንም በኛ ስህተት የተጎዳ ሰው ካለ ያንን ሰው አግኝተን ይቅርታ እስከምንጠይቀው እንቅልፍ
የማይወስደን ብዙዎች ነን!" አላትና ምላሿን መጠባበቅ ጀመረ•••ብታድያ ዛሬ ላይ ትክክል እንዳልነበረ ገብቶት የሚጠይቀኝ ይቅርታ ትክክል እንዳልነበረ ማመኑን እንጂ ታርቆኝ ከኔ ጋር አብሮ
የመኖር ፍላጎት እንዳለው አያመለክትም እኮ። አየህ መስዬ የጥፋተኝነት ስሜት እና አብሮ የመሆን ፍላጎት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ለዚህ ነው አንዳንድ ፍቅረኛሞች ሀምሳ ግዜ እየተጣሉ ሀምሳ ግዜ ይቅርታ እየተባባሉ የሚታረቁት። ይቅርታ አብዛኛውን ግዜ ያለፈን ስህተት የማመን ጉዳይ እንጂ መጪውን ህይወት ለማቅናት በፍቅር እና በደስታ ተሳስቦ ለመኖር የመወሰን ወይም የመለወጥ ጉዳይን ያካተተ ነው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ይቅርታዎች ስላለፈው ጉዳይ እንጂ ስለመጪው ህይወት የመወሰን አቅማቸው ምንም ነው። ያንን የመወሰን ሙሉ አቅም ያለው
እውነተኛ ፍቅር ብቻ ነው ስለዚህ ሚኪ እኔ ላይ የፈፀመው በደል አላስቀምጥ ሲለው ከህሊና ወቀሳ ለመዳን ይቅርታ ጠየቀኝ ማለት ከኔ ጋር ታርቆ ደስተኛ አርጎኝ ለመኖር የሚያስችል ፍቅር በውስጡ
መኖሩን አረጋገጠልኝ ማለት አይደለም። አለችው። መሳይ ምኞት ለነገሮች ያላት ጠለቅ ያለ ምልከታ ከገመተው በላይ
ሆነበትና ታድያ ምን ብሎ ቢጠይቃት ነው ይቅርታው በፍቅር አብሮ የመኖር ዋስትናንም የሚያካትተው እያለ ሲያሰላስል••• እሱ ዝም በማለቱ ምኞት ግዜ አገኘች። እሷም በተራዋ የመልስ
ምት የሚሆን ሚሳኤል የሆነ ጥያቄ ወደ መሳይ አስወነጨፈች••• ናርዶስ ጥላህ ለመጥፋቷ በቂ ምክንያት ይዛ ዛሬ ብትመጣ ይቅር ብለሀት አብረህ ለመኖር የማሰቢያ ግዜ ያስፈልግኻል?መስዬ?
አለችው•••
በመሳይ በኩል ትንፋሽ ጠፋ። ይኸውልህ መስዬ መልሱን ስለማውቀው አትንገረኝ እስካሁን እየሆነ ያለው ነገር እኔ ወይም
አንተ ቀድመን ያቀድነው ሳይሆን መሆን ያለበት ነው እየሆነ ያለው ስለዚህ መሆን ያለበትን ነገር ለነገ እንተወው። ኑሮ ወይም ህይወትን በእቅድ ለመምራት ይቻል ይሆናል ፍቅርን ግን በእቅድና ቀድሞ በተናገረው መንገድ የመራ ሰው የለም ፍቅር ስሜት ነውና በእቅድ አይመራም ።
እኔ አንተን ከሚኪ ፍቅር መሸሸግያ ላደርግህ አልፈልግም! አንተም የናርዶስን ፍቅር በኔ ውስጥ እንድትደበቀው አልፈልግም። ግን እኮ እኔ እየወደድኩሽ ነው ምኞቴ? አላት እጅግ በሚያሳዝን
ሁኔታ። ግን መቸኮል የለብንማ መስዬ!! ውስጣችን ማለት የኔም ያንተም ልብ ያልደመሰሰው ፍቅር አለ። ግኑኝነታችን የእውነት እንዲሆን አሁን ባለንበት ከነገሮች ነፃ በሆነ እና መተሳሰብ በሞላበት ፍቅራችን ትንሽ እንቆይ ግን መስዬ እንዳትናደድብኝ! ካንተ የተደበቀ ምክንያት ኖሮኝ ሳይሆን ቸኩሎ መጣዱን ፈርቼው ነው እባክህን ግዜ ስጠኝ ! አለችው። ላንቺ ያለኝን ሁሉንም ስሜት አልነግርሽም አንቺ ዝግጁ እስከምትሆኚ ብቻዬን አጣጥመዋለሁ ። እንዳልሽውም አንዱን ስሜት ለመሸሽ ዘለን ገብተን ዘለን የምንወጣበት የወረት ፍቅር እንዲሆን እኔም አልፈልግም። ነገር ግን የኔ ብትሆኝም ባትሆኝም እንደነብሴ ከምወዳት ታናሽ እህቴ ከራሴ አስቀድሜ የማይሽ! ተጎድቼ ባስደስትሽ ቅር የማይለኝ! በስስት እና በናፍቆት የምጠብቅሽ ዳግም ለመኖሬ ምክንያት እንድትሆኚ መርጦ የላከሽ የፈጣሪ ስጦታዬ እንደሆንሽ እወቂ! ብሏት ቀና ሲል የሱ ብቻ ሳይሆኑ የሷም አይኖች በእምባ መሞላታቸውን አስተዋለ ተያዩ እንባ ባጠለሉ አይኖቻችው ዝም ብለው ተያዩ " ግን አሁንም የመጀመሪያው ጥያቄዬ አልተመለሰልኝም አጠር አድርገሽ እንድትመልሽልኝ ጥያቄዬን
አስተካክዬ በድጋሚ እጠይቅሻለሁ••
ሚኪ ካንቺ ጋር በፍቅር ለመኖር ፍላጎት እንዳለው አረጋግጦ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ትቀበይዋለሽ?ምላሽሽ ምን ይሆናል?
መልሼልሀለሁ። አለችው። አልመለሽልኝም ምኞቴ አላት። አቦ ተወኛ አንተ ደረቅ የሆንክ ነገር አለችው። ተሳሳቁ እንባ ካዘሉ አይኖች ስር የፈለቀ ንፁህ የፍቅር ሳቅ። ተነስቶ እንባዋን ጠረገና
ጉንጯን ሳማት ። ተያይዘው ጎን ለጎን ወደያዟቸው ክፍሎች አመሩ። ሁለቱም ቁልፎቻቸውን እበሩ ቀዳዳ ውስጥ አስገብተው በሩን ከመክፈታቸው በፊት ተያዩ ። ደና እደር መስ። አለችው። ደና
እደሪ ምኞቴ አላት ቁልፉን ዘወሩት። በሩን ከፍተው ከመግባታቸውበፊት በድጋሚ "ደና እደሪ መልካም እንቅልፍ አላት። አሜን ብላው ወደ ክፍሏ ገባች።
ትንሽ ቆመና እሱም ወደ ክፍሉ ገባ ።
አንቺ ትችይ ይሆናል እኔ ግን አልችልም ምኞት አለ አልጋው ላይ ተደፍቶ። መሳይ በቀላሉ ፍቅር የሚያጠቃው አይነት ሰው ነው ምኞት በዚች አጭር ግዜ ውስጥ ውስጡ ገብታ ልትነግስ ተደላድላ ለመቀመጥ የሚሆናትን የልቡን ዙፋን ለመቆጣጠር ልቡ ላይ ተሰንቅራ የቆየችውን ናርዶስን ጠራርጋ ለማስወጣት ናርዶስ በመሳይ ልብ ለመንገሷ ፣ ለመፈቀራ ፣ በናርዶስ ለመሸነፉ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙሉ በተሻለ ኹኔታ እየተካቻቸው
መኾኑን ሲረዳ ልቡ ፈራ። " ቸኩሎ መጣዱን ፈርቼው ነው" ያለችው ነገር ደጋግሞ ያቃጭልበታል እኔኮ ተጥጄ በፍቅርሽ መሞቅ ጀምሬአለሁ ምኞቴ !
አለ ጮክ ብሎ ምኞት አጠገቡ የለችምና አልሰማችውም። ምኞትን አዲስ አበባ ይዟት መመለስ ፈራ ወዴት ወስጄ ልደብቅሽ ወዴት ይዤሽ ልሽሽ ምኞቴ ?ይዘሀት ጥፋ ጥፋ አለው ከዛ በፊት ግን ነገውኑ ምኞትን እዛው ሀዋሳ እንድትሆን በማድረግ የሆነ ምክንያት ፈጥሮ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የሚኪን ሁኔታ
ማጣራት ። ሚኪን አጋጣሚ እንዳገኘው መስሎ አግኝቶት ስሜቱን መረዳት ፈለገ ። በዚህ ሁኔታ እዚህ መቆየት አልፈልግም ነገውኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሼ ሚኪን አገኘዋለሁ አለ...

የመጨረሻው ክፍል 500 ላይክ ከሞላ አውን ይለቀቃል
10.4K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 10:34:46 300 ላይክ ከደረሰ ቀጣይ ክፍል ይለቀቃል ውድ ቤተሰቦች ሼር ማረግ ኣይርሱ ለወዳጆቻቹ
11.5K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 10:34:33 ​​​ ምኞት

ክፍል 48






"ተርፏል ብዙ አልተጎዳም መሰለኝ እናውጣው እስቲ በዛ በኩል
ክፈቱት ኑ እባካችሁ እንፍጠን!" አለ ብሩክ መኪና ጋር ቀድሞ
የደረሰው ሰው ከፊት በተጨራመተው መኪናው ውስጥ ፊቱ በደም
የተጨማለቀውን ብሩክን ለማዳን አልከፈት ያለውን በር ለመክፈት
እየታገለ።
"ኧረ ተው እባካችሁ ትራፊክ ሳይመጣ መነካካቱ ጥሩ
አይመስለኝም አለች አንዲት ሴትዬ ወደመኪናው እየተጠጋች ።
አንድ አጠገባ የነበረ ሰው ብሽቅ ብሎ " እኔኮ እማይገባኝ ትራፊክ
እስኪመጣ ውስጥ ያለው ሰው ደሙ ፈሶ ይሙት ነው እምትይው?
ጥፋተኛው እንደሆነ ከውኻላ መጥቶ የገጨው እራሱ እንደሆነ
ይታወቃል! ደሞ ባይታወቅስ አንድ አደጋ ሲደርስ ትራፊክ
እስኪመጣ ፖሊስ እስኪመጣ እያልን ባደጋ የተጎዳው ሰው
እስኪሞት መጠበቁ ተገቢ ነው? ፈጣሪ ምናልባት በኛ ምክንያት
ዳን ብሎት ቢሆንስ የኛ እንቢተኝነት ምን እሚሉት ነው?
ተጠያቂነትን ለመሸሽ በሰው ስቃይና ነብስ መፍረድ ሰው ከሆነ
ፍጡር አይጠበቅም። " እሱስ ልክ ነው አለች ሴትዮዋ የሰውየው
ብስጭት አስደንግጧት።
ብሩክን ከመኪኖው ውስጥ ተጋግዘው አወጡት። ግንባሩ አከባቢ
በፍንጥርጣሪ ከመፈንከቱና ከጉልበቱ በታች መጠነኛ ጉዳት
ከመድረሱ ውጪ ብዙ የሚያሰጋ ጉዳት አልደረሰበትም።
"ፈጣሪ ይመስገን ኧረ ምንም አልተጎዳም ቀበቶ ማሰሩ በጀው!"
አለ ከመሀላቸው አንደኛው። ማን እንደደወለ ባይታወቅም
ከደቂቃዎች ቡኻላ አንድ አንፑላንስ እያቃንጨለች ቦታው ደረሰች
አፋፍሰው አስገቡት አንድ የብሩክን ሞባይል እና የኪስ ዋሌት የያዘ
ግለሰብ አብሮት ወደ ሆስፒታል ሄደ።
ብሩኬ ከሌላ መኪና ጋር በተላተመበት ተመሰሳይ ሰአት ላይ
በሀዋሳ ሁለት ወይን እስከወገባቸው የያዙ ብርጭቆዎች እርስ
በርስ ተላተሙ።
ምኛት እና መሳይ ሀዋሳ ከደረሱ ቡሀላ ስለምንም ጉዳይ ሳያወሩ
መዝናናትና መዝናናት ላይ ብቻ በማተኮር ታስራ እንደተለቀቀች
ጥጃ በሀዋሳ ምድር ሲቦርቁ ሲሽከረከሩ ሲስቁ ሲበሻሸቁ ዋሉ።
ከምሽቱ ሁለት ሰአት አከባቢ አልጋ ወደያዙበት ሄቴል አምርተው
እራት በልተው ከጨረሱ ቡሀላ የብሩኬ መኪና ስትጋጭ እነሱ
ለፍቅራቸው ወይን የተቀዳበት ብርጭቋቸውን አጋጩ።
መሳይ ጎንጨት አለና ውስጡ ሲከነክነው የነበረውን ነገር አነሳ
"የፍቅር ታሪክሽን እንጂ ፍቅረኛሽ ስለነበረው ሰው ማንነት እኮ
አልነገርሽኝም አላት ።
እሄን ርእስ እንደጦር በፍርሀት ስትጠብቀው ነበርና ደነገጠች
ፍርሀቱን የጫሩባት ሁለት ምክንያቶች ነበሯት ።
አንደኛው የርእሱ መነሳት ወደ ነበሩበት ጥሩ ያልሆነ ስሜት
እንዳይከታቸው መፍራቷ ሲሆን ሁለተኛው ስጓቷ ደግሞ ሚኪ
በመጀመሪያው አዲስ አበባ በመጣችበት ቀን በቤቱ መታደስ
ሰበብ ወደዛ ኮንዶሚንየም ሲያመጣት ኮንዶሚንየሙን የተከራዩት
እሱና ሌሎች ጓደኛቹ በጋራ ሆነው እንደነበር ነግሯታል ። መሳይን
ወደዛ ኮንደሚንየም ያመጣው ደሞ አባቱ ነው። አባትየው
ከተከራዮቹ አንድ ከሆነ ደሞ ከሚኪ ጋር ይተዋወቃሉ ማለት ነው ።
የመሳይ አባትና ሚኪ ከተዋወቁ ደግሞ መሳይ ሚኪን ሊያውቀው
ይችላል እኼንን ስታስብ ለምን እንደሆነ ለራሳም ባይገባትም እዛ
ኮንደሚንየም ውስጥ አምጥቶ የጣላት ፍቅረኛዋ ሚኪ መሆኑን
ለመሳይ መናገሩ አስፈራት። ግን እስከመቼ?
ትንሽ ተቁነጠነጠችና እሄውልህ መስዬ•••
አሁን ለግዜው አንተም ከናርዶስ አለም እኔም የኔ ከነበረው ሰው
አለም ወጥተን በራሳችን አለም ውስጥ የምናሳልፍበት ግዜ ቢሆን
አይሻልም መስዬ እስከመጨረሻው ባንድ ግዜ አውጥተን መጣል
ባንችልም እስቲ ትንሽ ግዜ አንተን ለአመት እኔን ለወራት
ሲያስጨንቁን የነበሩትን ሀሳቦች ፊት እንንሳቸው!? አለችው
" ግድ የለሽም ምኛትዬ በሙሉ ልብ ወደራሳችን አለም ለመግባት
መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ስላሉ ነው ቀለል አርጊው እና
ንገሪኝ እባክሽ ?"አላት።
አቦ ያበጠው ይፈንዳ ምን አስጨነቀኝሳ አለች በውስጧ ወድያው
ሚኪ •••ማለት ሚክያስ ይባላል ።ለብዙ አመት ከሀገር ውጪ
ቆይቶ በቅርብ ግዜ ነው ወደ የመጣው ስትለው •••
መሳይ አፉን ተሻግሮ ጉሮሮው ላይ ደርሶ የነበረው ወይን ትን
ብሎት ሊወጣ ሲል እንደምንም አከሸፈው ።
ደነገጠ ሚኪን በደንብ ያውቀዋል ከአባቱ ጋር በእድሜ
የማይደራረሱ ሚኪ ገና በጎልማሳዎቹ እድሜ ውስጥ ያለ ሰው
ቢሆንም ከአባትየው ጋር ጓደኛ ነው እቤታቸው ብዙ ግዜ ይመጣል
ከሱም ጋር በጣም ይግባባሉ ።
ምን እንዳስደነገጠው አሰበ እቺን ልጅ እየወደድኳት ነው መሰለኝ
ፈጣሪዬ ባክህ ዳግም ለጉዳት አታጋልጠኝ አለ በውስጡ።
ዝምታው ያስፈራት ምኛት ምነው ዝም አልክ መስ ታውቀዋለህ
እንዴ? አለችው
"ኧረ በጭራሽ አላውቀውም ያስጨነኩሽ መሎኝ ነው ዝም ያልኩት
ብሎ መልሶ ፀጥ አለ።
ዝምታ በመሀላቸው ሰፈነ ተያዩ መሳይ ከዝምታው መሀል ድንገት
ያልታሰበ እና ቦንብ የሆነ ጥያቄ አስወነጨፈ።
"ምኛትዬ" ወዬ መስ ምነው ?
" ሚኪ እንደው ምናልባት ባንቺ ላይ ያደረገው ነገር ስተት
እንደነበር ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ይቅርታውን ተቀብለሽ
ታርቀሽው አብረሽው ትኖሪያለሽ...

ይቀጥላል..



11.0K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 19:12:02 ​​​ ምኞት ክፍል 47

ሚኪ ከአዳማ እንደመጣ ወደ ቤቱ ሳይገባ ቀጥታ ወደ መጠጥ ቤት ስልኩን አጥፍቶ ሲጠጣ አመሸ ። ከምሽቱ ሶስት ስአት አከባቢ ሞቅ እንዳለው ስልኩን አውጥቶ በመክፈት ፅናት ላይ ደወለ። በብሩክ አማካሪበት በቀየረው አዲሱ ሲም ካርድ ነበርና የደወለው ፅናት አላነሳችውም። "እባክሽ አንሺው ፅናቴ ዛሬ ታስፈልጊኛለሽ እኔ ያንቺው ወንድም…
10.9K views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 20:12:53 ​​​ ምኞት

ክፍል 47





ሚኪ ከአዳማ እንደመጣ ወደ ቤቱ ሳይገባ ቀጥታ ወደ መጠጥ ቤት ስልኩን አጥፍቶ ሲጠጣ አመሸ ። ከምሽቱ ሶስት ስአት አከባቢ ሞቅ እንዳለው ስልኩን አውጥቶ በመክፈት ፅናት ላይ ደወለ።
በብሩክ አማካሪበት በቀየረው አዲሱ ሲም ካርድ ነበርና የደወለው ፅናት አላነሳችውም። "እባክሽ አንሺው ፅናቴ ዛሬ ታስፈልጊኛለሽ እኔ ያንቺው ወንድም
ሚኪ ፅናቴ እህቴ ከጎኔ ሆና አይዞህ እንድትለኝ እሻለሁ ከፍቶኛል ፅናቴ ከፍቶኛል! አለም በሙሉ የጠላኝ ይመስለኛል? ቢሆንም አንቺ ምንም ጥሩ ባልሆን እንደማትጨክኝብኝ አውቃለሁ።" ብሎ መልክት ላከላት። ፅናት መልክቱን አንብባ መልሳ ለመደወል ሰከንዶች ብቻ ነበሩ ያስፈለጓት።
"ሚኪዬ በህይወት አለህ ግን ቆይ ምን አድርጌህ ነው ይሄን ያክል ቀን ስልክህን አጥፍተህ የጠፋኽብኝ••• አንቺ ደሞ ምን ታጠፊያለሽ ህይወቴ በሙሉ በጥፋት እና በፀፀት የታጠርኩት እኔ ምንም አላጠፋሽም ፅናቴ ግን ልክ ነሽ ጠፍቻለሁ በዚህ ሰአት እንኳን አንቺን ለምን እንደጠፋሁ አስረድቼ የማሳምንበት የተፈጠረውን ነገር አምኜ መቀበል ያቃተኝ ደካማ ሰው ሆኛለሁና ጥዬቄሽ ሳይሆን ድጋፍሽ ብቻ ነው የሚያስፈልገኝ ፅኑዬ ባንቺ ውስጥ የድሮውን ሚኪ ማየት እፈልጋለሁ ሚኪ
ጠፍቶብኛል ፅናቴ! ሚኪን አጥቼዋለሁ። ቅጣቴ በዛና የድሮውን ደስተኛ እና ሳቂታዉን ሚኪ አጥፍቶ ሌላ ሰው አደረገኝ ። ይሄንን ሚኪ አላውቀውም ፅናት እህቴ እባክሽ ወደራሴ እንድመለስ
እርጅኝ•••" እሺ ሚኪዬ እባክህ ከዚህ በላይ ያንተን ጉዳት የመስማት አቅሙም
የለኝም አሁኑኑ እመጣለሁ የት እንዳለህ ንገረኝ!" ሚኪ እና ፅናት ሲያወሩ ጆሮዋን ደቅና ስታዳምጥ የነበረችው ሰራተኛ ስልኳን ወዳስቀመጠችበት ክፍሏ ተንደረደረች። እነፅናት ቤት ውስጥ ካሉት ሶስት ቋሚ ሰራተኛች መሀል አንዷ
ስትሆን ብርኬ አጥምዶ በመተዋወቅ በገንዘብ ሀይል የፅኑን እንቅስቃሴ እየተከታተለች መረጃ እንድታቀብለው በገዛ ቤታቸው ቃል አቀባይ አድርጎ የሾማት ተባባሪው ነች። ስልኳን አንስታ ደወለች ። የብርኬ ስልክ በሚጠጣበት ግሮሰሪ ውስጥ ስታቃጭል ድምጿን ግሮሰሪው ውስጥ የተለቀቀው ሙዚቃ
ቢውጠውም ብርሃኗን አይቶ አነሳት •••
"ሄሎ አዲስ ነገር አለ እንዴ? በደንብ እንጂ ልትወጣ እየለባበሰችልህ ነው!
ወዴት እንደምትሄድ አጣርተሻል?
ወደ ሚኪ! ሚኪ! መጣ እንዴ ?ብሎ ጮኸና ብርጭቆው ውስጥ ያለውን
ውስኪ ጨለጠው። በምንድን ነው የምትሄደው ግቢ ውስጥ መኪናዋ አለ እንዴ? ምናልባት የጋሽዬን ይዛ ከወጣች እንጂ የሷን ወንድሟ የሱ ገራዥ ስለገባች ይዞባት ወጥቷል።አለችው ቃል አቀባይ የሆነችው የፅናት የቤት ሰራተኛ።
" በይ አሁኑኑ ከቻልሽ የመኪናውን ጎማ አተንፍሺው ካልሆነ•••ብቻ እሷ ቶሎ እንዳትወጣ የሆነ ነገር አድርጊ ብሎ መልሼ ደውላለሁ ከስልክሽ እንዳትርቂ ብሎ ስልኩን በመዝጋት እንዴት ሳይነግረኝ መጣ ብሎ እየተብከነከነ ወደ ሚኪ ደወለ።ሚኪ ስልኩ ሲጠራ ገና
እንደተመለከተው••• "አቦ ወደዛ ተፋታኝ አንተ ምክረ ደረቅ የሆንክ ሰውዬ እስካሁን ባንተ ምክር ሄጄ የቀናኝ ነገር የለም! አሁን ለምን እንዲህ አታረግም? እንዲህ ማድረግ እኮ አልነበረብህም እያለ ቁስሌን የሚያመረቅዝ ሳይሆን ቁስሌን የሚያክም የሚያድን ሱው ነው ማግኘት የምፈልገው ወደ እራሴ እስክመለስ ተወኝ አትደውልብኝ !"
አለ ስልኩን ሳያነሳው በብስጭት እጁን እያወናጨፈ ። ብሩኬ ሚኪ ስልኩን ባለማንሳት በገነ! ተቁነጠነጠ። ወደ ፅናት
ስልክ ደወለ ። እሷም አታነሳም። በንዴት እየተወናጨፈ ግሮሰሪው አካባቢ ወዳቆማት መኪናው ገባ። ትንሽ እንደሄደ ወደ ሰራተኛዋ ደወለ••• አነሳች። 'ወጣች እንዴ? ኧረ አልወጣችም። እንዴት እስካሁን ለባብሳ አልጨረሰችም ወይስ እንዳልኩሽ ጎማውን አስተነፈሽላት። እእእ ጋሽዬ ሲገቡ የመኪናውን ቁልፍ የት እንዳስቀመጡት አይቼ ስለነበር አንስቼ የወደቀ እንዲመስል ወደ አንድ ጥግ
አሽቀነጠርኩላት። ይኸው ቤት ውስጥ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች እየተመነቃቀረች በመፈልግ ላይ ነች።
አይ አንቺ ስማርት (smart) እኮ ነሽ ። በቃ ቀረብ ስል ሚስኮል አረግልሻለሁ ያኔ ቁልፉን አገኘሁልሽ ብለሽ ትሰጫታለሽ ሌላው ደግሞ ባለፈው የተነጋገርነውን እቅድ ሁለትን ነገ እንጀምራለን ምን
ማረግ እንዳለብሽ የነገርኩሽን አረሳሽውም አደል?
አረሳሁትም።
እስቲ ንገሪኝ?
እንዴ የሱ ምኞት የላከችለት ደብዳቤ ላይ ሊያገኛት የሚችልበትን ስልክ አስቀምጣ እንደነበር ብሩኬ ስለማይመቸው ደብዳቤውን ላንተ እንድትሰጥህ ለፅናት ሲሰጣት ስልኩ የተፃፈበትን ሌላኛውን ገፅ በማውጣት አጣሁት እራስህ ስጠው ብላ ለብሩኬ እንደምትመልስለት ከወንድሟ ስትማከር መስማቴን ። ከዛ ምኞት ጋር ደውለው ስራ እናስገባሽ ብለው በወንድሟ ሀሳብ አመንጪነት
ፅናትና እና ወንድሟ አንድ ክፍል ውስጥ አግተው እንዳስቀመጧት ምግብ የማደርስላት እኔ እንደሆንኩና ታሪኳን ስታጫውተኝ አሳዝናኝ ለሱ እንደደወልኩለት የዚህ ሴራ ዋና ተግባሪ የፅናት ወንድም እንደሆነ ከነገርከኝ ታሪክ እያጣቀስኩ እግተዋለው" በቃ የኔ ቆንጆ ነብሴን አስደሰትሻት በቃ አሁን ትንሽ ቆይቼ ሚስኮል ሳረግ ቁልፉን ስጫት።ካካካካ። ቻው ቻው።" እነፅናት ሰፈር ደርሶ የመኪናውን መብራት አጠፋፍቶ አንድ ጥግ አቆመና ለሰራተኛዋ ሚስ ኮል አደረገላት።
ወድያው ቀልፉን አገኘሁት ብላ ስትሰጣት ከእጇ ላይ መንትፋ ሮጠች ። በሰከንዶች ውስጥ የነፅናት የውጪ በር ወደ ጎን
ተንሸራቶ ተበረገደ። የአባቷን ቪ ስምንት(V-8) መኪና ከግቢ ይዛ
በመውጣት ቁልቁል ተፈተለከች።
ብሩኬ የያዛትን ቪትስ(vitz) አስነስቶ የፅኑን መኪና እንድትከተል ሲያስጨንቃት ሳቋ መጣባት ሲበዛባት ተናደደች የምታወጣው ድምፅ ያቅሜን እየሄድኩ ነው እንግዲህ ከዚህ በላይ ልፈንዳልህ
እንዴ? የሚል መልክት ያዘለ ይመስላል።
በቅርብ ርቀት እንዳይከተላት በመሀል እየገቡ እንቅፋት የሚሆኑበትን እየተሳደበ እሱም እየተሰደበ ስቴድየም አከባቢ
ሲደርሱ በሱና በፅናት መኪና መካከል ከአራት ያላነሱ መኪናዎች አሉ።
ቀና ብሎ ከፊት ለፊቱ ያለውን የትራፊክ መብራት ደቂቃ ሲመለከተው ቆሌው ተገፈፈ። የትራፊክ መብራቱ ፅናትን ካሳለፈ ቡኻላ እሱን ካስቆመው ፅናት ልታመልጠው ነው። ያ ከሆነ ደግሞ
ምን ያኽል እንደሚበሳጭና ምን አይነት አዳር እንደሚያድር ያውቀዋል። አይሆንም•••ይሄንም እያለ እየቶሽለከለከ ከአቅማ በላይ ጋለባት ፅኑ የትራፊክ መብራቱን አለፈች ። ከፅኑ ጀርባ ያለው ሌላኛው መኪና እንዳለፈ ደቂቃው አበቃ። ቀዩ መብራት ቦግ አለ። ከብሩክ ፊት የነበረው መኪና ለማለፍ ከነበረው ፍጥነት ባንዴ ሲጢጢጢ አርጎ ፍሬን በመያዝ ቀጥ አለ። ብሩኬ ከዋላ መጥቶ ተላተመ። በአከባቢው የነበሩ እግረኞች እየጮሁ ወደ ብሩኬ መኪና ተሯሯጡ። ከጀርባዋ ምን እንደተፈጠረ ያላወቀችው ፅናት ለሚኪ ለመድረስ ከአከባቢው ተሰወረች..........

ይቀጥላል....



12.0K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 22:02:47 የኔ አለም አለሜን የማይብክ ደስታየ ሀዘን ማስረሻየ ይችን ቀን በ ጉጉት ስጠብቃት ነበር ከዛ አረም ከበዛበት ህይወት ነቅለህ ልብህ ላይ ያተከልከኝ ያለማንም ግፊት አንተን ተደግፌ የቆምኩባት እለት የኔ ህይወት እንኳን አደረሰን ከዚህም በኋላ ብዙ anniversaryወችን እንድናሳልፋ ፈጣሪ ይርዳን አፈቅርሃለው ስጦታየ
2/9/14 . M&M
።።።።።።።።።።።።።።from Meri
......... . ................. to mule
11.8K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 22:02:47 የፍቅረኛሞቹ ሰአት
10.6K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 22:20:39 እስከ ነገ ማታ 300 ላይክ ከደረሰ ቀጣይ ክፍል ይለቀቃል ውድ ቤተሰቦች ሼር ማረግ ኣይርሱ ለወዳጆቻቹ
10.9K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ