Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidu_kidu — ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች
የሰርጥ አድራሻ: @kidu_kidu
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.93K
የሰርጥ መግለጫ

ጣፋጭ ግጥሞችን ይፈልጋሉ
ልብን የሚማርክ ደብዳቤዎችስ ማድመጥ ከፈለጉ ይቀላቀሉን
@kidu_kidu.......https://t.me/ -me8FzuCO5NmZmI0
የፍቅር ፣ የትዝታ ፣ የይቅርታ ደብዳቤዎችን ከማያልቀው ማዕዳችን ገብተው ይመገቡ፡፡
Connect Admin @Who12

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-06-18 09:11:03 .......ወንድሜ ነው........
እንዴት ነሽ ብሎ ስለደወለልኝ?
ከራሱ አስበልጦ ስለ አሰበልኝ?
እሱ ምናጠፍ??
ከልቡ ወዶኛል ይጨነቅልኛል
ስናፍቀው ጊዜም ይደውልልኛል
ለራሱሳይሆን ስለኔ ይኖራል
እኮ ምናጠፋ?
ምንም አላጠፍም ወንድሜ ነው እሱ
እውነት ወዶኛል እስኪወጣ ነብሱ
ክፉ ቃል አይወጣም ማር ነው ምላሱ
አዎ ወንድሜ ነው!
ጊዜውን ሰውቶ ለኔ ሰቶኛል
ስለ አፈቀርኩት እሱም አፍቅሮኛል
ወንድሜ አይደለ? ይሞትልኛል
ከአንድ ወር በኋላ ሚስቱ ያረገኛል



3.2K viewsDJ BOSS , 06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 09:09:57 ህይወት ካለ ጉድለት አልተሰራችም። ስለዚህ ሁሉም ጉድለቱን ይዞ ይጉዋዛል የእፎይታን አፈር እስኪቀምስ ያዝግማል።ፍንጭትህ በምን ትደፍነዋለህ ባለመሳቅ ብትል የተጨማደደ ግንባር ታተርፍለህ። የድድህ መጥቆር የጥርስህን ንጣት አይሸፍነውም ውበት ይሆንለታል እንጂ እነኚህ በክፍተትና በጥቁረት የተሞሉ ጌጦች ለፈገግታችን ድምቀት ናቸው። እናም እናዝግማለን እህህ ማለት አይበጅምና በጉድለት መኳል እንመርጣለን ። መከፍታችን ለእግዜር ና ለኛ የድልድይ መንገድ ነው። ምንድነው ችግርህ ? የምንልበት
ምን አጠፍው ብለህ የምታዋይበት ፣ሙላልልኝ ብለን የምንጨቀጭቅበት፣ እግዜርነቱን የምናምንበት ፣ዝቅታችንን የምናውቅበት ነው። ያ ባይሆንማ አዳም እፀበለስን አትብላ ባልተባለ ነበር ባይጎድልበት ዝቅታውን እንዴት ያውቅ ነበር? ሲፈጥረን አጉድሎብናል የሰጠን ግን ከሁሉ ይበልጣል ።ይሄን አምኖ ምስጋናውን የማይነሳ በእውነት እሱ ብፁህ ነው።

ፍቅር ያሸንፋል
3.1K viewsDJ BOSS , 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 22:09:32 ከሌላ እንዳትቆጥር

ይሀዉልህ ዉዴ
ትላንትና ማታ

እንባዬን አፍስሼ
አፈር ትቢያ ልሼ
ከእግርህ ወድቄ ማረኝ ተዉ ማለቴ
ታቦት እየጠራዉ መማል መገዘቴ

ከሌላ እንዳትቆጥር

ደግሞም ታቦታቱን ጠርቼ ጠርቼ
አንተም ዝም ብትል
የሞተች እናትህን መቃብር አዉጥቼ
በሷ ሞት እያልኩኝ ያኔ መለመኔን
አንተንም እያስማልኩ.......
ቅዱሱን መፅሐፍ በእጆችህ አስይዤ
አልተውሽም ስትል በደስታ ፈንጥዤ

ያኔ መጨፈሬን

ከሌላ እንዳትቆጥር

ከወትሮዉ በሌላ
ካልለመድከዉ ገላ
እራሴን ሰጥቼ ደባብሰኝ ማለቴን
ሳመኝ እቅፍ አርገኝ ብዬ መማፀኔን
ላለፈ ስህተቴ
ከእቅፍህ ገብቼ ንስሀ መግባቴን

ከሌላ እንዳትቆጥር

አንተን ከረሳሁኝ
ባንተ ከማገጥኩኝ
ሳት ብላኝ ነብሴ
ሌላዉን ከሻተች ሞት ይሁነኝ ዋሴ።

ስቅበዘበዝ ልሙት ልክ እንደ ይሁዳ
የሄድኩበት እግሬ ይቅር ምድረ በዳ።

ነፍሴንም አይማረዉ
እግዜሩም ይጣላኝ
እኔ አንተን ከረሳዉ
ያቀፍኩበት እጄን ለምጥ እከክ ይዉረሰዉ
ብዬ መገዘቴን
በራሴ ጨክኜ ርግማን ማዝነቤን

አደራ እንዳትቆጥረዉ
እባክህ በሌላ
ሰክሬ ነዉ እንጂ
ባሌ ትዝ ብሎኝ
ለደቂቃም እንኳን እንዲያዉ ለቅፅበቱ
አንተ የኔ እንድትሆን አልሻም በእዉነቱ።
..........................
..........................
..........................
..........................
አንተን እንደ ንፁህ ወንድሜ ነዉ የማይህ አላለችም

ፍቅር ያሸንፋል
4.3K viewsDJ BOSS , 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ