Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidu_kidu — ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች
የሰርጥ አድራሻ: @kidu_kidu
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.93K
የሰርጥ መግለጫ

ጣፋጭ ግጥሞችን ይፈልጋሉ
ልብን የሚማርክ ደብዳቤዎችስ ማድመጥ ከፈለጉ ይቀላቀሉን
@kidu_kidu.......https://t.me/ -me8FzuCO5NmZmI0
የፍቅር ፣ የትዝታ ፣ የይቅርታ ደብዳቤዎችን ከማያልቀው ማዕዳችን ገብተው ይመገቡ፡፡
Connect Admin @Who12

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-23 09:15:13 ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!


ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።


እስክስ ቅዳሜ! !!!!!!


ከሰኞ እስከ አርብ ፤
ባለቃ በምንዝር ፣ ታምሜ ተምሜ ፤
የምታከምብሽ ፤
የቀኑ ባለሟል፤ እንዴት ነሽ ቅዳሜ! !!!!!!

((Kida))



ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!


ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ...ወርቆቼ!!!!!!
ፍቅር ያሸንፋል
3.3K viewsDJ BOSS , 06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 09:07:11 እንተሳሰብ !!!

"እንቁላሉ ስንት ስንት ነው?" ስትል ጠየቀቻቸው…
"አንዱ እንቁላል 4 ብር ነው " ልጄ በማለት መለሱ፣ እማማ…
"አምስቱን እንቁላል በ10 ብር ልወሰደው?…" ስትል ደግማ
ጠየቀቻቸው …
"አይጎዳኝም ብለሽ ነው ልጄ?"…በማለት ደከም ባለ ድምፅ
መለሱላት…
"ከፈለጉ ይሽጡ፣ ካልፈለጉ ግን በቃ መሄዴ ነው…" አለች፣
ጠንከር ባለ ድምፅ…
እማማ ትንሽ አሰቡና ቀና ብለው አይተዋት…
"እስካሁን ምንም አልሸጥኩም፣ ባያዋጣኝም እንደ መጀመሪያ
ገድ ልቁጠረውና ልሽጥልሽ፣ የፈለግሺውን ያህል እንቁላል
በፈለግሺው ዋጋ ውሰጂ…" ሲሉ በደከመ ድምፅ ተናገሩ…
ዘንቢሏን አውጥታ 5 እንቁላል መርጣ አስገባች፣ ከበርካታ
100 ብሮች መካከል ነጠላ 10 ብር አውጥታ ወርውራላቸው
እየተጣደፈች የሚያምረው ዘመናዊ መኪናዋ ውስጥ ገባች…
የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷታል…

ከጓደኛዋ ጋር ወደ አንድ ዘመናዊ ሬስቶራንት ገብተው
የሚፈልጉትን አዘዙ…ትንሽ በልተው ብዙ አተረፉ። ተዝናኑ።
ሂሳቡ ሲመጣ ቢሉ ላይ 1420 ብር ይላል ። ከቦርሳዋ ውስጥ
1500 ብር አውጥታ ሰጠች ። መልሱን ለሪስቶራንቱ ባለቤት
ቲፕ እንዲሆነው ነግራው ወጥተው ሄዱ…

ይህ ድርጊት ለሬስቶራንቱ ባለቤት አዲስ አይደለም፣
ለእንቁላል ሻጮ ግን አስደንጋጭና ልብ ሰባሪ ነው…
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
※ከድሆችና ከምስኪኖች የምንፈልገውን ለማገኘት
የበላይነታችንን ለማሳየት የምንጥረው ለምንድን ነው? የእኛን
እርዳታ ለማይፈልጉትስ ቸር ሆነን ለመታየት ለምን
እንፈልጋለን?
.
ለሚገባው እንስጥ

ፍቅር ያሸንፋል
3.0K viewsDJ BOSS , edited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 06:01:43 Channel photo updated
03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 21:53:03 ዛሬም እወድሻለሁ
3.0K viewsDJ BOSS , edited  18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 21:14:49 አሁኑኑ አቁም

★ ነፍስህን መዋሸት አቁም

★ ከችግርህ መሸሽ አቁም

★ ትምህርት ከማትወስድባቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ማጥፋትን አቁም


★ እሳሳታለው በሚል ጥሩ ስራ ከመስራት መቆጠብን አቁም ስላለፈው ጊዜ በመጨነቅ ያለህበትን ጊዜ ማበላሸት አቁም

★ውስጣዊ ደስታን በቁሳዊ ነገሮች ለመገዛት መሞከርን አቁም እኔ ውስጣዊ ደስታ ማግኘት አልችልም ብሎ ማሰብን አቁም

★ከችግርህ በላይ ሌላ ችግር እንዳትፈጥር በችግርህ ላይ ከመጠን በላይ ማሰብን

አቁም

ሁልጊዜ ለሰዎች ስሞታ ማሰማትን አቁም

ወደ ምቅኝነት እንዳይቀይር ከሰዎች ላይ ባለ ነገር ሁሉ መቅናትን አቁም

በፈፀምከው ስህተት ምክንያት ሌሎችን. መውቀስን አቁም

ከምታደረገው ነገር ላይ ከሰዎች ምስጋና መጠበቅን አቁም

በአንተና በሌሎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ይቅርታን ከሌሎች መጠበቅን አቁም እርግጠኛ የሆንክበትን ነገር ትተህ የሚያጠራጥርህን ነገር መስራትን አቁም።

ፍቅር ያሸንፋል
3.0K viewsDJ BOSS , 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 21:09:49
2.7K viewsDJ BOSS , 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:25:31 #የፍቅር_ደብዳቤዎች


“የዓለማችን ምርጥ የፍቅር ታሪኮች ” ከተሰኘው
መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
“ፍቅር ዕብደት” የተሰኘው ታሪክ እነሆ…
ድሮ ድሮ ነው አሉ….ያኔ በጥንት ዘመን፡፡ ገና አለም ሳይፈጠር
ሰው የሚሉት ፍጥረት ሳይኖር! እግዚአብሄር የሰው ልጅ
ባህሪያት የሚባሉትን ሁሉ ባንድ የተወሰነ ቦታ ከልሎ
አስቀምጧቸው ነበር፡፡
ለረጅም ጊዜ በአንድ ቦታ ተከርችመው መቀመጥ የሰለቻቸው
ባህሪያት ድብርቱን ለመግፈፍ ጨዋታ አመጡ፡፡ ድብብቆሽ
ሊጫወቱ ተነሱ፡፡ ከባህሪያቶቹ መካከል ድንገት እብደት ተብዬው
ተነሳና እኔ እቆጥራለሁ እናንተ ተደበቁ አለ፡፡ ወዲያው ነው
ሁሉም የተስማማው፡፡ አዎና…ማን ሞኝ አለ እብደትን ተደበቅ
ብሎ እሱን የሚፈልግ፡፡ ከዚያ በኃላ እንግዲህ እብደት ፊቱን
አዙሮ መቁጠር ጀመረ፡፡
አንድ…ሁለት…ሦስት፣ ይሄኔ ባህሪያቱ ለመደበቅ ይጣደû
ጀመር፡፡ ሁሉም በአገኘው ስርቻ ተሸጎጠ ….ለምሳሌ ያህል
ውሸት ድንጋይ ስር እደበቃለሁ ብሎ ለፍፎ ሲያበቃ ሀይቁ ውስጥ
ገብቶ ተደበቀ፡፡ እብደት መቁጠሩን ቀጥሏል….ሰባ ዘጠኝ፣
ሰማኒያ ፣ሰማኒያ አንድ….ይሄኔ ከፍቅር በስተቀር ሁሉም
ባህሪያቶች በየስርቻው ተደብቀዋል፡፡ ጅሉ ፍቅር ብቻ ሳይደበቅ
ተንከርፍፎ ቀረ፡፡ ለነገሩ ይሄ አይደንቀንም፡፡ የፍቅር ባህሪው
ይኸውም አይደል፡፡ ፍቅርን መደበቅ ምን ያህል አስቸጋሪ
እንደሆነ አይጠፋንም! ለማንኛውም እብደት መቁጠሩን
ቀጥሏል፡፡ ዘጠና አምስት፣ ዘጠና ስድስት፣ ዘጠና ሰባት….እያለ
ነው፡፡
እብደት ልክ መቶ ላይ ሲደርስ ፍቅር ዘልሎ የፅጌረዳ
ቁጥቋጦው ውስጥ ገብቶ ተደበቀ፡፡ እብደት መቁጠሩን ጨርሶ
መጣሁላቸሁ እያለ መôህ ጀመረ፡፡ መጀመሪያ የተያዘው ስንፍና
ነው፡፡ ዳተኛው ስንፍና ለመደበቅ ካለበት ቦታ ብዙም ሳይርቅ
ተያዘ፡፡ እብደት ባለ በሌለ ሀይሉ በርብሮ ከሀይቁ ጥልቀት
ውስጥ ውሸትን ፈልፍሎ አወጣ፡፡ እብደት አንድ በአንድ ሁሉንም
ባህሪያቶች መንጥሮ ሲያወጣ አንድ ባህሪ ግን እንደተደበቀ
ቀረ፡፡ ፍቅር፡፡ እብደት ፍቅርን ፈልጎ ሊያገኘው ባለመቻሉ ተስፋ
ወደ መቁረጥ አዘንብሎ ነበር፡፡
በስተመጨረሻ ግን በፍቅር ላይ ቅናት ያደረበት ባህሪ ወደ
እብደት ጠጋ ብሎ ፍቅር የተደበቀው በፅጌረዳ ቁጥቋጦው
ውሰጥ ነው ሲል አንሾካሾከለት፡፡ ይሄኔ እብደት ዘሎ የፅጌረዳው
ቁጥቋጦ ውስጥ ሲገባ ፍቅር ከቁጥቋጦው ውስጥ ታላቅ
ጩኸት አሰማ፡፡ የፅጌረዳው እሾህ የፍቅርን አይኖች ደንቁለው
አጥፍተውታል፡፡ እንግዲህ ከዚህ በኃላ ፍቅር እውር ሆነ፡፡
የፍቅርን የስቃይ ጩኸት ሰምቶ የመጣው ፈጣሪ ባየው ነገር
አዘነ እናም እብደትን ፈጣሪ እንዲህ አለው…. ‘ፍቅር እውር
የሆነው ባንተ ሰበብ ነው፡፡
በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ፍቅርን የገባበት ቦታ እየተከታተልክ
የምትመራው አንተ ትሆናለህ፡፡ መቼም ቢሆን አብራችሁ
ትሆናላችሁ፡፡ እናም አንተ መንገድ ታሳየዋለህ፡፡ ...እንግዲህ
ከዚህን ጊዜ ጀምሮ እውሩ ፍቅር በእብደት እየተመራ ያላሰሰው
የምድር ክፍል ያልጎበኘው ጎጆ የለም፡፡ ከዚያን ዘመን አንስቶ
የዕውሩ ፍቅር ክንፍ ምንግዴው እብደት ሆነ፡፡
እናም ከዚያን ጊዜ አንስቶ የንጉሱን ቤተ መንግስት ከደሳሰው
ጎጆ ፣የሩህሩሁን ልብ ከጨካኙ፣ ቸሩን ከንûጉ፣ ምሁሩን
ከመሃይም፣ ደፋሩን ከፈሪ እንደቀየጠ አለ፡፡
አለምም በዚህ ቅይጥ ሳቢያ ይበልጥ ህበረቀለማዊ እንደ ሆነች
አለች፡፡ ግሩም ተበጀ ከተረጎመው መጽሀፍ የተወሰደ…
ፍቅር ያሸንፋል
2.9K viewsDJ BOSS , 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 00:24:28 እንደ ወንዝ አለፈ...
ድፍርስ ጎርፍ አመልሽ ~ ይሁን በማለቴ፣
የሚንገዋለለው...
ቀሊል በሀ ግብርሽ ~ በልቶታል ፏፏቴ፣
የቁልቁል መንገድሽ...
ተጓዥ ይምሰል እንጂ ~ ባጀብ ወረት ሆኖ፣
አይሰነባብትም...
ቀላጭ ነው በጣይ ቀን ~ በ'ውነት ጀምበር ተኖ!!!
.
.
.
ያ ደራሽ ትምክህትሽ...
የድንገት ጅረትትሽን~ ጥራጊ ሰብስቦ፣
ሆ ብሎ ተመመ..
ሳር ቅጠል አፈሩን~ተፈጥሮን ወክቦ፣
.
.
ባታስተውይ እንጂ..
ከመክበርሽ በፊት~ ብሶት ያስገደደው፣
የጨው ልውስ ጣዕም...
ሰርክ እየጨመቅኩት ~ካይኖቼ ሚወርደው፣
ካፍያ ዶፍ ዝናቡ...
የውሀ ቤተሰብ ~ ክረምቱን አስታኮ፣
ወንዝ አርጎ ሊሾምሽ...
የኔ እንባም ውሀ ነው ~ ተኖ ዘንቧል እኮ!!!
.

.
.
እኔ ግን ልንገርሽ...
ሰሞነኛ ሆኖ ~ ቢሞላም ሸለቆሽ፣
ያልፍ እንደሆን እንጂ...
ከዳር ቆሞ እያየ ~ስትጎድይ ጠብቆሽ፣
(እንዳምና ታች አምና)
ዘሎ ጥልቅ አይልም...
ቂል አይደለም ልቤ~ ሞኝሽን ፈልጊ፣
መሻገሪያ አያጣም...
ይለፈኝ ክረምትሽ ~ ይደርሳል ብላጊ፣
አመልሽ ነው አንቺ..
በደሀ እንባ ካፊያ ~ቦይሽን ጥረጊ!!!!!
2.9K viewsDJ BOSS , 21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 00:17:32 ስለሄዱ የአፋቸው እንቅስቃሴ ይታያል እንጂ ምን እንደሚባባሉ አይታወቅም።

2.6K viewsDJ BOSS , 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 00:17:32 ቅንፍ () ፪ እሱ እና እሷ

ሽሮሜዳ ከሚገኘው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት በጥዋት ወጣ። ወደስራ። ፲ ደቂቃ ተራምዶ ታክሲ ተራ ደረሰ ፤ እንደ ሌሎች ታክሲ ተራዎች የመነን ታክክሲ ተራ ግርግር የለውም። ትልቅ ጭንቅላት ያለው፣ ቀይ ፣ ለንቦጫም 11 ወንም 12 አመት የሚሆነው ልጅ በፍጥነት ''አቶብስ ተራ አቶብስ ተራ'' እያለ ይጣራል። ያጠራሩ ፍጥነት 'ዝናብ እየመጣ ነው ቶሎ ግቡ ! እረ እናተ ሰዎች ዝናብ ሳይጥል ቶሎ በሉ እንጂ ! እረ ወይኔ በቃ በዝናብ በሰበስን' የሚል የቸኮለ ይመስላል። እንደቁራ ሚጮኸው ልጅ ታክሲ ውስጥ ገብቶ መሳለሚያ ወደሚገኘው መስሪያ ቤቱ ተሳፈረ።

ሽሮሜዳ ላይ የነበረው ደመናማ አየር አፍንጮ በር ላይ ካፊያ ፣ ጊዮርጊስ ላይ ቀላል ዝናብ ፣ መርካቶ ላይ ከባድ ዝናብ ሆኖ ጠበቀው። እዝከዚህ ጊዜ ግን ዝናቡ ቢዘንብም ፣ ከባድ ቢሆንም ፣ ቀላል ቢሆንም ለሱ ችግር አልነበረም ምክንያቱም ታክሲ ውስጥ ነው ዝናቡ አያገኘውም። አውቶብስ ተራ ላይ የታክሲው የመጨረሻ ማውረጃ በመሆኑ ዝናቡ ችግር ሊሆንበት ነው ፤ እስካሁን አላባራም በጣም እየዘነበ ነው ፣ ልጅ እግሩ የታክሲው ረዳት እና ሹፌሩ 'ውረድ እንጂ' በሚል አስተያየት አፈጠጡበት፤ ሌሎቹ ተሳፋሪዎች እየወረዱ አልቀው እሱ ብቻ በመቅረቱ። አልፈረደባቸውም እንጀራቸው ነው እሱን ከዝናብ አስጠልለው በሚቆዩበት ደቂቃ ሌሎች ታክሲዎች ተሳፋሪዎችን በመጫን ይቀድሟቸዋል።

ታክሲ ውስጥ ሆኖ ከዝናብ ሚጠለልበትን ቦታ በአይኑ በመቃኘት ፈለገ፦ፊት ለፊቱ ሸራ ወጥረው የሚሰሩ ጥንንጥዬ የቤዝነስ ቤቶች ማለትም ሊስትሮዎች ፣ ሻይ ቡናዎች አሉ ከነሱ በስተቀኝ ደግሞ ትንሽዬ የፖሊስ ማረፊያ ቀጥሎ ባስ መጠበቂያ አለ፤ ሁሉም በዝናብ ተጠላዮች ተሞልተዋል ፣ ከታክሲው በመውረድ እግሩ ወዳመራበት ሮጠ፣ እግሩ ያመራው ወደ ባስ መጠበቂያው ነው።

እንደደረሰ አንድ ጥግ ላይ ተጣቦ ቆመ። ከጎኑ ብዙ አይነት ሰዎች ነበሩ። በቀኙ፦ አናታቸው ላይ ወንፊት የሚመስል ጥቁር ሻሽ ያሰሩ ከሹራባቸው ላይ ነጠላ ያጣፉ ከስር አበባ የታተመበት ረጅም ቀሚስ የለበሱ በእግራቸው አርንጓዴ ኮንጎ ጫማ የተጫሙ ጠይም አሮጊት እናት በንፋስ እየተገፋ የሚመጣውን ወጨፎ ለመከላከለ ጥላቸውን ከፊት ለፊት ደቅነዋል። ካሮጊቷ ኋላ በስስት የሚተያዩ ፍቅረኛሞች ፀጥ ብለው ተቃቅፈው ቆመዋል። ፍቅረኛሞቹን እያየ ደስ የሚል ስሜት ተሰማው። ከዛ ግን ብቸኝነቱን ሲያስታውስ ከፋው። ወደግራው ዞረ ፤ ከሰዎቹ ጋር ተቀላቅላ ከዝናብ የተጠለለች አንዲት መልአክ ተመለከተ። አተነፋፈሱ ፈጠነበት። አንድ ጊዜ አየር በረጅሙ ስቦ ተነፈሰ። ከፊት ለፊቱ በግራ በኩል ቆማ ያለች ቀይ፣ ወፍራም፣ ልጅ ያዘለች ሴት ዞር ብላ ገላመጠችው። በድጋሚ በረጅሙ ተንፍሶ መልአኳን ወዳየበት አቅጣጫ ማተረ፤ ክንፍ የላትም ፀጉሯን ቁጥርጥር ተሰርታለች ከተቀባችው ቅባት ወይም በተፈጥሮዋ ፊቷ ወዛም ነው። አንገቷን ትንሽ ዘንበል አርጋ ስለምታይ አይኗ ትልቅ ይመስላል፣ የፃን ልጅ አፍንጫ ነው ያላት ትንሽዬ ነው። ከጉንጯ ጋር ተስማምተዋል። ከንፈሮቿ ሞላ ሞላ ስላሉ ለመሳ'ም የተፈጠሩ ይመስላሉ። (ያንዳንድ ሰው ከንፈር ጥርስን ከብርድ ለመከላከል ብቻ የተቀመጡ ይመስላሉ ምንም መረቅ የላቸውም ምንም ስጋ የላቸውም አጥንት ብቻ ሚሳሙ ሳይሆን ሚጋጡ ነው ሚመስሉት) ከቸኮሌት ገፅታዋ ጋር ሀርሞኒ የፈጠረ ስስ ጥቁር ሹራብ ከሹራቡ ላይ ከጉልበቷ ትንሽ ከፍ ያለ ቀይ ቀሚስ እና እስከ ጉልበቷ የሚደርስ ጥቁር ቡትስ ጫማ እና በቀኝ ትከሻዋ ላይ ጥቁር አነስተኛ ቦርሳ አንጠልጥላለች። ከነዛ ሁሉ ሰዎች ግን ዝናብ የተጠለለችውን መልአክ ያስተዋላት እሱ ብቻ ነው። ሌሎቹ እሷን እንዳያዩ አይናቸው የተጋረደ ነው ሚመስለው ማንም ዞር ብሎ የሚያያት የለም። ለሱ ብቻ የታየችውን መልአክ እንዴት እንደሚያወራት በሀሳቡ ሲያወጣ ሲያወረድ ቆየና ለንግግር ማስጀመሪያ ጠጋ ብሎ ''ዝናቡ ቶሎ ሚያባራ አይመስለኝም እንደዚህ አይነት ዝናብ ይቆያል'' አላት።

'' አዎ ይቆያል'' አለችው ባጭሩ አዝማሚያው ገብቷታል። ፊቱን ገርመም አድርጋ ተመለከተችው ፣ ለሰከንዶች በቆየ እይታዋ ፀገሩን ፣ አይኑን ፣ አፍንጫውን ፣ ከንፈሩን ገምግማለች። "ቆንጆ ነው" ብላ አሰበች። እሱ በበኩሉ ከዚህ በፊት መልአክ አውርቶ ስለማያውቅ መልአክቶች ስለምን ቢወራ ነው ደስ ሚላቸው እያለ በሀሳቡ ሲያወጣ ሲያወርድ ቆየና ''እዚህ ሰፈር ነሽ''? አላት። ፈገግ ብላ '' አይ አይደለሁም ወደ ስራ እየሄድኩ ነው ''አለችው። የበለዙትን የፊት ጥርሶቿን ምትሀታዊ በሆነ ፈግታዋ ውስጥ ተመለከቶ 'የአዳማ ልጅ ትሆናለች' ብሎ ገመተ። የመልአክት ስራቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓግቶ የኔ ስራ ምን ይሰራልሀል ወረኛ እንዳትለው ሰግቶ '' ምንድነው ምትሰሪው'' አላት ምን ሊሆን እንደሚችል በሀሳቡ እየገመተ እየጣለ።

አንድ የመንግስት መስሪያቤት ውስጥ ፀሀፊ እንደሆነች ነግራው ፣ ወደ ሁለተኛ ግምገማዋ ገባች። አይኑን እያየች ማውራት እንዳፈረች እንደመሽኮርመም እያደረጋት አንገቷን በሱ በኩል ዘንበል አድርጋ ጫማውን አየችው፦ የዝናብ ነጠብጣቦች ያቀረረ እንባ መስለው ተዘባርቀው ውበቱን ሊቀንሱ ቢጣጣሩም ፏ ብሎ የተወለወለ ጥቁር ቆዳ ጫማ ተጫምቷል። ጫማውን ተከትሎ ብዙም ያልጠበበ ብዙም ያልሰፋ ጥቁር ጅንስ ሱሪ ለብሷል። ከላይ የለበሰውን ግራጫ ሹራብ ቀድማ ያየችው ቢሆንም ከጫማው እና ከሱሪው ጋር ስታየው ሀርሞኒ ስለፈጠረ አለባበሱን እንድታደንቅ አስገደዳት።

ውበቱን እና አለባበሱን ብታደንቅም ቶሎ ልትሸነፍለት አለፈለገችም አነጋገርዋን ቁጥብ እና የተመጠነ ነው የምታደርገው። የሚጠይቃትን ጥያቄ ትመልሳለች ግን ስለሱ ለማወቅ ምንም ጥረት አታደርግም። ብዙ ግዜ በታክሲ ተሳፍራ ስትሄድ አንዳንድ ካጠገቧ የሚቀመጡ ወንዶች እሷን ለማውራት ሲቁነጠነጡ የማውራት ግዴታ ያለባቸው ይመስል ወሬ ለመፍጠር ሲጨነቁ ስታስተውል በጣም ይገርሟታል ፣ በሆነ ጉዳይ በመንገድ ስትጓዝ እስኪጨንቃት ሚያፈጡባት ወንዶች ይሰለቿታል፣ መስሪያ ቤቷ የመቶ ብር ራት ጋብዞ አብሯት ለማደር የሚንሰፈሰፉ ወንዶች አሰልችተዋታል። የሱ ግን ለየት አለባት። ቀልቡ እና ቀልቧ የተስማሙ የተግባቡ አይነት ስሜት ይሰማታል ግን መቸኮል አልፈለገችም።

ስለ ዝናብ ፣ ስለ ክረምት ማለፍ ፣ ስለ ስራ ሲያወሩ ቆዩ። ዝናቡ ቀለል እያለ ሄደ ። በመጠለያው ውስጥ የነበሩ ሰዎችም በየፊናቸው መሰማራት ጀመሩ፣ ወደየ ጉዳዮቻቸው ነጎዱ። ዝናቡ ሙሉ ለሙሉ አላባራም። መጠለያ ውስጥ አሮጊቷ ፣ ልጅ ያዘለችው እናት ፣ በስስት የሚተያዩት ፍቅረኛሞች እና እሱ እና እሷ ቀሩ። ከቦርሳዋ ውስጥ ጥላ አወጣች እና ዘረጋች። ልትሄድ ነው። ቅር አለው። ቅር ባለው ድምፀት " እዚህ አካባቢ ነው መስሪያ ቤትሽ" ብሎ ጠየቃት። ዞር ብላ አየችው "አይደለም አብነት ነው ያለው። ታጥፌ ሰባተኛጋ ታክሲ መያዜ አይቀርም። ወደዛ ከሆንክ እንሂድ" አለችው። በችኮላ "እሺ አዎ" አላት። ቁመት ስለሚረዝማት ጥላውን እንዲይዝ ሰጠችው። ሶስት እርምጃ ያህል እንደተራመዱ ዙር ብሎ የባስ መጠበቂያውን አየ። ልጅ ካዘለችው ሴት ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ ገላመጠችው። አይኑን ወደ ፍቅረኛሞቹ አዞረ ካጠገባቸው ማንም እንደለለ ሁሉ በጥልቅ ስሜት እየተሳሳሙ ነው። አሮጊቷ የለችም። ቀልቡን ወደ እሷ እና ወደ መንገዱ መልሶ እንዴት ስልኳን እንደሚቀበላት እያሰላሰለ ጉዞዋቸውን ቀጠሉ። ብዙ አልተነካኩም። ጥላውን በቀኝ እጁ ይዟል በቀኙ ናት። የሆነ ነገር ይላታል ፣ የሆነ ነገር ትመልሳለች። እየራቁ
2.8K viewsDJ BOSS , 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ