Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidu_kidu — ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች
የሰርጥ አድራሻ: @kidu_kidu
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.93K
የሰርጥ መግለጫ

ጣፋጭ ግጥሞችን ይፈልጋሉ
ልብን የሚማርክ ደብዳቤዎችስ ማድመጥ ከፈለጉ ይቀላቀሉን
@kidu_kidu.......https://t.me/ -me8FzuCO5NmZmI0
የፍቅር ፣ የትዝታ ፣ የይቅርታ ደብዳቤዎችን ከማያልቀው ማዕዳችን ገብተው ይመገቡ፡፡
Connect Admin @Who12

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-07 16:22:36 ." ከአንድ እርምጃ ቡኋላ እሾሁ ይታይሻል አይደል!? ታድያ ስለምን ለመራመድ ታኮበኩቢያለሽ?" ጠየቀኝ

" መሄድ ስላለብኝ። ከመጣሁበት የጭቃ እሾህ መንገድ ይሄ ኢምንት መስሎ ስለታየኝ ወይ ደሞ እኔንጃ! ግን'ኮ ምናልባት ይህ እሾህ ቢወጋኝ እግሬን ነው የሚያደማው ፤ በርግጥም መርቅዞ ሲታከክ ሰላም የሚሰጥ ቁስል ይሆነኛል። እመነኝ! አትስጋ ፤ እሄዳለሁ። ይልቅ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ? የልብን ቁስል በየት በኩል ገብተው ቢያኩት ይሆን እረፍት የሚሰጠው?" አይኑን እያየሁ ጠየኩት። ትንፋሹን እንኳን ለመልስ'ነት አላቀረበልኝም። በቀስታ አቀፈኝ። ከቃሉ በላይ እቅፉ መልስ ሆነኝ መሰለኝ እኔ ቀጠልኩ።

" ታውቃለህ እጄን ከእጁ መፈልቀቄ አጥብቆ እንዲይዘኝ ነበር! ግራውን መርጬ ስሄድ መንገዴን እንዲወደው ነበር! ስገፋው እኮ እንዲፈልገኝ አጥብቄ መፈለጌ ነበር ! ራስ ወዳድ ነኛ!? የምርም ዝም ሲለኝ ምንምነቴን እየነገረኝ ይመስለኝ ነበር፤ በርግጥም ነው። ነፍሴን ሳቀርብለት ከሌለኝ ላይ ሞልቼ ቢሆንም ነፍሱን የሰጠኝ ግን የተረፈለትን ነበር። ምናልባት ለምን ብዬ አለመጠየቄ ስህተት ቢሆንም ማስመሰሉን እንዳይደግም ማድረጌ ግን ልክ ነበርኩ። በመሆን መጉደል ግን ምንኛ ህመም ነው!? " እቅፉ ሰላም ሰቶኛል፤ አልፌው እንዳልሄድ ጨርሶውኑ አድክሞኛል።

"የልብ ቁስል እንዴት ነበር የሚታከከው!?" ስለመንገዴ እያመነታሁ ጠየኩት
"እንደዚ" ደግሞ አቀፈኝ። ልቤ ውስጥ የማላውቀው እፎይታ ተሰማኝ
"እወድሃለሁ!" አልኩት
"አፈቅርሻለሁ!"

ዳግመኛ እጆቼን ያዛቸው፤ ሊለቀኝ አይፈልግም። አይኖቼ ውስጥ ምስሉን ፍለጋ ተተከለ ፤ ራሱን የማያውቀው ያህል ሊያጣው አይፈልግም። የተረፈ ነፍሴን ሳይሆን በእቅፉ አድሶ ሰላም የሰጣትን ነፍስ ያለማንም ከልካይ አስረኩብኩት።

ወትሮውኑም ያላየነው አንድ ማንም ነበር....
1.4K viewsDJ BOSS , 13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:18:38 ይብላኝለት ለኔ
።።።።።።።።።።።

ያልወረደ መና ፣
ልቡን ለሰቀዘው፣
ያልተበላ ዳቦ፣
፣አንጀቱን ለያዘው።
ባልተጠጣ ወተት ፣
ምናቡ እያገሳ፣
ስጋው ሲደነድን፣
ልቡ ለሚከሳ።

ይብላኝለት ለኔ...
ኖርኩ እያለ ሲሞት፣
አፈር ለማይለብሰው፣
ይብላኝለት ለኔ
በነፍስና ስጋ፣ ድንበር ተገትሮ፣
መኖር ላልቀመሰው።
ዛሬ ቀኑ ፀሀይ ፣ ነግ ደሞ ዳመና፣
ታቻምና ረሀብ ነው ፣ አሁን ብልፅግና።
ፍቅር ይተኮሳል፣ ከወዲያኛው ማዶ፣
ዘመድ ይገናኛል፣ ተራራው ተንዶ።
ምናምን ምናምን...
ይሉት እንቶፈንቶ...

ቢያገኝ ለሚበላ ፣ቢያጣ ለሚጋደም፣ ተመስገኑን በልቶ፣
ምን ሊፈይድለት፣ አንዱ አደረ ቢባል፣ በሰው ስጋ አግስቶ?

ይብላኝለት ለኔ...
ከሰው አብራክ ወጥቶ ፣
ሰው ለማይናፍቀው፣
ዕልፍ ችግኝ መሀል፣
ተስፋው ለደረቀ
እኔን ባይ ለራቀው።
ይብላኝለት ልቤን ፣
ይብላኝለት ገላ፣
ብርድ አያውቅ ሙቀት፣
የአፍላነት ዘለላ።
እንባ የለው ዐይኔ፣
ላብ የል ከአካላቴ፣
እንዲህ ያል ድርቅናን፣
ከማን ሸመትኩ እቴ?
ሳቅ እማያስቀኝ ፣
ሰቆቃ እማይገደኝ፣
ምን ያል የሰው አውሬ ፣
አምጦ ወለደኝ?

ይብላኝለት ዐይኔን ...
የሱ ብጤ በርባን፣
አማትሮ ለሚያጣ፣
ውንብድናው አንሶት፣
አምላክ ለሚቀጣ።
ባልሰመረ ቅኝት፣
ለሚደክር ከንፈር፣
መሳም ላልታከተው
ያለመተፋፈር።
ለማይደክም እግሬ፣
በየብስ ባህሩ፣
ንዳድ ለሚነዳው
አልፎ ከድንበሩ።
ይብላኝለት ለኔ...
ሰው ተብሎ ላልሞላው፣
የ "ሰ"ን አንድ ቅኔ።
ይብላኝለት ለኔ!
1.5K viewsDJ BOSS , 13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 12:53:59 ፍቅርና ጊዜ

ሁሉም አይነት ስሜቶች የሚኖሩበት አንድ ደሴት ነበር፡፡ የደስታ ስሜት፣የመከፋት ስሜት፣ እውቀት እና ሌሎቹ ስሜቶች ፍቅርን ጨምሮ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ደሴቱ ሊሰምጥ እንደሆነና ሁላቸውም ስሜቶች ሊያመልጡ የሚችሉበትን ጀልባ መስራት እንዲችሉ አዋጅ ተነገረ፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን ሲሰሩ ፍቅር ግን ደሴቱ እስኪ ሰምጥ ድረስ ጀልባ አልሰራም ነበርና ከሊሎቹ ስሜቶች እገዛ ለመጠየቅ ወሰነ፡፡

ሀብታምነት የሚባለው ስሜት በፍቅር በኩል ሲያልፍ “ሀብታም ሆይ ከአንተ ጋ ይዘኸኝ ልትሻገር ትችላለህ?” አለው ፍቅር፡ “አይሆንም፡፡ አልችልም በጀልባየ ውስጥ በርካታ ወርቅና መዳብ የያዝኩ በመሆኑ ለአንተ የሚሆን ቦታ የለኝም” ሲል ጥሎት ሄደ፡፡ ፍቅር አቶ ስግብግብን ሲያልፍ ተመለከተውና እንዲረዳው ጠየቀው፡፡ “አልችልም አቶ ፍቅር ጀልባየን ታበላሽብኛለህ አይሆንም ብሎ” ትቶት ሄደ፡፡ አቶ መከፋትን በቅርብ አገኘውና አሁንም ፍቅር አብሮ እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡ “ኦው! ፍቅር አዝናለሁ እኔ ብቻየን ነው መሆን የምፈልገው፡፡” ብሎ አሰናበተው፡፡ ደስታም ፍቅርን አልፎት እየሄደ በጣም በፈንጠዝያ ደስታ ላይ ስለነበር ፍቅር ሲጠራውም መስማት አልቻለም፡፡ ባጋጣሚ “ፍቅር ና እኔ እወስድሃለሁ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲዞር የተባረከ አዛወንት ነበር፡፡ “ጊዜው ነው” ወዳጀ ፍቅር ሲል እውቀት የተባለው ስሜት መለሰ፡፡ “ጊዜ ማለት!?” ፍቅር በመደነቅ ጠየቀው “ነገር ግን ለምን ጊዜው ሊረዳኝ ቻለ?” እውቀት ፈገግ እያለ ምክንያቱም “የፍቅርን ዋጋ መረዳት የሚችለው ጊዜ ነው፡፡” ሲል መልስ ሰጠው፡፡
3.4K viewsDJ BOSS , 09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 11:47:13 ሻማው ሲጠፋ
ሀዘን ካሰጠመው
ጨለማ ከዋጠው
ከቀዝቃዛው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል ...
አንቺ ግን የለሽም ሁሉ ሞልቶ.
2.9K viewsDJ BOSS , edited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 09:24:58 በስሜትሽ በስሜቷ
አምባር ክንዷ ዋንጫ አንገቷ
እየረታኝ እርቃን ቃሏ
እያሰረኝ ልቅ አካሏ
ብዕር ቁልቁል እያደላ
ልገጥምለት ላ'ልቦ ገላ

ስሽኮረመም ስግደረደር
ሐረግ ስኩል ስንኝ ስድር
ቢያስገርመኝ
ቢያስደምመኝ ሃቅ እውነታ
ለቃል ፊደል ሰጪ ጌታ
ለኔ አንቺን የሚነሳኝ
ከተሰጪ የሚረሳኝ
ምን ባጠፋ ምን ብበድል
ያሳነሰኝ ከቃል እድል
ምን ባይኖረኝ ምን ብጎድል?

እግዚአብሔሩስ እየሳሳሽ
ለሰው ላዳም የሚነሳሽ
ምን ብትሆኚ መከልከልሽ
ወይ አይድርሽ
ወይ አይኩልሽ

ለመላዕክት ለ ቅዱሳን
ማትገለጭ
ሚስጢር ድርሳን
ሂጃብ ነሽ ወይ?
ወይ ማህተብ
የእምነት ማጽኛ የእውነት ገደብ
መሐላ ነሽ? ወይ ቃልኪዳን
ላዳም ተስፋ ለሰው መዳን

ምን ነሽ አንቺ
ሚያስውብብሽ ሰይጣን መልኩን
ሚለካብሽ ውበት ልኩን
መስታዬት ነሽ? ንጹህ ውሃ
በረዶ ነሽ? ወይ በረሃ
እየቆየሽ ምትጠሚ
ዲያቢሎስን ምትጠቅሚ

ትዝታው ነሽ? ወይ ቅጽበቱ
ሳያዘቅጠው መተበቱ
ለነበረው ሰማይ ቤቱ
እንባ ካይኑ እየደማው
ያንን ስልጣን ያንን ግርማው
ሚስልብሽ ዘፈን ዜማው?

ላትገዝፊ ካንዲት ፊደል
ንጥል ሆኜ የምበደል
ጠንቋይ እንኳ ማይገምትሽ
እንደ እጣን የምትጨሽ
ማን ነሽ አንቺ
ምን ነሽ አንቺ
ቅኔ ነሽ ወይ ማትፈቺ?
3.0K viewsDJ BOSS , 06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 09:21:50 " የናፈከኝ ለታ"

ብዙ አለም ኣላውቅም
ብዙ አለም ኣልኖርኩም
ጊዜን ካንተ ጋራ
ቁጥር ኣልሰፈርኩም
ግን......የናፈከኝ ለታ
አይንህ ከአይኔ ሲያርፍ
አቅሜን እንዳሳጣኝ
በከንፈርህ መሳም
ልቤ እንደከዳኝ
በእቅፍህ አለም
ሚወስደኝ አታሎ
ደስታ እንደ ሞት ነው ወይ
እራሴን አስጥሎ
እኔ አላውቅም.......
ነብስ ድረስ ሚዘልቅ
ፍቅር ይሰማኛል
የናፈከኝ ለታ
ሰከንድ ያድርብኛል
ትዝታን እየካበ
አንተን አንተን እያለ
እኔን ይንደኛል
ማሰቤስ የታለ
ሸመትከው በፍቅርህ
ሸከፍከው በጀርባ
ልቁረጥ ያሉት ፍቅር
ለምለም ነው ሚረባ
የናፈከኝ ለታ........
አንተ አደርስበት
ጥልቅ ነው ስሜቱ
በሌለህበት
እልፍ ነው ፍሰቱ
ናፍቆትህ ትንግርቱ
.
.
.
2.6K viewsDJ BOSS , 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 16:14:00
3.5K viewsDJ BOSS , 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 16:13:26 አትመጣም

አባቴ እወድካለው
3.2K viewsDJ BOSS , edited  13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 16:09:12 ስንብት
በዘናጭ ፊደላት በደማቅ ቀለማት
ፍቅርሽን ለማድመቅ የተንተባተብኩት
ፊትትሽ ተሰይሜ የተንቀጠቀጥኩት
ፍቅር እኮ ነዉ ያልኩት
የቃል ሽንገላ እንጂ አልነበረም እዉነት ....
3.2K viewsDJ BOSS , 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 09:14:39 ......ገነቴ........
በሚያምረው ገላዋ ልጥፍ ብሎባት
ላይዋ ላው ተጭኖ እንደልብ እያሻት
ከላይ እስከታቿ ከታች እስከላይዋ
ከፍ ዝቅ እያለ ያሟሟል ገላዋ
በዛ ውብ ገላ በዚያ ሰውነቷ
አዝላ በጀርባዋ ፈታ መቀነቷ
ታባብለዋለች በእጅዋ አሻሽታ
ምናለ ባረገኝ? ብሆን በሱ ቦታ
ላንድ ቀን እንኳ ለዛሬ ለአፍታ
እንዴት ታድሏል ያሸዋል ገላዋን
ምንኛ ገነት ነው መሆን እንስራዋን
.



3.3K viewsDJ BOSS , 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ