Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidu_kidu — ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች
የሰርጥ አድራሻ: @kidu_kidu
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.93K
የሰርጥ መግለጫ

ጣፋጭ ግጥሞችን ይፈልጋሉ
ልብን የሚማርክ ደብዳቤዎችስ ማድመጥ ከፈለጉ ይቀላቀሉን
@kidu_kidu.......https://t.me/ -me8FzuCO5NmZmI0
የፍቅር ፣ የትዝታ ፣ የይቅርታ ደብዳቤዎችን ከማያልቀው ማዕዳችን ገብተው ይመገቡ፡፡
Connect Admin @Who12

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 11:17:07 ማንን ነው

እግዜር ጥበበኛን
የአርያሙን ንጉስ
የሚመሰገነውን
ያን ስሉስ ቅዱስ
አንተን የወደደ
ወደ ምድር የላከ
አንዲትን ማህፀን
ምነኛ ባረከ
ደግሞም እናትህን
ያቺን ባለፀጋ
ትወልድ ዘንድ አንተን
ከልቧ ፈልጋ
በአንዲት ልዩ ቀን
ከአንድ አልጋ ውላ
በልብ ሰንጥቅ ደስታ
አንድ ፍቅርን ብላ
ፍቅርን ፀነሰች ፍቅርን ወለደች
ፍቅርን አቀፈች
ደስ እያላት ይኸው
አንተን ለአለም ቸረች
አንተ የልቤ ሰው
በፍቅርህ ጉደኛ
ሰርከ የምማሰው
እኔ ያንተ አፍቃሪ
እኔ ያንተ ወዳጅ
አንተን ከሰጠኝ
ከየቱ ልወዳጅ
ከእግዜሩ ነው ወይ
ቀድሞ ካሰበክ
ወይስ ከእናትህ
ዘጠኝ ወር በሆዳ አንተን በታቀፈች
ስለየትኛው ልስብክ
ወይስ ያቺን ቀን
አንተን ያወኩባት
በልቤ ላኖርህ
በእድሜ ያሰብኳት
ወይ ደሞ ቅድስት
አንተ የኔ ተስፋ
ሆነህ የመጣህ ቀን
ህመሜ ሊጠፋ
እና ልጠይቅህ
እግዜሩ ሲያስብህ
እናትህ ስትወልድህ
እኔ አንተን ሳውቅህ
ዳግም ስታኖረኝ
በየትኛው ቀን ነው
አንተን ለኔ ያደለኝ
ማንን ነው ማመስገን
ማንንነው ማወደስ
የግኝትህ ቀን ሁሉ ለህይወት መዓዛ ነው
አንተነትህ አደስ
(እንኳን ተወለድክልኝ )
.
.
.
.
223 viewsDJ BOSS , 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:16:00 .

..


ሁሉም ይሁን ምክንያቱም እነሱን ደስተኛ አላረጋቸውም ፡፡
መቼ ይሆን ግን በፊታቸው ሙሉ ሆነን የምንገኘው:
ሁሌ እንደጎደልን ነው እንዴት ማስደሰት እንዳለብን
እንኳን አናውቅም :/አንዳንዴ እነሱን በሆንን እና ሁሉ
ነገራቸውን መጠበቅ ብንችል ምነኛ መታደል ነው: ሆኖ
አለመገኘት ግን በጣም ይከብዳል:: አፍቃሪ ሆኖ ለሚወዱት
የልብ እርካታ አለመሆን ፣ፊታቸው ቆመን ፈገግታቸውን አለማየት ፣ሚሆን የመሰለን እንደማይሆናቸው ማወቅ ፣የእኛነት ጉድለትስ ለራሳችን አቅምን ያሳጣል ።የምር በቃ ለሚወዱት አለመሆን ያማል.......
.
.
.
..

.
..... ፍቅር ያሸንፋል
193 viewsDJ BOSS , 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:13:40 .
..
..
..
...



ለእነሱ ምንም ማለት አልነበረም እንደመዝናኛ ወይ ደሞ ከሱስ ስሜታቸው መብረጃ ::አንደበት ለከት አለው ልቅ ሲሆን ስንቱን ይወስዳልና: እንዲህም አለ እንዴ አስብለው ስንቶች ያለ ስማችን ስም ሰጥተው አፋችንን አስያዙን: ምክንያቱም እንናገር ብንል እንኳ ሌላ ሀሜት እናተርፋለን አይገርምም ህይወት ግን ቀስ እያለች ነው ምታስተምረው ::ስለራስ ከራስ በላይ ማን? ሀቃችንን እውነታችንን እያወቅን እነሱ በዘሩት ዘር ከልባችን መከፋትን አጨዱ እናም ስኬታቸው ነበር ሆነላቸው ለመናገር አንደበታችን ከበደው ምክንያቱም ያለ እውነቱ እውነት መሳይ ተጠየቀ ቢችል እንኳን ንግረቱ ይታመን ይሆን? ሰው ግን የራሱ ሞልቶለት ይሆን ስለሰው እየኖረ ያለው? ግን እኮ ቢያንስ ማውራት ካልቀረ መፍጠራቸው ካልቀረ ምን ነበረበት በክፉ ፈንታ ጥሩን ቢያስቡልን በነቀፌታው ፈንታ ሙገሳን ቢያበጁ ጥሩ አሉባልታ ከምናለቅስበት ይልቅ ምንስቅበትን አላውቅም እንዲያ ቢሆን ግን ምነኛ ነበር (ብቻ ግን ለእነርሱ ምንም ማለት አልነበረም ለእኛ ግን...........)
.
.
.
.
.
ፍቅር ያሸንፋል
245 viewsDJ BOSS , 08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 15:09:35 ስቀሽ … አበረድሽኝ

ከጥም ቆራጭ ምንጭሽ ፥ ልጠጣ ጎምጅቼ
ላታልልሽ ዝቼ
ጢሜን ተላጭቼ
ጫማዬን አጥድቼ
በሚያሽበለብል ቃል ፥ ምላሴን ገርቼ
ለበአሌ ላርድሽ ፥ ቢላዋየን ስዬ
ሁዳዴን የጦመ ፥ መልካም ሰው መስዬ
እንደ አታላይ ተኩላ
ሊነጥቅ ሊበላ
ለምድ እንደለበሰ ፥ በበጎች መካከል
ሳር መጋጥ ጀምሮ ፥ መንጋውን ለመምሰል
በዚያው እንደቀረ ፥ ከሰርዶ ተዋዶ
ጨዋታ ወግሽን ፥ ዠሮየ ተላምዶ
ፍቅር አልብሰሽኝ
ውሀ ልሰርቅሽ ስል ፥ እርጎ አበድረሽኝ
ነድጄ መጥቼ ፥ ስቀሽ አበረድሽኝ


ፍቅር ያሸንፋል
3.4K viewsDJ BOSS , edited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 10:01:44 ." ከአንድ እርምጃ ቡኋላ እሾሁ ይታይሻል አይደል!? ታድያ ስለምን ለመራመድ ታኮበኩቢያለሽ?" ጠየቀኝ

" መሄድ ስላለብኝ። ከመጣሁበት የጭቃ እሾህ መንገድ ይሄ ኢምንት መስሎ ስለታየኝ ወይ ደሞ እኔንጃ! ግን'ኮ ምናልባት ይህ እሾህ ቢወጋኝ እግሬን ነው የሚያደማው ፤ በርግጥም መርቅዞ ሲታከክ ሰላም የሚሰጥ ቁስል ይሆነኛል። እመነኝ! አትስጋ ፤ እሄዳለሁ። ይልቅ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ? የልብን ቁስል በየት በኩል ገብተው ቢያኩት ይሆን እረፍት የሚሰጠው?" አይኑን እያየሁ ጠየኩት። ትንፋሹን እንኳን ለመልስ'ነት አላቀረበልኝም። በቀስታ አቀፈኝ። ከቃሉ በላይ እቅፉ መልስ ሆነኝ መሰለኝ እኔ ቀጠልኩ።

" ታውቃለህ እጄን ከእጁ መፈልቀቄ አጥብቆ እንዲይዘኝ ነበር! ግራውን መርጬ ስሄድ መንገዴን እንዲወደው ነበር! ስገፋው እኮ እንዲፈልገኝ አጥብቄ መፈለጌ ነበር ! ራስ ወዳድ ነኛ!? የምርም ዝም ሲለኝ ምንምነቴን እየነገረኝ ይመስለኝ ነበር፤ በርግጥም ነው። ነፍሴን ሳቀርብለት ከሌለኝ ላይ ሞልቼ ቢሆንም ነፍሱን የሰጠኝ ግን የተረፈለትን ነበር። ምናልባት ለምን ብዬ አለመጠየቄ ስህተት ቢሆንም ማስመሰሉን እንዳይደግም ማድረጌ ግን ልክ ነበርኩ። በመሆን መጉደል ግን ምንኛ ህመም ነው!? " እቅፉ ሰላም ሰቶኛል፤ አልፌው እንዳልሄድ ጨርሶውኑ አድክሞኛል።

"የልብ ቁስል እንዴት ነበር የሚታከከው!?" ስለመንገዴ እያመነታሁ ጠየኩት
"እንደዚ" ደግሞ አቀፈኝ። ልቤ ውስጥ የማላውቀው እፎይታ ተሰማኝ
"እወድሃለሁ!" አልኩት
"አፈቅርሻለሁ!"

ዳግመኛ እጆቼን ያዛቸው፤ ሊለቀኝ አይፈልግም። አይኖቼ ውስጥ ምስሉን ፍለጋ ተተከለ ፤ ራሱን የማያውቀው ያህል ሊያጣው አይፈልግም። የተረፈ ነፍሴን ሳይሆን በእቅፉ አድሶ ሰላም የሰጣትን ነፍስ ያለማንም ከልካይ አስረኩብኩት።

ወትሮውኑም ያላየነው አንድ ማንም ነበር....!

ፍቅር ያሸንፋል
4.1K viewsDJ BOSS , 07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 09:56:09 የአይምሮ ሰላም

ሁሉንም ለማስደሰት እንደሚጥር ሰው ከንቱ የለም! ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ነገር አይደሰትም እኮ፤ በተለያየ ነገር ለሚደሰቱ ሰዎች ስንል ደግሞ እኛ እንደ ወረቀት መተታጠፍ የለብንም።

ህሊናችን የሚነግረንን አይምሮአችን የሚያዘንን ልባችንን በደስታ የሚቀበለውን ብቻ መርጦ ማድረግ፤ ያኔ ሰዎች ቢደሰቱም ባይደሰቱም ህሊናችን ግን ምን ነካህ እያለ አያስጨንቀንም። ወዳጄ ለህሊናህ ስትታመን ሁሌም ውስጥህ ሰላም አለ!
የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ
3.5K viewsDJ BOSS , 06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 12:51:13 #ስጦታ
አንድ ቀን ግን እናቴ ካለወትሮዋ ተለሳለሰች፡፡ በዚህ የባህሪ ለውጥ በጣም ነበር የተገረምነው፡፡ አንድም ቀን ስጦታ ሲሰጠንና ስንቀበል ፊቷ ተፈቶ የማያውቀው እናታችን፤ አጎታችን (ወንድሟ) ከልጆቹ ሁሉ ለይቶ ለእኔ ስጦታ ሊሰጠኝ ሲል ፈገግ አለች፡፡ከምር ፈገግ አለች! እሱ ስጦታውን ሲያወጣ፣የሆነች የተንኮል ፈገግታ ፊቷ ላይ አንዣበበች፡፡ እንዲያውም ጭራሽ “ምን ያቅደረድርሃል? ተቀበል! አጎትህ አይደል አለችን፡፡ የእናቴ ተንኮል የተገለጠልኝ በኋላ ነበር፡፡ ሴት መለኛ ናት የሚባለው የገባኝ በእናቴ ነው፡፡

አቤት የዚህ አጎቴ ስጦታ ሲገርም! ይኼ አጎታችን ገንዘብ ነፍሱ ነው፡፡ ማነት አይደለም፤ ለምሳሌ አጎታችን ሲራመድ ትንሽ ያነክሳል፡፡ወታደር ስለነበር አንዳንዶች ጦር ሜዳ ተመትቶ ይመስላቸዋል፡፡ እሱ እንደሆነ ከጦር ሜዳ የተመለሰው ጠላት ዝንቡን እሽ ሳይለው ነበር፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው! (እውነት ይሁን ውሸት ግን አላውቅም፤ ሲወራ ነው የሰማሁት) አንድ ቀን መንገድ ዳር እቃ ገዝቶ መልሱን ሲቆጥር፣ ስሙኒ ከእጁ አፈትልካ ትወድቃለች፡፡ ሣንቲሟ ስትንከባለል፣ አጎቴ አጎንብሶ ሲከተል ዘሎ መኪና መንገድ መሃል ይገባል፡፡ አጎቴ ስሙኒዋ ላይ ሳይደርስ ፣ሲግለበለብ የመጣ ታክሲ ቀኝ አግሩን አገኜው፤ ይኼው እስከ ዛሬ ያነክሳል፡፡ ታዲያ ይኼ አጎቴ አልፎ አልፎ ነው ስጦታ የሚሰጠን፡፡ እንዲያውም ስንቀልድ “የአጎታችን ስጦታ እንደ ፀሐይ ግርዶሽ በመቶ ዓመት አንድ ጊዜ ነው የሚከሰተው እንል ነበር፡፡ ለዚያውም ደግሞ ስጦታው ዝም ብሎ አይሰጥም፤ ሂደት አለው፣ማብራሪያ አለው፣መግለጫ አለው እና የዛን ቀን የሰጠኝ ስጦታ ትዝ ይለኛል! እቤታችን አራት ቀን ሰንብቶ በአምስተኛው ቀን ሊሄድ ሲነሳ “ኧረግ ረስቸው አቡቹ ና ስቲ ወዲህ ስጦታ ገዝቼልህ፣ረስቼ ተሸክሜው ልሄድ ነበር! አለ:: እኔ ደግሞ ለሸክም የሚበቃ ምን ጉድ አመጣልኝ ብዬ በግርምት መጠበቅ! መጀመሪያ እጁ ጋቢውን እየሰረሰረ ካፖርቱ ላይ ደረሰ፣ ካፖርቱን አልፎ ኮቱ፣ ኮቱን ሰርስሮ ከሸሚዙ ደረት ኪስ ውስጥ ምዝዝ አድርጎ፣ አንዲት ገና ያልተቀረጸች አዲስ እርሳስ አወጣ! በቃ እርሳስ ነበር ስጦታው፡፡ ያን ሁሉ ቁፋሮ ለተመለከተ፣ አጎቴ ነዳጅ የሚያወጣ ነበር የሚመስለው፡፡ “ይኼው….ይኼ ተላይ ያለው ማጥፊያው ነው(ይፈነዳ ይመስል በጥንቃቄ እየነካ)….አሁን __ የእርሳስ ማጥፊያ ምን ማብራሪያ ያስፈልገዋል? “በጣም አትፈግፍገው፤ ቶሎ ያልቃል፡፡ ደሞ ስተቀርጥ አባትህ በምላጭ ይቅረጥልህ፡፡ ይኼ ዘመን አመጣሽ መቅረጫ አንዴ ጠርቦ ነው የሚጥለው” ብሎ ከረዥም ምክር ጋር እርሳሷን ሰጠኝ፡፡ ይኼ ሲገርመኝ ከዚያን ቀን ጀምሮ ንዝንዙ በየት ይልቀቀኝ፡፡ እቤታችን በመጣ ቁጥር ሌላ ስጦታ የለም፡፡ “አቡቹ ያ ርሳስ ..እንዴት ነው? …ጥሩ እየተገለገልክበት ነው አዎ በጣም አትቅረጠው እንደነገርኩህ በምላጭ፣ሥዕል ደሞ ሣልበት ሥዕል ትልቅ ሙያ ነው… ለሥዕል ዋናው ነገር 'ርሳስ ነው፣ 'ርሳስ ካለ ሥዕል አለ፡፡ የሁሉ ነገር ንድፍ፣ ይኼ ሁሉ የምታየው ሕንጣና ፎቅ ሳይቀር የንድፉ መነሻው 'ርሳስ ነው፡፡ አንዳንድ ማስታወሻም ካለ፣ ከጡህፍህ ሥር በስሱ ለማስታወስ ብትጥፍበት ትችላለህ፡፡ በቃልህ ከተያዘልህ በኋላ ታጠፈዋለህ አጎቴ ከሚገባው በላይ ሲያካብደው፣ የማውቀው እርሳስ የሆነ ሌላ ተአምር ነገር መሰለኝ!!

#ከዕለታት_ግማሽ_ቀን
አሌክስ-አብርሃም
ከገፅ 163-164 የተቀነጨበ.
4.0K viewsDJ BOSS , 09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 19:27:17 Channel photo updated
16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 19:26:07 Channel photo removed
16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 10:54:00 "አሹ ሁለት ብር ይዘሀል?" አለኝ የመንደራችን ቀፋይ፣ ከሁለት ቀናት በፊት
'ምን ይሠራልሀል?' አልኩት የሁል ጊዜ ሠበቦቹ ስለሚያዝናኑኝ
"እራሴን ላጠፋ ፈልጌ አሪፍ ገመድ መግዛት ፈልጌ ነው" አለ ሳቅ እያለ
ከኪሴ ድፍን አሥር ብር አውጥቼ እየሰጠሁት
'ካሚል ሱቅ አሪፍ ሲባጎ ታገኛለህ፤ ሁለት ሜትሩን በሁለት ብር ይሸጥልሀል' አልኩት
"ታድያ አስር ብር ለምን ትሰጠኛለህ?" አለኝ ግራ ተጋብቶ
'በሥድሥት ብሩ ሶስት ሲጋራ አጭስ፤ በአንድ ብሩ መናዘዣ ወረቀት ግዛ' ብዬው ላልፍ ሥል
"የቀረችውን አንድ ብርስ ምን ላርጋት?" አለኝ በጭንቀት
'ወንድ ልጅ ባዶ ኪሱን አይሞትም!' አልኩት ኮሥተር ብዬ

ከሰዓት በሁዋላ ቀፋዬ ራሡን መሥቀሉን ሠማሁ።

ዛሬ፥ በሠልሥቱ ድንኩዋን ውሥጥ ካርታ እየተጫውትኩ ሳስበው የገረመኝ ነገር በኑዛዜው ማብቂያ አካባቢ ሞቱን ሥፖንሠር ሥላደረኩለት ማመሥገኑ ነበር!
.
.
.
.
'ማነህ ... ዳኛው፣ .... እስቲ ቦነስ ጻፍልኝ!'
3.5K viewsDJ BOSS , 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ