Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidu_kidu — ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች
የሰርጥ አድራሻ: @kidu_kidu
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.93K
የሰርጥ መግለጫ

ጣፋጭ ግጥሞችን ይፈልጋሉ
ልብን የሚማርክ ደብዳቤዎችስ ማድመጥ ከፈለጉ ይቀላቀሉን
@kidu_kidu.......https://t.me/ -me8FzuCO5NmZmI0
የፍቅር ፣ የትዝታ ፣ የይቅርታ ደብዳቤዎችን ከማያልቀው ማዕዳችን ገብተው ይመገቡ፡፡
Connect Admin @Who12

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-22 00:15:27
2.5K viewsDJ BOSS , 21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:46:52
2.7K viewsDJ BOSS , 07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:45:20
2.7K viewsDJ BOSS , 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:57:09 አንጽሮተ እንስት
==============
ሴት ማለት፣
አረፍተ ነገር ሳይኖር፣ ሥርዓተ ነጥብ፣
በባዶ ወረቀት ሥር፣ እምትነበብ፣
የሁኔታ ልብወለድ፣ የጊዜ አንቀጽ፣
ትርጉም የሌላት ስህተት፣ እንዴት ብዬ ልግለጽ?!

እናትነት ግን፣
ከአንድ ትልቅ ቡልኮ ሥር፣
የተመዘዘች አንዲት ክር፣ ...
በዛች ቀዳዳ፣ በዛች ሽንቁር፣
የበረሃ ንፋስ፣ የደጋ ቁር፣
ጆሮ እንዲያደነቁር፣
ልብ እንዲያወልቅ፣
አንድ ክር ናት፣ ተቆጥራ እማታልቅ።
እናትነት።

እናትነት ማለት፣
ብዕር ወረቀት ሳይኖር፣ የተጣፈች ጥበብ፣
ሥርዓተ ነጥብ ሳይኖር፣ የምትተረክ ነቢብ፣
የልብወለድ አላባዊ፣ የመልዕክቱ ክበብ፣
እናትነት ባይኖር፣ ሕይወትን ማ'ሊያነብ?!!

እናት ሳይሆኑ ሴት፣
ኤፉድ ያለ መቀነት።
እናትነት።

ጥምጣም የሌለው ካህን፣
ምግብ የሌለው ሳህን፣
ትርጉም አለው በምስጢር፣
እናት ሳይኮን፣
የሴትነት ዓለም፣ የሴትነት ምድር።

ጽላት ሳይኖር፣ የተጣፈ ትዕዛዝ፣
ግብጽ ሳይኖር፣ የፈርዖን አገዛዝ፣
ትርጉም አለው በስውር፣
ገረድ ሳይኮን፣
መመኘት የልዕልትነትን ክብር።

ከእናትነት ጎጆ፣ ብትነቀል አንዲት ሴት፣
የጥላቻ ዝናብ፣ አይዘንብም እኛ ቤት።
የተገላቢጦሽ ሆኖ፣ ቢዘንብ እንደ ድንገት፣
እዛም እዚህም ይዘረራል፣ የፍቅር ቅል አንገት።
================
494 viewsDJ BOSS , 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:55:46 ​​ሶስት አይነት ሰዎችን አክብር

የእውቀት ባለቤቶችን
ቤተሰብህን
አዛዉንቶችን

ሶስት ነገሮች ይኑሩህ

ታማኝነት
እምነት
መልካም ስራ

ራስህን ከሶስት ነገሮች አርቅ

ሰዎችን ከመናቅ
ከማጭበርበር
ራስን የበላይ ከማድረግ

ሶስት ነገሮችን ተቆጣጠር

ምላስህን
ቁጣህን
ስሜትህን

ከሶስት ነገሮች ራስህን ጠብቅ

ከመጥፎ ስራ
ሰዎችን ከማማት
ከምቀኝነት

ሶስት ነገሮችን ፈልግ

እዉቀትን
ጥሩ ስነምግባርን
ታዛዥነትን

ሶስት ነገሮችን ንጹህ አድርግ

ሰዉነትህን
ልብስህን
ንግግርህን

ሶስት ነገሮችን አስታዉስ

ሞትን
ሰዎች የዋሉልህን ዉለታ
ሰዎች የሰጡህን ምክር

ሶስት ነገሮችን አትርሳ

ቃልህን
እምነትህን
ስራህን

ሶስት ነገሮችን ተቆጠብ

ከጓደኛህ ብድር
ከውሸት
ከአሉባልታ
443 viewsDJ BOSS , 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:52:01 .
.
.
.
ስሜት ሲታመስ
ሲያስተጋባ ዝምታ
ምን ሆኜ ነው ልበል
አፌን በምን ልፍታ
ያመኛል......
ደግሞ አንዳች ጥሞ
እልፍ ይርበኛል
አታውቅም........
የእኔ እንጥልጥል ፍርጥ
የጉጉት ስስቴ
ቃልም ማይወጣለት
የመውደድ ቅጣቴ
አንተን አንተን ብሎ
ምልሰቱ የኦና
አሁንም ዝም ነው
ዝም ነው ሚያቀና
ምክንያቱም.......
በታፈነ ልሳን
ፍቅር ይተረካል
ቃላት ልጉም ናቸው
ከከንፈር ይደርቃል
አታውቅም..........
ስሜት በዝምታ
ከሁሉ ይልቃል
.
.
.
.
ፍቅር ያሸንፋል
492 viewsDJ BOSS , 15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 23:00:37 ​​ላትጨርሰው ነገር ፍቅርን ጀምረክ
የመሀላ ቃሉን ሁሉንም እረስተክ
መለዬትን ወሰንክ መራቅን ፈልገክ

ሂድ ተመላለስ ድረስ ካሰብክበት
ድሮም መንገደኛ አይቆምም ባለበት
ወደድኩሽ ሞትኩልሽ ማለቱም ይቅርበት
የሰጠከኝ ፍቅር ይኑር እንደዘበት
አንተም ከእኔ እራቅ እኔም ልቻልበት
​​
...........
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
1.7K viewsDJ BOSS , 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 22:59:43 የማያሽር...ጠባሳ
፨።።። ።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።።።
1.6K viewsDJ BOSS , 19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:38:25 ድሀ 'ናት'

በአፈር አቧራ የታጠበ ገላ
ተጠቅልሎ በነተበ ነጠላ
ጥለቱ የዛ የነጠላው
ተለይቶ ከሸማው
ተቀዳዶ ተነጥሎ ከመሬት
ከሷ በታች መጎተትን ሲመርጥ
............. ከሷነት

............ ከሰውነት

ያ ጠይም ፊት ደግሞ
ያ ደምግባት ደግሞ
በሰው ሀሜት ደክሞ
ዝሎ ተቆላሞ
ፊት አያርገኝ ብሎ
ለሷው ጀርባ ሰጧል
ፊቷ እንኳን እንደ ሰው
እሷን ፊት ነስቷታል
መሳቅ እንኳን ቀርቶ
ማዘን ቅጡን አጧል
... ሀሩ ፀጉሯ አዝኖላት
ከቀትርም ሊያድናት
ተደፍቷል ወደፊት
እሷ ያው ድሀ ናት ....
የአቤል ቃየል እናት
ድህነት በቁሟ አላምጦ የጣላት
ደሃ ?

ድሃ ናት ?

ደሃ እናት ?

ወይስ የድሃ ናት ?

ንፏጎች ይላሉ ይች ሴት ድሀ ናት
ድሀ የምትበላ ጾሟን ምታድር
ድሀ የምትዘጋ የድህነቷን በር
'እጅ የምትዘረጋ' መሬት የምትቧጭር
...... ድሃ ናት

የምትበላው የላት
ግን የጨቅላ ብዛት
እየተባባሉ እየተሳለቁ
በሷው ርቀቃ እየተራቀቁ
በልተው የጣሉትን የስንዴ ገለባ
ተዘርቶ ማይበቅል የእህሉን ላባ
ለሷው ይልካሉ
ማዳበሪያ አገልግል መቋጠር ያውቃሉ
እሷም እጅ ስማ ገለባውን ቆልታ
ቀቅላ አራርሳ
ከዛች እንጀራ ጎን 'ለጨቅሎቿ' አጉርሳ
ለሷስ ?
ለሷማ አይተርፋትም ካለም ጠርጋ አብሳ ድሃ ናት ....
ለስንዴ ገለባ ውለታ ሚይዛት
መካንነታቸው የሚጠዘጥዛት
ጉዲፈቻ ሲባል ጉዲፈቻ ብላ
ገለቱማ አክላ ...
ያሏትን ጥሪቶች ለነሱው አድላ
የምትኖር ድሃ ናት
ድሃ እናት እንዲህ ናት
ድሀ እንድትሰደድ
ቁማ እንዳትራመድ
'የአራስነት' ክብሯ በሾህ አጋም ሲነድ
ድሀ ልጆች ወልዳ ድሀ የምንላት
በጦር በረሃቡ ስሟን የሚያገኑት
. . .
ሌላ ማንም ሳትሆን
የኔ ድሀ እናት ናት
የኛ ድሀ እንበል
ለኔ ድሀ ነው በል
አሁንም ደጋግመህ
ማን ድሀ እንደሆነ እስኪገለጽልህ .......

1.8K viewsDJ BOSS , 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:37:29
1.3K viewsDJ BOSS , 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ