በቴሌግራም ቴራባይት የብልግና ምስሎችን ያግኙ »

የፍቅር ታሪክ 🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @yefkrtarik
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.18K
የሰርጥ መግለጫ

🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹
➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1
Since 2011 E.C.

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-26 21:00:50 ‍ ​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

            ክፍል ❿



መኪና ውስጥ ገብተን ጉዞ ቀጠልን...በድንገት ጆን ቆይ አንተስ ለምን ፍቅረኛ አትይዝም የሚል ጥያቄ ጠየቀችኝ
ባክሽ ፍቅር ለኔ ጭንቀት ነው በዛ ላይ ፍቅረኛ ለመፈለግ ጊዜ የለኝም አልኳት ላንተ ጊዜ ከሌለህ እኔ እፈልጋለሁ ግን ምን አይነት ሴት ትሁንህ ስትለኝ ከአፌ እንዴት እንደወጣ አላውቅም ልክ እንዳቺ  አይነቷን አልኳት ኧረ ጆን ታድያ አንተ የምትፈልገው ፍቅረኛ ሳይሆን እህት ነዋ
እህት እኔ አለሁ አይደል ነው ወይስ ሁለተኛ እህት ነው የምትፈልገው አለችኝ
አንቺ ደሞ ፍቅረኛ ማለት ያለው እህትም እናትም ማለት አይደል አልኳት
ተው ግን ጆን በቃ ፍቅረኛ ካገኘህ እኔን አትፈልግም ማለት ነዋ አለችኝ
እንዴ መቅዲ ለምን እንደዛ ትያለሽ ብዬ ስጠይቅ
ፍቅረኛ እህትም መሆን የምትችል ከሆነ በቃ አንተን አጣሁ ማለት እኮ ነው እንደውም ፍቅረኛ አልፈልግም እኔው ራሴ ነኝ ላንተ እናትም ፍቅረኛም እህትም የምሆነው ብላ መሳቅ ጀመረች ባክሽ ወደዛ ሂጅ አንቺን ሚስት አድርጎ ማን እየተቃጠለ ይኖራል አንቺ ማለት እኮ ፍየል ነሽ ፍየል መጠበቅ ከባድ ነው እኔም በተራ መሳቅ ጀመርኩኝ
እንደውም ተው እኔም አልፈልግም እሺ አንተ እኮ ውሸታም ዱርዬ ነህ እኔ ደሞ ውሸታም ሰው እንዴት እንደምጠላ ታውቃለህ አይደል ስትለኝ በድንጋጤ ክው አልኩኝ፣

  አንተ ጆን ምነው ዝም አልክ እኔ እኮ ለቀልድ ነው አቦ ፈታ በል በቃ ግን ቆይ ጆን ለደስታ ምን ልንለው ነው፣ እኔ ምን እላለሁ እናንተ የምታወሩትን እናንተው እወቁ እንጂ ሁለታችውም ፍየሎች አይደላችሁም አልኳት
ተው ግን ጆን እኔ ላንተ ጊዜ እንዲህ ነኝ? በእናትህ ንገረኝ ስትለኝ በቃ የኔ ፍቅር እወድሃለሁ በይው አልኳት
ምን? አይደለም ለእሱ ላንተም ቢሆን እንደዚህ አልልም እሺ ከፈለገ እሱ ይበለኝ ሆሆሆ ሲጀምር እኔ የምወደው ግጥሙን እንጂ እሱን አይደለም እሱ እኮ የሆነ እንከፍ ነገር ስትለኝ ሳቄን መቆጣጠር አቅቶኝ ሳቄን ለቀቅኩት

እእእእእ ምን ትስቃለህ? ባክህ መኪናውን አሁን እቁም ደርሰናል እኮ ስትለኛ ብለሽ ብለሽ አሁን መኪና እንዴት እንደማቆም ሁሉ መናገር ጀመርሽ ከዚህ ሁሉ ለምን ራስሽ አትይዥውም አልኳት
አንተ ምርጥ ሃሳብ ነው እንደውም ከዛሬ ጀምረህ መኪና ታስለምደኛለህ አለችኝ
አንቺን  አምኖ መኪና ማን ይሰጣል አንቺ ማለት እኮ እብድ ነሽ አልኳት
ጆን ነው አይደል እንደውም አሁን እቤት መመለስ እፈልጋለሁ ቤት መልሰኝ ስትለኝ እሺ ይቅርታ አሁን አድርግ ያልሽውን ሁሉ አደርጋለሁ አልኳት እንደዛ አትልም ታድያ በቃ ውረድ ብላኝ አብረን ከመኪና ወርደን ሱቅ ገባን....
ደስታ እውነትም ደስ ብሎታል
ለነገሩ እንደዚህች አይነት ውብ ንግስት በስጦታ መልክ ሰጥቼው ደስ ቢለው ምን ይገርማል?
መቅዲ ግን ጭር ያለች ትመስላለች


.....ለነገሩ እንደዚህች አይነት ውብ ንግስት በስጦታ መልካም ሰጥቼ ደስ ቢል ምኑ ይገርማል፣
መቅዲ ግን ጭር ያላት ትመስላለች...
በነገራችን ላይ የሱን ሱቅ የሄድነው ለእቃ አይደለም ዛሬ ምሽቱን ዘና ፈታ ለማለት ቀጠሮ ይዘናል ለደስታ ደግሞ መኪና የለውም ስለዚህ እርሱንም ይዘን እንሄዳለን ብለን ነው ስራ ቦታው የሄድነው

ትንሽ ራቅ ብሎ ለኔ ስልክ ደውለው  አንተ ምን አይነቱ ጅል ነህ የእውነትም ሱቅ ይዘህ ትመጣለህ? ባክህ አንድነት ሆቴል ይዘሀት ና ወንድ ልጅ ቀጠሮ ቦታ ቀድሞ ነው መገኘት ያለበት ለነገሩ አንተ ስለ ፍቅር ምን ታውቃለህ በል ፈጠን በል ብሎ ስልኩን ዘጋው
ቀድሞ ከበቀለው ጆሮ በኋላ የሚበቅለው ቀንድ ይሉታል ይኼ ነው
እኔ መኪና ውስጥ ከመቅዲ ጋር ስለሆንኩ ምንም መልስ አልሰጠውትም በውስጤ ለብቻዬ እየሳቅኩኝ ወደ አንድነት ሆቴል ጉዞ ቀጠለን...

    ፖፖፖ ዛሬ እንዴት አባቱ ሽክ ብሏል!
አይይይ ደስታ ቆይ የግብዣ ልምምድ እያደረክ ነበረ እንዴ እያልኩ በልቤ ብቻዬን እስቃለሁ እሱ ለራሱ ዛሬ የምግብ ምርጫ በኔ ነው እናንተ መምረጥ አትችሉም ብሎ አስተናጋጅ ጠርቶ ምግብ አዘዘ
በአንድ ልቤ እኛ የኢትዮ ወንዶች እኮ ምግቡን ራሳችን የምንመርጠው በምክንያት ነው ግፍ የማያውቁ የሀገራችን ሴቶች አይደለም ኪስ ውስጥ ይዘን የመጣነው ብር ደሞዛችን ራሱ የማይችለውን ምግብ ቢያዙ ጉድ ከምንሆን ብለን እንጂ
ለነገሩ ደስታ የብር ችግር የለበትም ግን ምርጫ በእኔ ነው ሲል የኔን ቁስል የነካው ስለመሰለኝ ነው፣

     ለማንኛውም ይምጣ እስኪ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩኝ...
ስሙ ምን እንደሆነ የማላውቅ ምግብ መጣ
ለነገሩ የእነዚህን ምግብ ሁሉ ስም ባውቅ ትልቅ እውቀት አለኝ ማለት አይደል!
እንብላ እንብላ ሲለን እሺ እሺ ብለን ልክ መብላት ስንጀምር. መቅዲ ቁጭ ካለችበት ብድግ ስትል ምን እየሆነች ነው ብዬ ቀና ስል ለካ በእጇ ላይ ምግብ ይዛለች እሰይ ድፍረት እንደዚህ ነው ለደስታ ልታጎርሰው ነው ብዬ ስጠብቅ ጆን ተቀበል ተቀብል ስትለኝ በአንድ ልቤ ደስ ብሎኝ ግን ደሞ ጉርሻው ለእሱ ይገባ ነበረ እያልኩ ግን እምቢ ማለት ስለማልችል ተቀበልኩኝ
እንግዲህ ብድር መመለስ ግድ ነው ብዬ እኔም አንስቼ አጎርስኳት፤
ቆይ ግን ጋበዡ ማነው
በሰው ግብዣ እኛ ጭራሽ ጥንዶች ሆነን ቁጭ አለን

    ደስታ ግን እንዴት አባቱ ቅጥል ብሎ ይሁን?....
ለነገሩ  እሱ እኔን በምንም መልኩ በዚህ ይጠራጠራል የሚል እምነት የለኝም፣
ምግቡን በልታን አሁን ለመቀውጥ ሦስታችንም ወደ መጠጥ ቤት ሄደን...
ለኔ ቤቱ አዲስ ነው
እኔ ሰፈር ውስጥ ጠላ ቤት ምናምን ነው እንጂ እንደዚህ ናይት ክለብ ገብቼ አላውቅም፣
ለመቅዲም ቤቱ አዲስ ነው ስለ ደስታ ግን የማውቀው ነገር የለም!
አንድ ጥግ ላይ ቁጭ ብለን መጠጣት ቀጠልን...
ናይት ክለብ ገብቼ አላውቅም ግን በፊትም በአንድ አንድ አጋጣሚ ጠጥቼ አውቃለሁ ለመቅዲ ግን አዲስ ሳይሆን አይቀርም
እሷ ገና በሙዚቃው ነው መስከር የጀመረችው....
መጠጥ ቤት ግማሹ ሰው ለመዝናናት ይሄዳል፣
ግማሹ ሰው የትኛውንም ቁስል ለመርሳት ይሄዳል፣
ግማሹ ሰው ደሞ ለጥያቄዎች መልስ መመለስ ሲያቅታቸው መጠጥ መፍትሄ የሚሰጣቸው መስሏቸው ይሄዳሉ፣
ብቻ ሁሉም ሰው የራሱን ምክንያት ይዞ ይሄዳል፤
መጠጥ ቤት ገብቶ መጠጣት ሲጀምር ግን ሁሉም ሰው መጀመሪያ አስቦ የሄደውን ነገር አያደርግም።
ለመዝናናት የሄደው ሰው ጭራሽ ለጥላቻ የሄደ ሰው መስሎ ቁጭ ይላል፣
ቁስሉን ለመርሳት የሄደው ሰው ጭራሽ ቁስል ተነክቶበት እብድ ሆኖ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል፣

.እኔን ብቻ ነው ግን መጠጥ ግራ የሚያገባኝ? ማለቴ ለኔ ብቻ ነው የመጠጥ የትኛውም አይነት ጥቅም የማይታየኝ?
የሆነ ሁሉ ይሁን ጥቅሙ ምን እንደሆነ ባለውቅም እኔም ጭልጥ ጭልጥ እያደረኩት ነው
እብዶች ብቻ በሞሉበት ጭስ እና አረቄ ተደምሮ እኔንም ሞቅ ሞቅ ማድረግ ጀምሯል


ክፍል አስራ አንድ እሁድ ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk

      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
5.2K views , 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 21:00:04 ‍ ​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ የቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ


             ክፍል ❾

promise ብለሽኛል ሌላ ነገር አልፈልግም አልኳት
ምን መሰለህ ጆን...ወሬው ላንተ ምንም አይጠቅምም ስትለኝ
ይጠቅማል እንጂ ማወቅ አለብኝ አልኳት እንደዛ ነው? በቃ ፍቅር ይዞኛል ብላ ማልቀስ ጀመረች
ዘንድሮ እኮ አልቃሽ በዝቶ ተቸገርን
ፍቅር የያዘው ሰው ማልቀስ ነው
ሚስት ያገባ ወንድ ማልቀስ ነው
ትዳር የያዘች ሴት ማልቀስ ነው
ትዳር ያጣች ሴት ማልቀስ ነው
  አሁንማ ሰው ለደስታ ብሎ እስከ አፍንጫው ጠጥቶ ሁሉ ማልቀስ ጀምሯል አንቺ በይ ወደዛ ሂጅ አትነፋረቂብኝ የወደደ ሰው መውደድ የሚችል ልብ ስላለው ደስ ማለት ነው እንጂ ያለበት  ምን የሚሉት ለቅሶ ነው?
ተይ ግን አንቺ ልጅ ቀልብ ግዥ በትንሽ በትልቁ አታልቅሽ ስላት አንተ ምን አለብህ በውስጤ ያለውን እሳት እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው ስትለኝ
ውስጥሽ ያለው እሳት ከሆነ ያንቺን እሳት ለማጥፋት ልብሽ ውስጥ የሚገባ ማንም አይኖርም ባይሆን በእሳቱ ቦታ  ወተት ምናምን ቢኖር ከኑሮ ውድነት ሸሽቶም ቢሆን ብዙ ሰው ይገባ ነበረ ብዬ መሳቅ ቀጠልኩኝ ጥርሳም ነህ እሺ
የኔ ልብ የወተት መደብር መሰለህ እንዴ ማንም ሰው ገብቶ ገዝቶ የሚወጣው እኔ ነኝ እንጂ ቁም ነገር አለህ ብዬ የልቤን ስሜት የምናግረው ስትለኝ
ውይይይ መቅዲ አንቺ እና ቴሌ ደሞ ቀልድ አታውቁም      ሁሉንም ነገር መቁጠር ስትወዱ በቃ እሺ ይቅርታ ከማነው ፍቅር የያዘሽ? ከባለሱቁ ደስታ ነው አይደል አልኳት
ባክህ ከእሱ አይደለም አለችኝ
ምን
ታድያ ከማን ሊሆን ይችላል አልኳት?
ከፌስቡክ ጓደኛዬ ደስታ ነዋ ስትለኝ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ አንቺ እሱ እኮ ደስታ አይደለም ምን እያልሽ ነው አልኳት
ምን? ምን እያልክ እንደሆነ አንተ ንገረኝ እንጂ ታድያ ደስታ ካልሆነ ማነው ስትለኝ
የቱ? ማን? ብዬ ድንብርብር ማለት ቀጠልኩኝ ጆን ምን ሆነካል? የፌስቡክ ጓደኛዬ ማነው ብላ በድጋሚ መጠየቅ ጀመረች
እኔም መልሼ የትኛው የፌስቡክ ጓደኛሽ አልኳት
ልጁ ጤና የለውም እንዴ ሆሆሆ በቃ እንደውም ተው ባለሱቁ ደስታ ራሱ ነው መሰለኝ ስትል መቅዲ እኔ እኮ ብዬሽ ነበረ ደስታ ማለት እኮ በቃ ሁለት ሰው ነው አልኳት
የምን ሁለት ሰው ስትለኝ
አይ እሱማ ያው አንድ ሰው ነው እኔ እኮ በፊትም ብዬሻለሁ ደስታ ሴት በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ሴቶች እፊት ለፊቱ ሲሆኑ ምን እንደሚያወራ ራሱ አያውቅም ችግሩ በቃ ይኼ ብቻ ነው እንጂ እሱም እኮ ይወድሻል አልኳት
እርግጠኛ ነህ ጆን ስትለኝ አዎ መቅዲ አልኳት
እንደዛ ከሆነ እንደምወደው እነግረዋለሁ በቃ የምን ጭንቀት ነው ስትለኝ ዋውውው መቅዲ ምርጥ ሃሳብ እንደውም ዛሬ እንሂድ አልኳት እሺ ግን አሁን አይደለም ከሰአት በኋላ እንሄዳለን አለችኝ እኔ ደስ ብሎኝ እሺ አልኳት
ሰአቱ እየቀረበ ሲመጣ መቅዲን ይዤ እሄዳለሁ ባልኩት ነገር ልቤ ቅር ተሰኝቶ ነው መሰለኝ መሄድ በጣም አስጠላኝ ልብስ ምናምን ቀይር እንሂድ ጆን ስትለኝ ድብርት ድብርት አለኝ ደሞ በጣም አምሮባታል
እንሂድ እንዴ አልኳት
እንደ አዲስ ጥያቄ ትጠይቀኛለህ እንዴ ቶሎ በል እንሂድ አለችኝ
ደስ ባይለኝም መኪና ውስጥ ገብተን ጉዞ ቀጠልን.....


ክፍል አስር አርብ   ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
5.2K views , 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 19:25:48 ‍ ​​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በ የፍቅር ታሪክ የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

                           ክፍል

እሷ ግን አሁንም ማልቀስ አላቆመችም ቆይ ግን ችግሯ ምንድነው?
መቅዲ በእናትሽ በጭንቀት መሞቴ ነው የሆንሽውን ነገር ንገሪኝ አልኳት
ጆን በቃ ቤት እንሂድ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መኪና ውስጥ ገባች
እኔም ዝም ብዬ መኪና ውስጥ ገብቼ ወደ ቤት መጣን....
ቤት እንደገባች በፍጥነት ወደ ክፍሏ ገብታ በሩን ዘጋች፣
መቅዲ እንደዚህ ስትሆን የመጀመርያ ነው
የሆነ አዲስ ነገር መኖሩ ግልጽ ነው፤ ግን ምን ሊሆን ይችላል? ቆይ ውሸቴን ሰምታ ይሁን?
እንደሱ ቢሆን ነው እኔንም ዘግታ ብቻዋን መሆን የመረጠችው?
ቆይ ቆይ እንደዛ ብሆን በዝምታ ብቻ ማለፍ ትችላለች? ኖ በፍጹም አትችልም በዝምታ ማለፍ የምትችል ቢሆንማ ዛሬውኑ እውነቱን አፍርጬ እርፍ አልልም ነበረ!
ለማንኛውም ለሁሉም ነገር ጊዜ መስጠት  ያስፈልጋል
ውሃ ራሱ ድፍርስ ሲል ሰአት ስሰጡት እኮ ቆሻሸው ለብቻው ንጹህ የሆነ ውሃ ደሞ ለብቻው ይሆናል፤
የሰውም ስሜት እንደዛ ሲሆን ትንሽ ጊዜ መስጠት ከምንም በላይ ጠቃሚ ነው።
እዛው በር አጠገብ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ስለ መቅዲ ማሰብ ጀመርኩኝ
መቅዲ ትንሽ ከቆየች በኋላ ከክፍሏ ስትወጣ እኔ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ በሃሳብ ግን ህንድ ውቅያኖስ በመርከብ በማቋረጥ ላይ ነኝ

ሃሳብ እኮ ግፍ አያውቅም አንድ አንድ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ በልቶ ሀገሩ በደስታ ሲዋጥ አንተም በዚያን ጊዜ ተጫዋች እንደነበርክ ሁሉ አድርገው አምጥቶ ፊትህ ላይ ድቅን ያደርገዋል
በዚያን ቀን ብራዚል ላይ ሃትሪክ የሠራክ ሁሉ ሊመስልክ ይችላል
ከሃሳብ መርከብ ወረድ ስትል ነው ባህር ውስጥ ሳትሆን ደረቅ መሬት ላይ እንደሆንክ የሚታውቀው፣
እኔም እኮ በዚህ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ እኔ እና መቅዲ ፍቅረኛሞች ሆነን ልጅ ምናምን ቢኖረን እያልኩ ነበረ
እንደውም የልጁን መልክ ራሱ የማውቀው ይመስለኛል
መቅዲ በበር ጭንቅላቴን ባትለው ቆይ በሃሳብ መርከብ የት ልደርስ ነበረ
አንቺ መቅዲ ወይኔ ጭንቅላቴ ስል እሷም ተደናግጣ አይዞህ እሺ ጆን እኔን ይምታኝ ሲጀምር ቆይ እዚህ በር ስር ምን ትሠራለህ ለዛውም መሬት ላይ፣
ደሞ እንቅልፍ ወስዶህ ነበረ እንዴ በር ስከፍት እንኳን አትነሳም እያለች ጭንቅላቴን በእጇ ማሸት ጀመረች
የሷ እጅ ጭንቅላቴ ላይ አይደል ያለው? ቆይ ምንድነው ልቤን እንደዚህ ደስ ደስ አለው
ህመሙ ትቶኛል ግን ዝም አልኩኝ እጇን ከጭንቅላቴ ላይ ታነሳዋለች ብዬ ይበልጥ እእእእ ወይኔ ጭንቅላቴ ወይኔ ጭንቅላቴ እያልኩ ጎንበስ ብዬ ቀስ አልኩና ትንሽ ምራቅ ከአፌ በእጄ አምጥቼ አይኔ ላይ ቀብቼ ማልቀስ ቀጠልኩኝ
የኔ ምስኪን የእውነቴን መስሏት ጆን አይዞህ ጆን ይቅርታ እያለችኝ ነው፣ አሁን ጥሩ ሃሳብ መጣልኝ ቆይ ቅድም እሷ ያለቀሰችበትን ምክንያት ለምን ይኼን አጋጣሚ ተጠቅሜ እላውቅም ብዬ መቅዲ ዞር በይ እንደውም ያንቺን እርዳታ አልፈልግም አልኳት
ምን እያልክ ነው ጆን ጭንቅላትህ እኮ አብጧል ቆይ ትንሽ ልሸው ስትል በቃ አልፈልግም አንቺ ምን ስለሆንሽ ነው እኔ ስጎዳ እኔን ለመርዳት የመጣሽው? ቅድም አንቺ አልቅሰሽ አይዞሽ ሲል አይደል ክፍልሽ ገብተሽ በር የዘጋሺው አልኳት
ጆን እሱ እኮ ሌላ ጉዳይ ነው ይኼ ደሞ ህመም እስቲ ቆይ ስትለኝ
አልፈልግም አልኩሽ እኮ በቃ ዞር በይ አልኳት
እሺ እኔም የሆንኩትን እናግራለሁ ግን በመጀመርያ ጭንቅላትህን ልሸው ስትል ኖ መጀመርያ ቃል ግቢልኝ አልኳት ከአንተ ይነጥለኝ እነግርሃለሁ አለችኝ
ህመሜ የውሸት እንደሆነ እንደታውቅ  ትንሽ ዝም አልኳትና መቅዲ እጅሽ እኮ መድኃኒት ነው ዳንኩኝ እኮ አልኳት
አየህ የኔ እጅ እንደዚህ ነው ስትለኝ እንኳንም የኔ ሆንሽ አሁን የቅድሙን ምስጢር አልኳት
ጆን እሱ ላንተ  ምን ያደርጋል ስትለኝ Promise ብለሽኛል ሌላ ነገር አልፈልግም አልኳት
ጆን ምን መሰለህ....

ክፍል ዘጠኝ ማክሰኞ ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
5.4K views , 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 20:54:56 ‍ ​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

          ክፍል

እኔ ግን እስከአሁንም በመቅዲ የጨረቃ ምሳሌ እንደተመሰጥኩ ነው ግን እኮ አንድም ቀን መቅዲ እንደዚህ አስተዋይ ናት ብዬ አስቤ አላውቅም ነበረ
ሞኝ የሚመስሉ ሰዎች ልባቸው እንቁ ነው፤
ልባቸው ውስጥ ከፍቅር ከገርነት ውጭ ተንኮል ሆነ ጥላቻ አይኖርም!
የዋሀ ሰዎች የፍቅር ተምሳሌት አይመስሉም? ኩራት አያውቁም ትዕቢት አያውቁም በኔ ላይ እየሳቁ ነው ብለው አይጨነቁም አንተ እነሱ ላይ ስትስቅ አብረው ይስቃሉ የዋሀ ሰዎች የፍቅር ተምሳሌት መሆናቸውን ያወኩት በመቅዲ ነው የመቅዲን ስሜት ሳጠና መቅዲ ከደስታ ጋር ስትሆን ብዙም ደስ አይላትም ቤት መጥታ በፌስቡክ ግጥም ማንበብ ስትጀምር ግን የት እንደሆነች ሁሉ አታውቅም

አንድ አንድ ጊዜ   ቤት ውስጥ እናቷ እና አባቷ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን እየተመለከቱ መቅዲ ፌስቡክ ውስጥ ገብታ ደስታ በእናትህ አንድ ግጥም ላክልኝ ትላለች እምቢ ማለት ችግር ስለሆነ አንድ ግጥም እልክላታለሁ መቅዲ በድንገት የስስስ የስስስ ብላ ቁጭ ካለችበት ብድግ ትልና ይቅርታ ብላ እንደገና ቁጭ ትላለች
እኔም በሆነ ነገር ምክንያት አድርጌ ሳቄን ለቅቄ እርፍ እላለሁ በነገራችን ላይ እኔ የመቅዲ ሹፌር ብቻ አይደለሁም ጋርድ ጭምር እንጂ
ማነው ቀጭን ሰው ጋርድ አይሆንም ያላችሁ? የትም ስትሄድ ብቻዋን መሄድ አትወድም አብረን ነው የምንሄደው፤
ደስታን ፍቅር ወጥሮ ይዞታል መሰለኝ ቀጠሮ ቀጠሮ አብዝቷል አሁንማ ቋንቋ ቻልኩ ብሎ አንተ ምንድነው ጭራሽ ፍቅረኛ መሰልክ እኮ አንድ አንድ ጊዜ ነጻነት ስጠን እንጂ እያለ በአሽሙር ላጥ እያደረገ ነው
እኛ ኢትዮጵያውያን በአሽሙር ምላጭ እኮ ነን
መቅዲ ደሞ ከእኔ ተለይታ መሄድ አትፈልግም አብሬ እሄድና እነሱ አብረው እንዲቀመጡ እኔ የሆነ ምክንያት ፍጥሬ ከቦታው ላሽ እላለሁ።
ለምንድነው አጠገቤ ስትሆን ለመቅዲ  ምንም  ስሜት የሌለኝ ለትንሽ ሰአታት ከአጠገቤ ስትጠፋ ለአንድ ሳምንት የራቀችኝ የሚመስለኝ?
ስሜታችሁ እንደ ሐምሌ ወራጅ ወንዝ ድፍርስ ሲልባችሁ ከየትኛውም ውሳኔ በፊት ለጊዜው ከቦታው መራቅ ምርጥ መፍትሔ ይመስለኛል
መቅዲ ስልኬን በተደጋጋሚ መያዝ ስትጀምር እውነቱን በአንድ አጋጣሚ ልታውቅ ትችላለች ብዬ ደስታ በሚለው ስም የከፈትኩትን የፌስቡክ አካውንት ለደስታ ሰጥቼ ከስልኬ Remove አደረኩት
በመጀመሪያው ቀን በጣም ደስ አለኝ
እንዴት ደስ ይላል ደስ እንዳላቸው ይሁኑ ግልግል ነው ግጥሙን እኔ ለደስታ እልካለሁ ብዬ ዘና አልኩኝ
በሁለተኛው ቀን ከመቅድ ይመጡ የነበሩ መልእክቶች ሁሉ ቆሙ
እእእእእ ትንሽ ቅር ብሎኛል
በሦስተኛው ቀን ለምን ሰጠሁት ማለት ቀጠልኩኝ
በድንገት ከሌላ ሰው ሚሴጅ ሲመጣ የመቅዲ መስሎኝ በደስታ ፍንጥዝ ብዬ ውስጥ ስገባ የሌላ ሰው ይሆናል
ቆይ ግን ምን አይነት እብደት ነው?
እሷ አጠገቤ ቁጭ ብላ እያለች የሷን ሚሴጅ መጠበቅ ምን የሚሉት ነው
አንድ ቀን ከት/ቤት እየመጣን እኔ መኪና ውስጥ ሙዚቃ ከፊቼ በሙዚቃው ተመስጫለሁ መቅዲ ከትከሻዬ ላይ መቼ እንቅልፍ ለጥ እንዳለች ሁሉ አላውቅም
ሙዚቃው አልቆ ወደ መቅዲ ዞር ስል እሷ ለራሷ ምቹ እንቅልፍ ላይ ናት ሰውነቷ በጣም ይሞቃል ራስ ምታት ነው መሰለኝ  ሰውነቷ በጣም እየሞቀ ነው
እንቅልፍ ላይ ስለሆነች ዝም አልኩኝ ትንሽ ቦታ እንደሄደን ከእንቅልፍ ተነሳች...
መቅዲ ምን ሆነሽ ነው ሰውነትሽ እኮ በጣም ይሞቃል አልኳት
ምንም አልሆንኩም ጆን አለችኝ
መቅዲ እሺ ቆይ ከእኔም ነገር መደበቅ ጀመርሽ አልኳት
ጆን እኔ እኮ ለመደበቅ ፈልጌ አይደለም ብላ ማልቀስ ጀመረች
እንዴ አንቺ ምንድነው የሆንሽው ብዬ መኪናውን ወደ ጥግ አውጥቼ አቆምኩኝና እምባዋን  መጥረግ ቀጠልኩኝ...
እሷ ግን አሁንም ማልቀስ አላቆመችም
ቆይ ችግሯ ምንድነው?

ክፍል ስምንት አርብ ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik
    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
6.3K views , 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 22:09:28 ‍ ​​​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

           ክፍል ❻

መፍትሄው ምን ይሁን እያልኩ ጭንቅ ውስጥ ገባሁ
ዬስስስ አንድ ሃሳብ መጣልኝ...
በነገራችን ላይ እንደ ውሸት ሰውን እንቅልፍ የሚነሳ ነገር የውስጥን ሰላም የሚያደፍርስ ነገር የለም!
Especially የቅርብ የሆነውን ሰው ሁሌም እየዋሹ መኖር  በጣም ከባድ ነገር ነው፤
የሰው ልጅ ትልቁ ስህተት ማለት ስህተት መስራቱ ብቻ ሳይሆን የሰራውን ስህተት ለመሸፈን ሲል ሌላ ስህተቶችን ጨምሮ ጨማምሮ መስራቱ ነው።
 
እኔም ለስህተቴ መፍትሄ እንደ አማራጭ መጠቀም የፍለኩት ራሱን ስህተት ነው በጊዜው እውነቱን  ለመቅዲ መናገር እሷን የሚጎዳት መስሎኝ ስለነበረ ለደስታ መሆን የማይችለውን ነገር ትችላለህ ብዬ ግጥም በድብቅ በስልክ እና በተግባር ማስለመድ ቀጠልኩኝ... በዚህ አለም ላይ መሆን የማይችሉትን ነገር ለሌሎች ሁኑ ብሎ እንደማስለመድ ሆነ ለመሆን እንደመሞከር የሚከብድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመሆን ስትሞክር  ሁሉ ነገር አስቂኝ ይሆናል በራስህ እንኳን መተማመን አትችልም ሁሌም ሰው ምን ይለኝ ይሁን ትክክል ነኝ ወይስ አይደለሁም የሚል ጥያቄ ታበዛለህ የምትከተለው ሰውን ስለሆነ በራስህ እርግጠኛ መሆን አትችልም።
እኔም ደስታ የማይችለውን ግጥም በግድ እንዲችል ለማድረግ መሞከር ትርፉ በራሴ ሰአት እና በደስታ ሞራል ላይ መጫወት ነው እንጂ ትክክለኛ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፤
ለጊዜው ግን ይሆናል ብዬ ነበረ ያሰብኩት እናም ጨወታው ቀጠለ....መቅዲ እንግዲህ ደስታ ለግጥም በጣም ጎበዝ እንደሆነ ነው የምታውቀው እውነታው ግን ደስታ ስለ ግጥም ምንም ስጦታ ሆነ እውቀት የላትም
መቅድን ሁሌም ት/ቤት ስወስዳት ደስ የሚል ስሜት ይሰማኛል ምክንያቱ ደሞ መቅዲ በቃ አሪፍ ልጅ ናት ሁሌም አዝናኝ ሳቂታ ነገር ነች የትኛውም ቦታ ላይ ይሁን በየትኛውም ሁኔታ የኔን ስሜት ለመጠበቅ የማትሆን ነገር የለም!
በደስታዬ ደስ ይላታል
በሌሎች ደስታ ደስታን ማግኘት ግን ምነኛ ታድሎት ነው!?
በሌላ ሰው ደስታ ደስ የሚል ሰው ውስጡ ሰላም የሆነ ውስጡ ላይ ችግር የሌላ ሰው ከቅናት ነጻ የሆነ ሰው ነው በሌሎች ደስታ ደስታን ማገኘት የሚችል ሰው ሲሆን ይህ ሰው ደሞ በህይወት ዘመኑ ሁሌም ደስተኛ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ አለም ላይ የሰዎችን ደስታ ከሚቀሙ ነገሮች አንዱ እና የመጀመሪያው ሌላ ሰዎችን እያዩ መቅናት ነው በሌላ ሰው ደስታ አብረው ደስ የሚል ሰው ከዚህ ችግር ነጻ ነው
እኔም እኮ የመቅዲን ደስታ እፈልጋለሁ መቅዲ ሁሌም ብትስቅ ደስ ይለኛል እንደውም የመቅዲን ጉዳት ማየት ስለማልፈልግ ነው ለደስታ ግጥም ማስተማር የጀመርኩት...
መቅዲ ደስታን በጣም ማቅረብ ጀምራለች ደስታም ቢሆን ከበፊቱ ቋንቋም ሆነ አነጋገር ተሻሽሏል የግጥሙ ነገር ግን አሁንም ትልቁ ጭንቅ ነው
ለደስታ ግጥም ማስተማር ለአንደኛ ክፍል ልጅ የአምስተኛ ክፍል ትምህርት ለማስረዳት እንደመሞከር ነው ቤት ውስጥ ስልኬን ልክ እንደ አይን ብሌኔ ነው የምጠብቀው ምክንያቱም እዚህ ስልክ ውስጥ ከእኔ እና ከደስታ ውጪ ሌላ ሰው የማያውቀው ሚስጥር አለ
እቺህ መቅድ ግን ለሁሉም ነገር ስልክህን ስልክህን ማለት አብዝታለች ስልክ ስትለኝ ልቤ በድንገት ቀጥ ይላል ስልክ ውስጥ ድሌት ያላደረኩት ነገር ካለ ብዬ በፍጥነት ገብቼ አይቼ ነው ስልኩን የምሰጣት ደሞ እኮ ለትንሽ ደቂቃ እኮ ስልኩ በሷ እጅ እንዲቆይ አልሰጥም ብቻ የሆነ ምክንያት ፈልጌ ከእጇ እቀባላለሁ ምናልባት ደስታ የሆነ መልእክት ቢልክ ብዬ እኮ ነው እንዴ ውሸታም ሰው ሁሌም ለነገሮች ምክንያት የሚፈልግ ሰው ግን ይኖር ይሁን?

አንድ ቀን  እኔ እና መቅዲ ቤት ውስጥ ለብቻችን ቁጭ ብለን እያለን ጆን ጆን ቆይ አንተ ለሴት ያለህ ጥላቻ ምንድነው ስትለኝ ደንግጬ መቅዲ ምን እያልሽኝ ነው? ከምን ተነስተሽ ነው እንደዚህ አይነት ጥያቄ ለመጠየቅ የቻልሽው ብዬ ስጠይቃት.....
ትንሽ ከሳቀች በኋላ ጆን ከልብህ የምትወዳት ሴት አለች ማለት ነው ባይሆን እንደዚህ አትደናግጥም ነበረ ስትለኝ ኧረ መቅዲ ቀልድ ጀመርሽ ማለት ነው በቃ? ቆይ መጀመሪያ ላንቺ ፍቅር ምንድነው አልኳት?
ፍቅር ማለት ለኔ?
አዎ ላንቺ አልኳት
ፍቅር ማለት ለኔ...
ባህር ውስጥ ገብቶ መዋኛት እንደማለት ነው ፍቅር ማለት ለኔ መሬት ላይ ሆነው ሰማይ ላይ ያለውን ጨረቃን እንደማየት ነው
ፍቅር ማለት ለኔ ራዕይ ነው ስትለኝ... መቅዲ ምን አይነት ንግግር ነው ግራ ተገባሁ እኮ ምን ለማለት ነው ብዬ በሚገርም ስሜት ውስጥ ሆኜ ስጠይቃት
ጆን አየህ ፍቅር ውስጥ ስትሆን ባህር ውስጥ ከመዋኛት ሁሉ አስር እጥፍ የሚከብድ ስሜት ጋር መጋፈጥ ትቀጥላለህ...
ውሃ ውስጥ ስትሆን ትንፋሽ እንደሚያጥር ሁሉ ፍቅር ውስጥ ስትሆንም ልብህ ሌላ ነገር ማሰብ ያቅተዋል
ፍቅር ማለት መሬት ላይ ሆነህ ሰማይ ላይ እንደምታየው እንደ ጨረቃ ነው
አንተ ሩቅ ላይ ነህ አንተ ጨለማ ላይ ነህ ብሎ ጨረቃ ውበቱ በፍጹም ደብዝዞ አያውቅም ፍቅርም እንደዚሁ ነው አንተ ድሃም ሁን አጭር ወይንም በሽተኛ አንተ እንደዚህ ነህ ብሎ እሱ ስራውን አይተው የማንም ልብ ውስጥ ገብቶ እንደ ጨረቃ ውበት ይሰጣል
ፍቅር ማለት ራዕይ ነው መቼም ዋሽቶ አያውቅም ራዕይ እኮ አይዋሽም ሁሌም እውነተኛ ነው አንዴ ያያከው ራዕይ ምንም ቢቆይም መሆኑ አይቀርም ለኔ በቃ ፍቅር ማለት ይኼ ነው
ብለ እሷ ወሬውን አውርታ ስትጨርስ እኔ ሌላ አለም ውስጥ ነበርኩኝ
አንተ ጆን? ምነው ፍዝዝ አልክ ስትለኝ አይ ምንም አልኳት
እኔ ግን በጨረቃው ምሳሌ እስከአሁንም እንደተመሰጥኩ ነው
መቅዲ ግን እንደዚህ አስተዋይ ናት ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም ነበር


ክፍል ሰባት ረቡዕ ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄

      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
5.5K views , 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 23:19:34 ‍ ​​​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

           ክፍል


አቤት የውሸት መጨረሻ ገና ከጅምሩ ተይዤ ነበረ እኮ
እነ መቅዲ ቤት ልዩ ክብር እና ቦታ እየሰጡኝ ነው እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጣቸው ለኔ ከሚገባ በላይ ብዙ ነገሮችን እያደረጉልኝ ነው ቤተሰቦቼም እንደበፊቱ ብዙ እየተቸገሩ አይደለም ምክንያቱ ደሞ የመቅዲ እናት እና አባት ናቸው።
ሁሌም ልብህ ንጹህ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሰውን አንዴ ከፈጠረ እንዴት አድርጎ እንደሚያኖር ራሱ ያውቃል የሰው ልጅ ብዙ ስለሮጠ ስኬታማ አይሆንም መስራት መሮጥ መጥፎ ነው እያልኩ አይደለም ግን አንድ አንድ ሰዎች አለን አይደል በመሮጥ ብቻ ስኬት የሚገኝ መስሎን የሰውን ሃቅ ጭምር በእጃችን ለማስገባት ቀን በእግር ማታ በሃሳብ እየሮጥን ውለን የምናድር!
ብዙዎች አለን አይደል ለገንዘብ ብለን ጓደኛን የምንክድ
ብዙዎች አለን  አይደል ለራሳችን ስኬት ብለን ቤተሰቦቻችን ሲቸገሩ አይተን ዝም የምንለው
ዛሬ ብር መሰብሰብ ብቻ ሀብታም አያደርግህም ምን አይነት ንግግር ነው ብር ከተሰበሰበ እንዴት ሀብት አይሆንም ልትሉኝ ትችላላችሁ ግን እውነታው ብር ስለሰበሰብክ ብቻ ሀብታም መሆን አትችልም!
ሀብታም መሆን የምትችለው የምትሰበስበው ብር ላይ ምንም እንከን የማይደርስ ከሆነ ነው እንከን የሚደርስ ከሆነ አንተ ዝም ብለህ ትሮጣለህ አንተ ለብዙ አመታት ሮጠህ ያጠራቀምከው ሁሉ በአንድ አጋጣሚ ተበትኖ ታያለህ ለዚህ ነው መሮጥ ብቻ ስኬታማ አያደርግም ያልኩት
ስኬታማ መሆን የምትችለው
በቅንነት
በታማኝነት
በእምነት መሮጥ ስትችል ነው
•ቅንነት ሲኖርህ ለሌሎች መልካም ነገር ማድረግ ትጀምራለህ ለሌሎች መልካም ነገር እያደርክ ነው ማለት ደሞ ለፈጣሪ ብድር እየሰጠህ ነው እንደማለት ነው ስለዚህ ፈጣሪ ለአንተም ይሰጣል ማለት ነው

•ታማኝነት ሲኖርህ አንተ ለሌላ ሰዎች ታማኝ እንደሆንክ ሁሉ ፈጣሪ ደሞ ለአንተ ታማኝ ይሆናል ማለት ነው

• እምነት ሲኖርህ በፈጣሪ በሙሉ ልብ ማመን ትጀምራለህ በሙሉ ልብህ ፈጣሪን ማመን የምትችል ከሆነ ደሞ ፈጣሪ በእሱ የሚያምኑትን መቼም ቢሆን አይጥልም ማለት ነው
ስለዚህ የስኬት ቁልፍ መሮጥ መስራት ብቻ ሳይሆን ከስራ እና ከሩጫ ጋር ቅንነት ታማኝነት እና እምነት ጭምር ይዞ መሮጥ እና መስራት ነው
እዚህ ቤት በጣም ጥሩ የሆነ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው መቅዲን በመኪና ት/ቤት አድርሼ መልሼ ቤት የማመጣት እኔ ነኝ
መቅዲ ቀበጥ ለሁሉም ነገር ችኩል እና የዋሀ ልጅ ናት
ከማንም በላይ የማውቃት እኔ ነኝ ብል ውሸት አይሆንብኝም፤
በርግጥ የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ ማለት ስህተት ነው እናትም ብትሆን ልጇን ሙሉ በሙሉ ማወቅ ላትችል ይሆናል ሰውን ሙሉ በሙሉ ማወቅ የሚችለው አንዱ ፈጣሪ ብቻ ነው።
ቢሆንም ግን ሰው ሰውን በሚያውቀው ልክ ከሌላ ሰዎች ይልቅ መቅዲን አውቃታለሁ ምክንያቱ ደሞ በነገሮች ላይ ግልጽ መሆንዋ ነው
በቃ መቅዲ በሁሉም ነገር ግልጽ ናት
ለምን ይሁን ብቻ አላውቅም የትኛውንም ነገር ከእኔ መደበቅ አትፈልግም አንድ አንድ ጊዜ ጭራሽ የሌላ ቤት ልጅ እንደሆንኩ ሁሉ ትረሳለች መሰለኝ ልክ እንደ ወንድም ሁሉ አድርጋ ትቆጥረኛለች
የዋሀ ሴቶች ግን ደስ አይሉም?
ወንድ ልጅ የዋሀ ሲሆን ሞኝ ይመስላል ሴት ልጅ የዋሀ ስትሆን ግን አንጀትን ነው የምትበላው
መቅዲ እኔ ደስታ ነኝ እያልኩ በምልክላት ግጥም ፍቅር ውስጥ ገብታለች
ጭራሽ ለጠዋት ቁርስ እና ለማታ እራት የአንተን ግጥም በልቼ ውዬ ባድር እያለችኝ ነው
የዋሀ ስለሆነች ማስመሰል ምናምን አታውቅም የምታወራው ነገር ሁሉ ከልቧ ነው

ትልቅ ችግር ውስጥ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል ውሸት እንደሆነ ጊዜ ይፈልጋል እንጂ የትኛውንም ጉርጓድ ቆፍረው ማውጣቱ አይቀሬ ነው
መፍትሄው ምን ይሁን እያልኩ ጭንቅ ውስጥ ገባሁ
የስስስ አንድ ሃሳብ መጣልኝ

ክፍል ስድስት ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄

      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
5.4K views , 20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 21:07:26 ‍ ​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

        ክፍል ❹


ዛሬ እንደውም ለእቃ ልመጣ ነው እስኪ አንድ ምርጥ ግጥም አዘጋጅ አለችኝ
ምን?
እሱ እኮ በአማርኛ ከሰላምታ እና ስድብ ሌላ ነገር አያውቅም  ወይኔ ጉዴ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብዬ ስልክ ደወልኩለት...
ጉራጌ እኮ ነኝ ለዚህ ነገር መፍትሄ አይጠፋም ብቻ እሷ ትምጣ እንጂ ግን መቼ ነው የምትመጣው ብሎ ጠየቀኝ እኔም ከሷ ጋር እመጣለሁ መፍትሄው ግን ምንድነው አልኩት
አንተ ብቻ በወረቀት አሪፍ ግጥም ይዘህ ና ሲለኝ እሷ እኮ በወረቀት ሳይሆን በተግባር ነው የምትፈልገው አልኩት
ለእሱ ችግር የለውም አንተ ብቻ ወረቀቱን ይዘህ ና አለኝ
ይኼ ልጅ ምን አስቦ ነው እንደዚህ በራስ መተማመኑ  ከፍ ያለው እያልኩ በወረቀት ላይ ግጥም ጽፌ ከመቅዲ ጋር አብረን ሄደን
ደስታ ሳቅ በሳቅ ሆኖዋል
ይኼ ልጅ ጠጥቶ ይሁን እንዴ እያልኩ እቃ መሰብሰብ ቀጠልኩኝ
መቅዲ ደስታን ሰላም ብላ ልክ ስለ ግጥም ምናምን ማውራት ስትጀምር የሆነ ደረቅ ልጅ መጥቶ ቤቱን ቅውጥ አደረገ
በዚህ መሃል ቀስ ብዬ በወረቀት የጻፍኩትን ግጥም ለደስታ ሰጠሁት እሱም መቅዲ ይቅርታ ይሄ እብድ ልጅ የጻፍኩትን ግጥም እንዳላናብ ከለከለኝ እኮ ባይሆን አንድ ምርጥ በወረቀት ላይ የጻፍኩት ግጥም አለኝ ብሎ ከእኔ የተቀበለውን ወረቀት ሰጣት
ችግር የለውም አንተም እኮ ስራ ላይ ነህ ወረቀት ላይ መሆኑ ጥሩ ነው በጣም አመሰግናለሁ ጓደኛዬ ብላ እቃውን ገዝተን ወጣን...
እኔ መቅዲ የረሳሁት ነገር አለ ጠብቂኝ ብዬ ሄጄ አንተ እብድ የቅድሙ እብድ ልጅ ማነው አልኩት ባክህ ልጁ እብድ አይደለም ጓደኛዬ እኮ ነው መቅዲ ግጥሙን አንብበው እንዳትለኝ ቤቱን ቅውጥ ያደረገው ብሎ መሳቅ ጀመረ
ከምር እብድ ነህ አንተ ግን ፍቅር ምናምን የሚለውን ነገር ትታ እንደ ሌሎቹ ጉራጌ ሁሉ ገንዘብ ብትሰበስብ ይሻልሃል ጉራጌ ሲሰራ ነው የሚያምረው ብዬ ስቀልድ
ባክህ ፍቅር እንደውም በጉራጌ ላይ ነው የሚያምረው ባይሆን ለውለታህ በጣም አመሰግናለሁ አለኝ

ማነህ ደስታ ምስጋና ኪስ አይገባም በአንተ ስም የጉራጌ ክትፎ ምናምን ልጋብዛት ብር ስጠኝ አልኩት
ደሞ ለመቅዲ ብሎ ስንት እንደሆነ ሳይቆጥር ብዙ ብር አውጥቶ ሰጠኝ
አንተ? እኔ ስቀልድ ነው ድሮ እኔ የማውቀው ጉራጌ ቆጣቢ ነው ሲባል ነበረ ምነው እንደዚህ ቸር ሆንክ በል በል ይኼን ብር ወደ ቦታው መልስ ብዬ ሀያ ብር ብቻ ስጠኝ ብዬ ሀያ ብር ተቀብዬ ወጣሁኝ ከዛም አንድ ትኩስ እሸት ከመንገድ ዳር ገዝቼ መቅዲ ጋር ሄድኩኝ....
አንተ ጆን ጤና የለህም እንዴ መንገድ ላይ እኔን አቁመ ይኼን ሁሉ ሰአት ስትለኝ ባክሽ ያ ደስታ የምንለው አዝግ ልጅ እኮ ነው ለመቅዲ እሸት ይዘህ ትሄዳለህ ብሎኝ እሸት እየገዛልሽ ያቆየኝ አልኳት
ለምን ቅድም ዝም አለ ስትለኝ
ምናልባት ፈርቶሽ ይሆናል አልኳት
እብድ የሆነ ልጅ ግራ እኮ ነው የሚያገባኝ ልጁ ግን ግጥም በጣም ይችላል ወይኔ ገጣሚ ወንድ ስወድ ስትለኝ በልቤ እየሳቅኩ ነው
እኔ በጻፍኩት ግጥም እሱ ምስጋና  ተቀበለ
እኔ በገዛሁ እሼት እሱ ምስጋና ተቀበለ
እኔ ምን አገባኝ ዋናው እሱ የሚፈልገውን መቅዲን አግኝቶ ደስ መሰኘቱ ነው እኔ እንደሆንኩ ስራ እንጂ ፍቅር ምናምን እያሉ ጊዜ ማበከን አልፈልግም ብቻዬን ዘና ፍታ ማለት ነው ምግብ እንኳን ጠግቤ መብላት ሳልጀምር የምን አባቱ ፍቅር ነው?
ልክ ቤት እንደደረሰን መቅዲ በፍጥነት ስልኳን ከኪስ አውጥታ አንተ እብድ ስለ ግጥሙም ስለ እሸቱም አመሰግናለሁ አለችኝ
ኧረ መቅዲ ምስጋና እኮ አያስፈልግም ጓደኛዬ አይደለሽ አልኳት እሺ ምን እያደርክ ነው ስትለኝ እውነትም እኔን የጠየቀችኝ መስሎኝ ቴሌቪዥን እያየሁ ነው አልኳት
ምን? የምን ቴሌቪዥን ሱቅ ውስጥ አይደለህ ስትለኝ ደንግጬ አይ በስልኬ በቴሌቭዥን የሚታለላፍውን ፕሮግራም ማለቴ ነው አልኳት
አቤት የውሸት መጨረሻ ገና ከጅምሩ ተይዤ ነበረ እኮ


ክፍል አምስት ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share

  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
6.1K views , 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 12:27:06 ‍ ​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት

በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

              ክፍል

ደስታ ነኝ ብዬ ወሬው ተጀመረ
እንግሊዝኛው በዚህ ከቀጠለ ሰላም አይመጣም ብዬ በቶሎ ወሬውን ወደ ግጥም ቀየርኩት
መቅዲ ግጥም በጣም እንደምትወድ አውቃለሁ እኔ ደሞ ግጥም መጻፍ ትንሽ ትንሽ እችላለሁ...
ግጥም ትወጃለሽ አይደል ስላት በጣም ነው የምወደው ግጥም እንደምወድ ግን በምን አወክ ስትለኝ ፌስቡክ ላይ አይቼ ነው አልኳት ደስታ ደስታ ግን እኮ እኔ አንተን አላውቅህም የት ነው የምትኖረው ብላ በድጋሚ ጠየቀችኝ እኔ ጥያቄውን መመለስ ትቼ አንድ ጥሩ ግጥም ልኬ ከኦንላይን ወጣሁኝ
ዋውውውው ግጥም ትችላለህ እንዴ በጣም ደስ የሚል ግጥም ነው እኔ እኮ የግጥም አድናቂ ነኝ ብቻ ግጥሙን በጣም ነው የወደድኩት አለችኝ
መልእክቱ የመጣው በአማርኛ መሆኑን አይቼ ተመስገን አምላኬ መፍትሄ ተገኘቷል ብዬ ለጊዜው ዝም አልኩኝ እኔም ለመከበድ ፈልጌ እኮ ነው
በሁለተኛው ቀን ማታ አካባቢ እሺ ደስታ ዛሬ ግጥም የለም እንዴ ምነው ዝም አልክ ስትለኝ
ሞት ይርሳኝ ረስቼ እኮ ነው ብዬ በድጋሚ አንድ አጭር ግጥም ልኬ ዝም ስል ከምር ሁሉም ግጥሞች ምርጥ ምርጥ ናቸው ቆይ ለምን ጓደኛሞች አንሆንም አለችኝ
በጣም ደስ ይለኛል አልኳት
ከዛ ቀን ጀምሮ በቴሌግራም ምርጥ ጓደኛሞች ሆነን...
አልፎ አልፎ በእንግሊዝኛ አስገድዳ ለመድፈር ብትሞክረኝም እኔ በግጥም ምክንያት እያደረኩ ወደ አማርኛ በመቀየር ጓደኝነታችን ቀጠለ....

የመቅዲ እናት እና አባት በፍጹም ከማስበው በላይ መልካም ነገር አደረጉልኝ
ሙሉ በሙሉ ወጭውን እኛ እንችላለን መንጃ ፍቃድ አውጣ ከዛ በኋላ እኔንም ስራ ቦታ በዛውም መቅዲንም ት/ቤት ታደርሳለህ አሉኝ
በፍጹም ይሆናል ያላልኩት ነገር በህይወቴ ሆነ ከሽቃላ ስራ በአንዴ ወደ መኪና መንዳት! የሚገርም ለውጥ ነው ለዚህም እኮ ነው ህይወት በገጠመኞች የተሞላች ናት የትኛውም ቦታ በየትኛውም ዝቅታ ላይ ብትሆን ተስፍ አትቁረጥ የተባለው! የመንጃ ፍቃድ ትምህርት ወስጄ መንጃ ፍቃድ አወጣሁ በዚህ መሃል ሁሉ ግን ከመቅዲ ጋር እያወራን ነው
መቅዲ ደስታም ማን እንደሆነ ከእሷ ጋር የሚያወራ ሰውም ማን እንደሆነ አታውቅም
ሁሌም Supermarket ስትሄድ ባለሱቁ ደስታ በውበቷ ተሸንፎ ሰውን እንኳን ማስተናገድ አይችልም ሁሌም ድንብርብር ሲል እሷ ለራሷ are you mad ብላ ቤት ትመጣለች
እሱ ስድቡንም እንደ ምስጋና ተቀብሎ እሱም አመሰግናለሁ ብሎ በደስታ ሞቅ ብሎ ይውላል

ከመቅዲ ጋር በቴሌግራም ጥሩ መግባባት ችለናል እኔም ግጥም እልክላታለሁ እሷም ለኔ ግጥም ትልክልኛለች እስከ አሁንም ግን ማንነቴን አታውቅም
አሁን ግን ማንነትህን ንገረኝ እያለች በጣም አስቸግራኛለች
እዚሁ ሰፈር እኮ ነኝ እኔ አላውቅም ስትይኝ ለቀልድ መስሎኝ እኮ ነው አንቺ የእውነትሽን ነው እንዴ አልኳት
ምን አይነት ቀልድ ነው? እውነት እኔ እዚህ ሰፈር ደስታ የሚባል ወንድ አላውቅም አለችኝ
እሺ Supermarket ውስጥ የሚሰራውን ልጅ አታውቂውም ስላት ምን?? ብቻ እኔ ነኝ ይኼን ግጥም የምልክልሽ እንዳትለኝ አለችኝ
እንዴ መቅዲ ምን ማለት ነው እኔ እኮ ግጥም እችላለሁ አልኳት
ታዲያ ምንድነው እዛ ስመጣ እርኩስ መንፈስ እንዳለበት ሰው የሚያደርግህ? ስትለኝ
ታድያ ፀበል አትወስጅኝም አሪፍ አሪፍ ግጥም እልክልሽ ነበረ አልኳት ለእሱ ችግር የለም አንተ ልጅ ግን ጭራሽ ሁለት ሰው እኮ ነው የምትመስለው በተግባር አንድ ራሱን የቻለ ሰው በቴሌግራም ደሞ ሌላ አንድ ራሱን የቻለ ሰው ስትለኝ በጣም ስቄ አንቺ እኮ ነሽ እንግሊዝኛ ብቻ አውርቼ ልሙት እያልሽ ሰውን ግራ የምታገቢ አልኳት
እንግሊዝኛ ትችል የለ እንዴ ነው ወይስ አይናፋር ነገር ነህ አለችኝ
እንደዛው በይኝ አልኳት
ዛሬ እንደውም ለእቃ ልመጣ ነው እስኪ አንድ ምርጥ ግጥም አዘጋጅ አለችኝ
ምን??

ክፍል አራት ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄

      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
7.1K views , 09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 20:39:28 ‍ ​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

             ክፍል 2


በዚህ አጋጣሚ ነበረ መቅዲም ከት/ቤት በመኪና የመጣችው....
አንገቴን ቀና አድርጌ አይኔን አፍጥቼ ውበትን በማድነቅ በልቤ አቤት የፈጣሪ ስራ እያልኩኝ በድንገት Whats up ስትለኝ በድንጋጤ ከግቢው በንኜ ልወጣ ስል ነው እናቷ ጆን ስራውን ጨርስክ እንዴ? ጨርሰህ ከሆነ ቤት ግባ ያሉኝ
ቤት ውስጥ ስገባ ምግብ ሰጡኝ ምግቡን በልቼ አመሰግናለሁ ብዬ ልወጣ ሲል ለአንድ አንድ ነገር ይሆንሃል ብለውኝ አምስት መቶ ብር ጨምረው ሰጡኝ
ኧረ እማማ አልበዛም ስላቸው ችግር የለም ያዘው ባይሆን ጠዋት ጠዋት መጥተህ ሁሌም ለአበቦቹ ውሃ ብታጠጣ ደስ ይለኛል ሲሉኝ በጣም ደስ ይለኛል ምንም ችግር የለም ብዬ ወደ ቤት መጣሁኝ....
ደስታ ይባላል በቅርቡ ከጉራጌ ዞን የመጣ ጃለሴ ነው በወንድሙ Supermarket ውስጥ ይሰራል እኔም እቃ ሲመጣ በሽቃላ ምክንያት ምናምን ስለምገባ በዛ ያውቀኛል ልጁ በቃ ምርጥ ነው በቃ ደስ ይለኛል
እሱ አማርኛ ብዙም አይችልም እኔ ጉራግኛ ማውራት ስለምችል በዛ እንግባባለን...

አንድ አንድ ጊዜ አንተ እኮ ጉራጌ አትመስልም ብዬ እቀልዳለሁ ለምን ሲለኝ ጉራጌ ለቋንቋ ሆነ ከሰው ጋር በቶሎ ለመግባባት በጣም ጎበዝ ናቸው አንተ ግን ትንሽ ለየት ትላለህ ቋንቋ አትችልም በዛ ላይ አይናፍር ነህ ስለው ተፈጥሮ ዘር ይለያል ብለህ ነው ብሎ ዝም ይላል።
ቀስ በቀስ እነ መቅዲ ቤት ሙሉ በሙሉ ግቢ ውስጥ ገባሁ ማለቴ የትኛውንም ግቢ ውስጥ ያሉ ስራዎችን እኔ መስራት ጀመርኩኝ
በዚህ ወራት ሁሉ የመቅዲ ትክክለኛ ፀባይ ምን እንደሆነ አላውቅም ክፉም ሆነ ደግም አትናገርም ስታወራ ራሱ በእንግሊዘኛ ስለሆነ ምንም ነገር መስማት አልችልም

ባለሱቁ ደስታ ስለ መቅዲ አብዝቶ ማውራት ጀምሯል የሚያወራው ራሱ ስለ እሷ መሆኑን ያወኩት ያቺ እንግሊዝኛ ብቻ አውርቼ ልሙት የምትለዋ ቆንጆ ልጅ ማናት ሲለኝ ነው
ምን ሆነች ስለው በቃ ደስ ትለኛለች እሷም ደሞ የምትወደኝ ይመስላል ቋንቋ ገደለኝ እንጂ ባለፈው ራሱ ብዙ እቃ ገዝታ ፍገግታ ስሰጣት Stupid ስትለኝ እኔም አመሰግናለሁ ብዬ በጣም ደስ አለኝ አመሰግናለሁ ማለት ነው አይደል ሲለኝ አዎ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ህልም እና እንግሊዝኛ እንደ ፍቺው እኮ ነው ስለዚህ ትክክል ነህ አልኩት

በእናትህ አንድ ነገር ተባባረኝ ሲለኝ ምን አልኩት?
አንተ የምትሠራው እነሱ ቤት ነው አይደል ሲለኝ አዎ አልኩት
በእናትህ እንደምንም ሆነህ ቁጥር ተቀበል አለኝ
እሺ ከዛስ ?
ከዛ በቃ ባለሱቁ ደስታ ነኝ ብለህ በስልክ አንተ ታወራለህ ትወደኛለች እኮ ቋንቋ ግን አልችልም በእናትህ ሲለኝ
ላንተ ይመችህ እንጂ ችግር የለውም እንደምንም ሆኜ ቁጥር አመጣለሁ አልኩት
ቤት ውስጥ ቀስ ብዬ የመቅዲ እናት ስልክ የሚያስቀምጡበት ቦታ መፈለግ ቀጠልኩኝ ......
በመጨረሻም ቦታውን አግኝቼ የመቅዲን ቁጥር በስልኬ ላይ Save አድርጌ ለደስታ ሰጠውት
ለኔ ለምን ትሰጠኛለህ? እኔ ምን ላርገው?? እንግሊዘኛም ቢሆን አማርኛ አንተ ከእኔ ትሻላለህ አንተ ደውለህ አውራ አለኝ
እኮ ማን ነኝ ብዬ ምን ብዬ አልኩት??
እኔ እንጃ ግን በእናትህ አንድ ነገር አድርግ አለኝ እሺ ግን መደወል የለብንም ይኼ የሷ ቁጥር telegram ይሰራል በቴሌግራም በእንግሊዝኛ ወሬ ልጀምር አልኩት
አንተ እንግሊዝኛ ትችላለህ እንዴ ሲለኝ
ማውራት አልችልም እንጂ መጻፍ እችላለሁ አልኩት
ምን? መጻፍ የምትችል ከሆነ ለምን ማውራት አትችልም ሲለኝ እብድ ነህ እንዴ? ስትጽፍ እኮ ሙሉውን ከጻፍክ በኋላ ስህተት ከሆነ delete አድርገህ በድጋሚ ቀላል መንገድ ተጠቅመህ መጻፍ ትችላለህ ማውራት ግን አንዴ ካመለጠ በቃ አመለጠ ነው ስለው በቃ አንተ ደስ እንዳለህ ሁን አለኝ እኔም አማርኛ ከጀመርኩ ገብታ ማየት እንኳን አትፈልግም ብዬ በእንግሊዝኛ ጀመርኩኝ
ደቂቃ እንኳን አልቆየችም who are you ስትለኝ I'm fine and you ብዬ ለመላክ ደግሜ ሳነበው ለካ ማነህ ነው ያለችኝ ለዚህም እኮ ነው መጻፍ ይሻላል ያልኩት ደስታ ነኝ ብዬ ወሬው ተጀመረ ....


✎ ክፍል 3 ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄

      ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
8.2K views , 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-25 20:36:49 ‍ ‍ ‍ ​​​​ ሚስጥራዊ ሚስት


በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

              ክፍል ➊


እንተዋወቅ? ጆን ነኝ ቤተሰቦቼ መንደራችን ውስጥ ድሃ
ከሚባሉ ሰዎች ተርታ ይመደባሉ ከድህነት በታች ሌላ ስም
ስለሌለ ነው እንጂ ድህነት የሚለው ስም ራሱ እኛ ቤት
ያለውን ችግር አይገልጽም!
ቤት ውስጥ ታለቅ እኔ ስለሆንኩኝ የታናሽ እህት ወንድሞቼ
ነገር እንቅልፍ አይሰጠኝም
ለዚህ ብዬ አይደል እንደዚህ የምወደውን ትምህርት ትቼ የቀን
ሽቀላ ምናምን የጀመርኩት
በህይወት ስትኖር ምናልባት የህይወት ፍቺ የሌለ ህልም
ልትሆንብህ ትችላለች አንተ ግን ምንጊዜም ""ለእምነትህ""
ኑር! በልቤ ሁሌም ትልቅ ህልም አለ እኔ ተምሬ መድረስ የምፈልገውን ቦታ እኔ መድረስ ባልችልም ከታናሽ እህቶቼ/ ወንድሞቼ መሃል አንዱ እንዲደርስ እፈልጋለሁ በቃ የዘወትር ህልሜ ይኼው ነው ልቤ ውስጥ ካለው መልካም ህልም የተነሳ የትኛውንም ስራ
እሰራለሁ ትልቅ ነገር ተሸክሜ እንኩዋን ከበደኝ አልልም
በዚህ መሃል ሁሉ ግን የሰው ነገር ላይ እጄን አንስቼ አላውቅም በቃ የሰው ነገር የሰው እንደሆነ አምናለሁ በድህነት ምክንያት እምነቴን ታማኝነቴን ማጣት አልፈልግም ። ለእምነት መኖር ታማኝ መሆን አንድ ቀን አንድ ብርሃን ይዞ እንደሚመጣ ሁሌም አምናለሁ ከእለታት አንድ ቀን ገበያ ውስጥ ሽቀላ ፍለጋ ላይ ዞር ዞር ስል የመቅዲ እናት ጆን ጆን ብላኝ ጠራችኝ... አቤት እማማ ብዬ ሄድኩኝ ጆን ዛሬ መኪና አልያዝኩም ትንሽ እቃ አለ ቤት ታደርስልኛለህ ሲሉኝ እሺ ብዬ እቃውን ተሸክሜ ቤታቸው ሄድን... የመቅዲ ቤተሰቦች እኛ ሰፈር በጣም ሀብታም ቤተሰቦች ናቸው: ከመቅዲ ሌላ ልጅ ግን የላቸውም አቤት የፈጣሪ ስራ! ምግብ እንኳን በሌለበት ቤት ለእናቴ ስምንት ልጆች አሳቅፎ ወርቅ እንኩዋን ትርጉም በሌለበት ቤት ደሞ ልጅ ከለከለ ለዚህም እኮ ነው ""የተሰጠውን ቢያውቅ"" ሰው ሁሉ ሀብታም ነው የተባለው ቤት ይሁን ቤተ መንግሥት ብቻ አላውቅም የሆነ ይሁን ብቻ ገብተን ለኔ የሰራውበትን ብር ተሰጥቶኝ ከግቢ ልወጣ ስል አይኔ በቅስፈት ግቢ ውስጥ አንድ ነገር አይቶ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ ምን ቢሆን ጥሩ ነው? ወርቅ እኮ ነው ስንት ግራም እንደሆነ እነሱ ያውቃሉ እኔ የማውቀው ወርቅ መሆኑን ብቻ ነው ሁሌም እርግጠኛ ሆኜ ማውራት የምፈልገው ነገር ቢኖር የሰውን ነገር ማንሳት አልወድም። ዛሬ ወርቁ እምነቴን ሊፍትነው ነው እንዴ? ብር ደሞ ቤት ውስጥ በጣም አስቸግሯል ትንሽ አስቤ ከምንም በላይ እምነቴ ይበልጣል ብዬ እማማ ይቺን ነገር ብዬ ወስጄ ሰጠሁ በጣም ተገርመው ጆን ነገሩ ምን እንደሆነ አውቀሃል? ብለው ጠየቁኝ ሀብታም ሰዎች እኮ አንድ አንዴ ሞኝ ናቸው ሁሉንም ነገር ከድህነት ጋር ወስደው ያገናኙታል መቼም ወርቅ መሆኑን ቢያውቅ አይመልስም ለማለት ነው አይደል!? ወርቅ ነው አይደል አልኩኝ ጥቅሙን ምንም እንደማያውቅ ሰው.. ለኔ ይኼ ወርቅ ማለት ምን ትርጉም እንዳለው የማውቀው
እኔ ብቻ ነኝ ወርቅ ለኔ ብርቄ አይደለም ይኼ ወርቅ ግን ትልቅ ነገር ነው አሁን ምን ትፈልጋለህ ብለው ጠየቁኝ የሰው ልጅ እኮ መልካም ነገር ሊያደርግልህ የሚፈልገው መልካምነትህን አይቶ ብቻ ነው ምናለ ቀድሞ መልካም ቢያደርግ? አይይይ ይኼ እኮ የራሶት እቃ ነው ምንም ክፍያ አልፈልግም ብዬ ሊሄድ ስል ጆን እንደዛ አይደለም አንድ ነገር ውሰድ
እኔንም ደስ ይበለኝ አሉኝ
የሰው ልጅ እኮ አስመሳይ ነው
መስጠት ደስታ የሚሰጥ ነገር መሆኑን ካወቀ ለምን እንደ እኔ
ለመስራት አቅም እንኩዋን የሌላቸውን በእየ መንገዱ ወድቀው ያሉትን አዛውንቶች አይቶ ያልፋል?
Free ነገር አልፈልግም ግን ስራ ካለ ስጡኝ ሰርቼ በኋላ ደስ
ያሎትን ነገር ትሰጡኛለችሁ ስላቸው እሺ ግቢውን ፀዳ ፀዳ
አድርግ አሉኝ እኔም እሺ ብዬ ስራውን ቀጠልኩኝ...በዚህ መሃል ነበረ መቅዲ ከት/ቤት በመኪና የመጣችው........
ይ ቀ ጥ ላ ል ......

✎ ክፍል ሁለት ይቀጥላል ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር ማድረግ አይርሱ።
        ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
••●◉Join us share
https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk
  ይከታተሉን | Follow us፡
@yefkrtarik @yefkrtarik

    ┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
      ‌‌‌‌‌‌‌     
10.2K views , 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ