2022-09-15 20:35:32
ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ!
......(( ክፍል 20))......
=====================
@Raymondds የተፆፈ በRaymond
ተዘጋጅቶ የቀረበ
መልካም ንባብ
"እና ምን አማራጭ አለኝ"
'እሺ ከዛስ?'
"ምን አደረኩኝ መሰለህ? ሲምቢሮዬ እስከ አምስት ሰዓት እስከ ስድስት
ሰዓት ድረስ አምሽቶ ስለሚመጣ እንደድሮው አዳር ሳልሰራ ከአራት እስከ
አምስት ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለት ሶስት ሾርቴን ሰርቼ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ"
'ልጅሽን ለማን ጥለሽ ነበር ቢዝነስ ትሰሪ የነበረው?'
"እኔ ብቻ መሰልኩህ እንዴ ባለትዳር ሆኜ ሸሌነት የምሰራው? ሌሎችም
ብዙዎች አሉ'ኮ በሲቪል ሙድ የሚጠቀሙ"
'ሲቪል ስትይ?'
"እኛ ያለምንም ማፈር ሴትነታችንን ለገበያ እንደምናቀርብ ሁሉ አንዳንድ
የኮሌጅና የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም ጥቂት የማይባሉ ባለትዳሮች
በሲቪል ሙድ አንዱ የቺቺኒያ ፐብ ይገቡና ለብቻቸው መጠጥ አዘው
ይቀመጣሉ። ከላይ ስታያቸው ምንም የማያውቁ ሸዋዬ ነው የሚመስሉህ ፣
ከኛ በላይ ግን እሳት የላሱ አራዶች ናቸው። ከዛ ሲቪሏ ብቻዋን ስጠጣ
አንዱ ፋርጣ ወንድ አገኘሁ ብሎ ሊበላ ሊጀነጅናት ይሞክራል። እሷም
ወዘናውን ታይና ጨላ የጫነ ቅባት ከመሰላት የፉገራ ብሶቷን
ታራግፍበታለች።
'የኔ ቆንጆ ምነው ባልጠፋ ወንድ ብቻሽን' ይላል የልብስ አራዳ የሆነው ጥሬ
ሰገጤ
'በናትህ የሌለ ምርር ነው ያለኝ!' እያለች የቤት ኪራይ አልፎብኝ ነው ወይ
ደግሞ የትምህርት ቤት ክፍያ ቸግሮኛል እያለች ትርፍ አንጀቱን ትበላዋለች።
አጅሬውም የቤት ልጅ አገኘሁ ብሎ 'ምንም አትጨነቂ የቻልኩትን
አግዝሻለሁ' ይልና የጠየቀችውን ብር ከፍሎ ይዟት እብስ ይላል። ይቺን ሙድ
እኔና ጓደኞቼም አንዳንዴ club H2O ፣ ዩጎቪያ ላውንች ፣ ቦሌ መስመር
ያሉ ክለቦች ስንገባ በኩል ሙድ ሆነን እንጠቀምበታለን።እናልህ ባለትዳሮቹ ሲቪል ሸሌዎች አንዳንዶቹ ቸግሯቸው ጥቂቶቹ የቁላ ሱስ
ኖሮባቸው ሊሰሩ ሲመጡ ልጆቻቸውን እስከ ለሊት ድረስ በቀን 50 ና 60 ብር
እየከፈሉ የምትጠብቅላቸው አንዲት ጥጋበኛ አሮጊት ከአክሱም ሆቴል ጀርባ
አሁንም ድረስ አለች እኔም አቢን ቢዝነስ እስክጨርስ ድረስ እሷ ጋር
እየከፈልኩ አስቀምጠው ነበር። ሴትዮዋ ደግሞ አቢ እንደሌሎቹ ህፃናት
ስለማይበጠብጥ ደስ ይላት ነበር።የመጀመሪያ ቀን ወደ ሚሚ ቂጦ ቤት ስመለስ አስተናጋጅ በል አዝማሪ ፣
ባሬስታ በል ቀደምት የቤቱ ደምበኞች......ጓደኞቼ ሸሌዎቹ ሳይቀሩ በዕንባ
እየተራጩ እንዳልዳሩኝ ፤ አሁን ምን ሆነሽ ነው የመጣሽው ብለው
እንደመጠየቅ ለይምሰል ሽንት እንደሸተተው በግ ድድቻውን እያሳዩ
እየገለፈጡ ሰላም ብለውኝ ገና ካጠገባቸው ዞር እንኳን ሳልል ኮንዶም
በቀደደው አፋቸው እያሽሟጠጡ 'ድሮም የሸሌ ትዳርና ቻይና የሰራው
መንገድ ብዙም አይቆዩም!' እያሉ አሸሞሩብኝ። እኛ ሸሌዎች በችግራችንና
በደስታችን ጊዜ ብንረዳዳም ሲበዛ ቀናተኞች ነን። እኛ ሳንለወጥ አንዲት
በለስ የቀናት አብራን የምትሰራ ሌዲ ከተለወጠች ቆርኪ የመሰለው አይናችን
በቅናት ደም ነው የሚመስለው! ከበድ ያለውን ነገር ተወውና ድንገት
ጠርሮብኝ ካንዷ ደንበኛ ጋር ሾርት ብሰራ ያቺ ሸሌ አኔን እንጦሮጦስ
ለመክተት የማትቆፍረው ጉድጓድ የለም። ፒኪኒዬን ወይ የፀጉሬን ዘለላ ብቻ
ያገኘችውን የኔን ዕቃ ሰርቃኝ ሙጣሙጢም ልታሰራብኝ ባለከራማዋ ጋር ነው
ስትከንፍ የምትሄደው! በዚህ የተነሳ እርስ በርሳችን አንተማመንም። ብዙም
ባንሆን ጥቂቶች ራሳችን በቦርሳችን ይዘነው ከምንዞረው ብርጭቆ ውጪ
በመጠጥ ቤት ብርጭቆ አንጠጣም.....እና በቃ ሴቶቹ እያሸሞሩኝም ቢሆን
ባልሰማ ባላየ ብዬ ስራዬን ጀመርኩኝ።የመጀመሪያ ቀን ስገባ ጠፍቼ ስለመጣሁ ወንዶቹ ተረባርበውብኝ ወደ
አምስት ሾርት ሰራሁኝ። ገላቸው ገላዬን ሲነካኝ እንዴት እንደቀፈፈኝ
አትጠይቀኝ! እስከዛሬ ስሸራሞጥ የኖርኩ ቢሆንም ያን ቀን ግን ገላዬ የኔ
ብቻ እንዳልሆነ ህሊናዬ ደጋግሞ ስለነዘነዘኝ ከወንዶቹ ጋር ስተኛ
አንገሸገሸኝ። የሸቀልኳትን ሳንቲም ይዤ ወደ ቤቴ ተመለስኩ። ታዲያልህ
እቤት ስገባ ትንሽ ቆይቶ ሲምቢሮዬ ብትን ድምቅ ብሎ መጣ። ገላውን
እንዴት ደፍሬ ልንካው? የቆሸሽኩ ፣ ሀጢያቴ ሰውነቴ ላይ እንደ ላብ ተለጥፎ
የሚሸት መስሎኝ ልጠጋው ፈራሁት ፤ ብጠጋው ቅድስናውን የማረክስበት
ንፅህናውን የማጎድፍበት መሰለኝ።ሁኔታዬን አይቶ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ። ፔሬድ ላይ ስለሆንኩ ራሴን
እያመመኝ ሆዴን እየቆረጠኝ ነው አልኩትና ሻወር ቤት ገብቼ ኩል
የተቀላቀለበት ጠቆር ያለ ዕንባ እያነባሁ ሀጢያቴ የሚፀዳልኝ ይመስል
ገላዬን እንደ አራስ ገብስ ፈትጌ ታጠብኩት። ከሰውነቴ ላይ ተባይ ተባይ
የሚል ጠረናቸው የለቀቀ ቢሆንም ህሊናዬ ላይ የተከማቸውን ክርፋት ግን
በምን ላፅዳው?
ዝም ብዬ ሄጄ አጠገቡ ተኛሁ። ለነገሩ እንቅልፌ እኔን ተኛኝ እንጂ እኔ
አልተኛሁም ነበረ። ጋን ጋን በሚል የአፉ ትንፋሽ መገረፌን እንደ ቄዳር
ጥምቀት ቆጠርኩት። ለሳምንታት ባልታጠበው ብብቱ ውስጥ ጭንቅላቴን
መቅበሬን ለአፍንጫ የሚከረክር የወንድነት ጠረኑን መሳብ ልክ ለምልጃ
በመላዕክት እጅ ውስጥ ከሚያልፈው የከበረ ዕጣን በላይ ፈውስ ይሰጠኝ
ነበር።መቼም ፈጣሪ ከሰይጣን በላይ ሆድ የሚሉት ቆንጆ ጠላት ፈጥሮልን የለ?
ማታ የሸቃቀልኳት ሳንቲም በሶስተኛው ቀን አለቀ። ዳግመኛ ልጄን ለሞግዚቷ
አስረክቤ የቺቺኒያ ምትሀተኛ ውቅያኖስ የወንድን ልጅ ዋሌት ላጠምድ
የሴትነት መረቤን ጣልኩኝ። እንዲህ ከባሌ ጋር እንዳይነቃብኝ እያልኩ
አይጥና ድመት ሆኜ እየኖርኩኝ ሳለ በሁለተኛው ወር ይመስለኛል ፦
ሲምቢሮዬ ሳንቲም አጥሮት ሳይሰክር ቤት ገብቶ አሽሹን ስላልወሰደ
እየተንዘፈዘፈ አገኘሁት። አቤት ሱሱን ሲያጣ እንዴት ያሳዝናል መሰለህ?
ራሱን ለመቆጣጠር እየሞከረ ጉበት በሚመስሉት ትናንሽ ዓይኖቹ ቁልጭ
ቁልጭ እያለ ያየኝ ጀመር። ዝም ብዬው ልጄን አስተኝቼ አጠገቡ ተቀመጥኩ።
ለብዙ ዓመታት አይቶኝ የማያውቅ ይመስል ልክ እንደ መርማሪ ፖሊስ በዓይኖቹ ዓይኖቼን እየበረበረ
"የት ሄደሽ ነው?" አለኝ። ያላሰብኩት ጥያቄ ስለነበር ቀልቤ ግፍፍ አለ። ምን
ብዬ ልመልስለት............?
'ኧኧኧኧኧ...ኧ..ኧ...የየየየትትትትም አአልሄድኩም'
"እንዴት የትም አልሄድኩም ፣ እቤት ከመጣሁ'ኮ ቆይቻለሁ"
'ማማለቴ'
"ለጠየኩሽ ጥያቄ ለምን በቀጥታ አትመልሽልኝም? ምን ዙሪያ ጥምጥም
ያስኬድሻል! የት ሄደሽ ነበር?" እስከዛሬ ጮሆብኝ የማያውቀውን ጮኸብኝ።
ተስፋ ሲቆርጥ ነው እንዴ እኔን መቆጣጠር ትዝ የሚለው? ከሱ ውጪ የትም
መሄጃ እንደሌለኝ እኔም እሱም ስለምናውቅ ዝም አልኩት። እሱ ቀጠለ
"ሰሞኑንስ ገንዘብ ከየት ነበር የምታመጪው?"
እኔ አሁንም ዝም
"እሺ ዝምታ ካዋጣሽ እሺ" ብሎኝ.......ክፍል21.....እንቀጥለዋለን......
ለአስተያየትና ጥያቄ
@raymondds
ምርጥ የወሲብ ታሪክ በWebsite ለማግኘት ከታች ያለውን link ይጫኑ አዳዲስ ታሪኮች እዛ ላይ ይገኛሉ በቅርብ ቀን በ አማርኛ እና በ ድምፅ ይጀመራል linku
STORY.TEBETA.NET
❥━══━━❥══❥━══━━❥═
ለአስተያየት ወይም የወሲብ ታሪክ
ለመላክ
@raymondds ይጠቀሙ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#share
Join us @wesib_tarikoch
❥━══━━❥══❥━══━━❥═
29.9K viewsedited 17:35