Get Mystery Box with random crypto!

ማንን ነው እግዜር ጥበበኛን የአርያሙን ንጉስ የሚመሰገነውን ያን ስሉስ ቅዱስ | ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

ማንን ነው

እግዜር ጥበበኛን
የአርያሙን ንጉስ
የሚመሰገነውን
ያን ስሉስ ቅዱስ
አንተን የወደደ
ወደ ምድር የላከ
አንዲትን ማህፀን
ምነኛ ባረከ
ደግሞም እናትህን
ያቺን ባለፀጋ
ትወልድ ዘንድ አንተን
ከልቧ ፈልጋ
በአንዲት ልዩ ቀን
ከአንድ አልጋ ውላ
በልብ ሰንጥቅ ደስታ
አንድ ፍቅርን ብላ
ፍቅርን ፀነሰች ፍቅርን ወለደች
ፍቅርን አቀፈች
ደስ እያላት ይኸው
አንተን ለአለም ቸረች
አንተ የልቤ ሰው
በፍቅርህ ጉደኛ
ሰርከ የምማሰው
እኔ ያንተ አፍቃሪ
እኔ ያንተ ወዳጅ
አንተን ከሰጠኝ
ከየቱ ልወዳጅ
ከእግዜሩ ነው ወይ
ቀድሞ ካሰበክ
ወይስ ከእናትህ
ዘጠኝ ወር በሆዳ አንተን በታቀፈች
ስለየትኛው ልስብክ
ወይስ ያቺን ቀን
አንተን ያወኩባት
በልቤ ላኖርህ
በእድሜ ያሰብኳት
ወይ ደሞ ቅድስት
አንተ የኔ ተስፋ
ሆነህ የመጣህ ቀን
ህመሜ ሊጠፋ
እና ልጠይቅህ
እግዜሩ ሲያስብህ
እናትህ ስትወልድህ
እኔ አንተን ሳውቅህ
ዳግም ስታኖረኝ
በየትኛው ቀን ነው
አንተን ለኔ ያደለኝ
ማንን ነው ማመስገን
ማንንነው ማወደስ
የግኝትህ ቀን ሁሉ ለህይወት መዓዛ ነው
አንተነትህ አደስ
(እንኳን ተወለድክልኝ )
.
.
.
.