Get Mystery Box with random crypto!

. .. .. .. ... ለእነሱ ምንም ማለት አልነበረም እንደመዝናኛ ወይ ደሞ ከሱስ ስሜታቸው | ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

.
..
..
..
...



ለእነሱ ምንም ማለት አልነበረም እንደመዝናኛ ወይ ደሞ ከሱስ ስሜታቸው መብረጃ ::አንደበት ለከት አለው ልቅ ሲሆን ስንቱን ይወስዳልና: እንዲህም አለ እንዴ አስብለው ስንቶች ያለ ስማችን ስም ሰጥተው አፋችንን አስያዙን: ምክንያቱም እንናገር ብንል እንኳ ሌላ ሀሜት እናተርፋለን አይገርምም ህይወት ግን ቀስ እያለች ነው ምታስተምረው ::ስለራስ ከራስ በላይ ማን? ሀቃችንን እውነታችንን እያወቅን እነሱ በዘሩት ዘር ከልባችን መከፋትን አጨዱ እናም ስኬታቸው ነበር ሆነላቸው ለመናገር አንደበታችን ከበደው ምክንያቱም ያለ እውነቱ እውነት መሳይ ተጠየቀ ቢችል እንኳን ንግረቱ ይታመን ይሆን? ሰው ግን የራሱ ሞልቶለት ይሆን ስለሰው እየኖረ ያለው? ግን እኮ ቢያንስ ማውራት ካልቀረ መፍጠራቸው ካልቀረ ምን ነበረበት በክፉ ፈንታ ጥሩን ቢያስቡልን በነቀፌታው ፈንታ ሙገሳን ቢያበጁ ጥሩ አሉባልታ ከምናለቅስበት ይልቅ ምንስቅበትን አላውቅም እንዲያ ቢሆን ግን ምነኛ ነበር (ብቻ ግን ለእነርሱ ምንም ማለት አልነበረም ለእኛ ግን...........)
.
.
.
.
.
ፍቅር ያሸንፋል