Get Mystery Box with random crypto!

' #ፍርሃት ' ስሜታቸውን አሸንፈው እግዚአብሄርን ለማስደሰት የቆረጡ ብዙ ወጣቶች ወደ ትዳር | Purity Tube

' #ፍርሃት '

ስሜታቸውን አሸንፈው እግዚአብሄርን ለማስደሰት የቆረጡ ብዙ ወጣቶች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት የግብረስጋ ግንኙነት ፈፅመው ስለማያውቁ የሚጋሩት አንድ የጋራ ስሜት አላቸው

እሱም 'ፍርሃት' ነው

በወንዶቹ በኩል "ምናልባት ባላረካት እንደወንድ አትቆጥረኝ ይሆን?" የሚለው የብዙዎች ፍርሃት ነው፡፡

ሴቶች ደግሞ "ምናልባት ብዙ ቢያመኝ ደስታችንን ወደ ሰቀቀን እቀይረው ይሆን?" የሚለውን ፍርሃት ይጋሩታል፡፡

እውነቱ ግን እነዚህ ፍርሃት የሚመስሉ ስሜቶች አንድ ህፃን ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ከሚሰማው ፍርሃት የተለዩ አለመሆናቸው ነው፡፡

እግዚአብሄርም ቤተሰብም 'ይሁን' ባለው ነገር መጨናነቅ ተገቢ አይደለም፡፡

አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር በሁለት ተጋቢዎች መሃል የግብረስጋ ግንኙነት መጣጣም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የሚሄድ ነገር መሆኑን ነው፡፡

ይልቁንም እግዚአብሄርን በማያከብርና ጊዜያዊ ስሜትን ለማርካት ሲሉ ብቻ ከጋብቻ ውጪ የግብረስጋ ግንኙነትን የተለማመዱ ሰዎች ከእርካታ ይልቅ የፍርሃት ሰለባ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡

ምክንያቱም ገና ከመጀመሪያው ነገሩን የሚጀምሩት"ወይኔ ሃጢያት ነው እኮ!" ፣ "አረግዝ ይሆን?" ፣ "ታረግዝብኝ ይሆን?" ፣ "ቤተሰብ ቢያውቅብንስ?" ፣ "HIV ብያዝስ?" ፣ "ለጓደኞቹ/ቿ ስለእኔ መጥፎ ነገር ቢያወራስ/ብታወራስ?" እና ከመሳሰሉ አስፈሪ ሁኔታዎች ጋር ፊትለፊት በመጋጠም ነው፡፡

ስለዚህ እስከ ጋብቻችሁ ቀን ድረስ በድንግልናና ስሜታችሁን በመግዛት የቆያችሁ ተጋቢዎች ሁሉ ፍርሃታችሁ ተፈጥሮአዊና የሚጠበቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን "You will be fine "

በቅርቡ ለሚያጋቡ ወዳጆቻችዎ #ሼር ያድርጉ

#couples
#General

@PurityTube
@PurityTube