Get Mystery Box with random crypto!

ፍፁም የሆነ ትዳር እንዲኖርህ መጣርህን አቁም!! በእውነቱ ከሆነ 'የተሻለ ትዳር' እንዲኖርህ | Purity Tube

ፍፁም የሆነ ትዳር እንዲኖርህ መጣርህን አቁም!!

በእውነቱ ከሆነ 'የተሻለ ትዳር' እንዲኖርህ ባትጥርም መልካም ነው!!

ይልቁንም ለራስህ የተሻለ ማንነት ለመፍጠር ትጋ!!

ትኩረትህ እግዚአብሄር አንተ እንድትሆን
የሚፈለግውን አይነት ሰው መሆን ከሆነ የዚህ ነገር ውጤቱ ይህ ነው
ሚስትህ የተሻለ ባል ይኖራታል የተሻለ ትዳርም ይኖራችኋል

እርግጥ ነው ከሚስትህ ጋር የተሻለ ተግባቦት መፍጠር መቻል አለብህ፡፡

ግጭቶች በሚኖሯችሁ ጊዜ ለራስህ ተሟጋች ልትሆንና ጭራሽ እሷን ላታዳምጣት ትችል ይሆናል፡፡

መፅሀፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ያስተምርሃል፡፡

" ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤" ያዕ 1: 19

መልስ ለመስጠት ሳይሆን ሚስትህን ለመረዳት የምታዳምጣት ከሆነ የተሻልክ ሚዛናዊ ሰው ሆነሃል ማለት ነው፡፡ የዚህ ነገርም ውጤት ከሚስትህ ጋር የሚኖርህ መልካም ተግባቦት ነው ማለት ነው፡፡

#Married


@Appeal4purity
@Appeal4purity