Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? አመሠራረቱ፥ በኦሪት ዘፍጥረት 1፥28 ላይ እግዚአብሔር አም | Purity Tube

ስለ ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አመሠራረቱ፥ በኦሪት ዘፍጥረት 1፥28 ላይ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ
እንደፈጠረው ይገልጻል። ምዕራፍ 2፥18ደግሞ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለምና
ሴት እንፍጠርለት ይላል። በምዕራፍ 2 ስአዳም እርሱን የምትመስልና የእርሱን ኑሮ የምትካፈል
ፍጥረት ሌላ አልተገኘስትም ይላል።

እነዚህ አባባሎች አንድ ብቸኛ የሆነውን ሰውን አንድ ሌላ ረዳት እንዳስፈለገው፣ ያለዚያች ረዳት
ደግሞ ከባድ እንደሆነ ያስተምረናል። እነዚሁ ዓረፍተ ነገሮች በደምብ ሲመረመሩና ሲታዩ ሰው
ከሌላው ፍጥረት ለየት ያለና ብርቱ ጥንቃቄ የተደረገለት መሆኑንም ያስተምራሉ። ከዚህ በተጨማሪ
የአዳምን ብቸኝነት በዙሪያው ያሉ የእንስሳትና የአራዊት ክምችት፣ የገነት መዓዛና ፍራፍሬዎች
ባዶነቱን ሊሞሉ ወይም ደስታ ሊስጡት አልቻሉም። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው ሁሉም
ፍጥረታት ከተቃራኒ ጾታ ጓደኞቻቸው ጋር ሲጫወቱ ለአዳም ምንም ዓይነት የደስታውም ሆነ የኃዘኑ
ተካፋይ ሊሆኑለት አልቻሉም። እነሱን ትክ ብሎ ከማየት በስተቀር ምንም አልፈየዱለትም። በዚያ
ፈንታ ይልቅ እነዚያ ሲጫወቱና እሱን ሲያስደስቱት የዋሉት ፍጥረታት ሁሉ ወደየማደሪያቸው ሲጓዙ
አዳም ብቻውን ፈገግ ብሎ መቅረት ብቻ ሆነ። ይሄ ብቸኝነት ነው እንግዲህ እግዚአብሔር
እንዲያስብለት ያደረገው። ይህ አኗኗር ለአዳም መልካም አልነበረም፤ ለአዳም መልካም የሚሆን
ረዳትና አጫዋች እርሱን የሚመስልና የእሱን ኑሮ የሚካፈል ሊኖር አስፈለገው። ያ ካልሆነ በቀር
አዳም ደስተኛ ሊሆን አይችልም። ስለሆነም እግዚአብሔር የፈጠረውን አዳምን በላዩ ላይ እንቅልፍ
እንዲመጣ አድርጎ ከእርሱ ከጎኑ ረዳት የምትሆነውን ሴትን ሰጠው። ይህ እንግዲህ የመጀመሪያው
ጋብቻ ስለሆነ አዳምና ሔዋንን የገነት ሙሽሮች ብለን ልንጠራቸው እንችላለን። የአዳምና የሔዋን
አባት የሆነው እግዚአብሔር በብቸኝነት ጠውልጎና ተስፋ ቆርጦ ለነበረው አዳም የሔዋንን እጅ ጎትቶ
ሲሰጠው ከየት እንደመጣች ስለተረዳ «ሥጋዋ ሥጋዬ አጥንቷ አጥንቴ» በማስት ደስ ብሎት ኑሮውን ጀመረ።
ስለዚህ ነው ጋብቻ የተፈጠረ እንጂ የተፈለሰፈ አይደለም የምንለው።

#General

@PurityTube
@PurityTube