Get Mystery Box with random crypto!

Love - ፍቅር

የቴሌግራም ቻናል አርማ lovefkr — Love - ፍቅር L
የሰርጥ አድራሻ: @lovefkr
ምድቦች: የአዋቂዎች ይዘት (18+)
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.65K
የሰርጥ መግለጫ

ስለተቃራኒ ጾታ ግንኙነት አብረን እንድንማማር መድረኩን ከፍተናል። በሚመቸን እንሳተፍ።
@kkzinu1
@TgKassa
@Nahooom
@Yona4501
@Fkr_Orthodox
https://t.me/lovefkr
https://t.me/lovefkrlove
youtube.com/lovefkrlove
https://LoveFkrLove.com
www.facebook.com/lovefkrlove

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-05 16:33:41 ፀጋ አግኝታ ከሰማያት
ብሩክ ነች እውነት ለሚያያት


149 views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 17:53:59 ፍቅራችን ድንበር ሳይኖረው
      ዘር ቀለም ፍፁም ሳይለየው
      በኖረው አብሮነታችን
      እናብር ላንዷ ጎጆአችን


989 viewsBelay, 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 07:26:22 አዳምና ሄዋን በገነት ሆነው አትብሉ የተባሉትን በሉ። ህግንም ተላለፉ። ይኸው ዛሬም ምንም ሳናጣ የተከለከልነውን በማድረግ ሃጢያት እንሰራለን፤ እንበድላለን፤ እናስቀይማለን። ሃጢያት የሰው ልጅ ባህሪ ነው።

ነገር ግን እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ ስለወደደ በይቅርታ ከሃጢያታችን የምነነፃበት ሁለተኛ እድል ሰጠን።

ይቅርታ ሁለት አይነት ትርጉም አለው። አንድ የእግዚአብሔርን ህግ በሃጢያት ስንስት፡ ተፀፅተን ይቅርታ የምንጠይቅበት፣ በዚህም ካለፈ እድፋችን የምንነፃበት ነው።

ሁለተኛው እኛ የበደሉንን ይቅርታ የምናደርግበት ነው።

ሁለተኛው ለመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ እንደሆን አስበንበታል።
ለሌሎች ይቅርታ ስናደርግ የእግዚአብሔርን ይቅርታ አድራጊነት የምንመሰክርበት ነው።
ይቅርታ እንዲደረግልን፡ ይቅር ማለት አለብን!

ተቀይማችሁ፡ በቂም የምትኖሩ፡ ሽንፈት፡ የሚመስላችሁ ካላችሁ ፡ ከፈጣሪ ህግ ይሉኝታ የባሰባችሁ የሚባክን ግዜ የለምና ዛሬውኑ ከልብ ይቅር በሉ።

ይቅርታ ያደረጋችሁበት፡ ወይም ይቅርታ ለማድረግ የከበዳችሁ አጋጣሚ አለ? እስቲ አካፍሉን።
@LoveFkrLove
1.8K viewsBelay, 04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 20:00:13 ትናንት ስታዜመው የነበረ፣ ለዛሬ ያላደረ አስተሳሰብ አለህ?…

አይግረምህ!!.. ይልቅ ዛሬ የምታወግዘው ሃሳብ የነገ ተረኛ ቅኝትህ ሆኖ ሊከሰት እንደሚችል አስብ… በመኖር ውስጥ ወጥ የሚባል ቅኝት፣ የማይለወጥ የሚባል የማሰብ ፍኖት የለም… ‘ልክ’ ይመስለኝ ነበር ያልከውን መረጃ ‘ልክ እንዳልሆንክ’ ባሳየህ የዛሬ ክስተት ለመለወጥ ስትንደረደርም ሆነ ሽንጥህን ገትረህ የተሟገትክለት ሃሳብ ነገ ደርሶ ብን ሲልብህ ስታይ ውል አልባነት አይሰማህ

በሕላዌ ሕዋ ውስጥ ወዲህ ቢሉት ወዲያ የማይለወጥ አንድ ነገር እውነት ብቻ ነው… እውነት እውነትነቷ ነው ውበቷ - እውነት እውነት ትባል ዘንድ የድጋፍ ሰልፍ አትፈልግም… በራሷ የምትቆም ጽኑ ናት… የተከታዮቿ ማነስና መብዛት የእውነትነቷን ሞገስ አይነቀንቀውም… “The truth is like a lion; you don’t have to defend it. Let it loose; it will defend itself.” እንዲሉ... እስስት ሆኖ የሚዘልቀው ምን ይሆን ታዲያ?… መረዳትህ ነው… ግንዛቤህ… የእይታ አንፃርህ /Level of understanding/…

የብዙ ውይይቶች ውጤት ጽንፍ ለጽንፍ በሚተያዩ ሃሳቦች መደምደም የየትኛውንም ወገን ትክክለኛነት አይናገርም… የማንኛውንም ስህትነትም አይገልጽም… የየወገኑን አንፃር እንጂ… ስለዚህ እንደኔ ካላሰብክ ብሎ ሙግት መግጠምም ሆነ የሌላውን ሌላነት የመግለጽ ነፃነት መጋፋት በደል ነው… የእውነት ተክለ ቁመና በአንፃራዊነት ባይዳኝም ታዳሚዎቿ ግን በየልካችን የምንሰፋው ‘እውነት’ ያለን መሆኑ እርግጥ ነው…

ፈጣሪ ሕይወትን ሳንሰለች እንዋብባት ዘንድ የተለያየ መነጽር እያቀበለን የእውነት ፀሐይ ከደመና ጥጥ ውስጥ ተፈልቅቃ ስትወጣ ያለውን ሂደት ጊዜ በሚሉት ሃዲድ ላይ ሆነን እንመለከታለን… ግና የገባን እንጂ ደርሶ የጨበጥነው እውነት የለንም!!!

እና ምን ለማለት ነው… ‘ፍጹም እውነትን ይዘናል’ ከሚሉኝ ይልቅ ‘እውነትን እየፈለግን ነው’ በሚሉኝ ሰዎች ዙሪያ መገኘት ያስደስተኛል…

ደምስ ሰይፉ

#ውብ_ምሽት
@Lovefkrlove
@lovefkr
724 viewsZizuye , 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 20:00:05
662 viewsZizuye , 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:09:08 #ብቁ_ናችሁ!

ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!

እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡

እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!

አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡

በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

ውብ ምሽት

@lovefkrlove
@Lovefkr
2.0K viewsZizuye , 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 19:59:27 ከምንም በላይ አንዳችንን ከሌላኛችን የሚለየን ነገር ቢኖር ለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም ምስል በእንግሊዘኛው ደግሞ "Self Image" ነው። ሁላችንም በዚህ አለም ላይ ስንኖር የኑሮዋችን መጠንና ልኩ የሚወሰነው ለራሳችን ባለን አመለካከት ወይም በአይምሮዋችን ውስጥ ስለራሳችን በምንቀርጸው ምስል ነው። ባህሪያቶቻችን፤ ውሳኔዎቻችን፤ አጋጣሚዎቻችንና በህይወታችን የምንስባቸው ሰዎች በሙሉ ለራሳችን ባለን አመለካከት ተጽዕኖ ስር ይወድቃሉ።

ለራስ የሚሰጥ አመለካከት (self Image) በህይወታችን እጅግ ወሳኝ ነገር ነው። አንድ ሰው ስኬታማና ደስተኛ ሊሆን የሚችለው ለራሱ የተስተካከለና አወንታዊ አመለካከት ሲኖረው ብቻ ነው። ችግሩ ይህንን እውነታ ማንም ሰው ከልጅነታችን ጀምሮ ስለማያስተምረን አብዛኛዎቻችን ለራሳችን የተሳሳተ አመለካከት በመያዝ እናድጋለን። አቅምና ችሎታችንን የሚገድቡ እምነቶች "Self Limiting beliefs" ሳናውቀው በአይምሮዋችን ውስጥ ስር ይሰዳሉ። እኒህ አመለካከቶቻችን ናቸው የምንፈልገውን ኑሮ እንዳንኖር እንቅፋት የሚሆኑብን።

ህይወታችንን ሊቀይሩ የሚችሉ እውነታዎች በሙሉ ቀላልና ያልተወሳሰቡ ሀሳቦች ናቸው። ምናልባት ለዛም ይሆናል በቁም ነገር ወስደን የማንተገብራቸው። እኛ ሰዎች በተፈጥሮዋችን የተወሳሰበና ከባድ ነገር ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ይመስለናል። ለችግሮቻችን መፍትሄ ስንፈልግ እንኳን ቀለል ያለ ሃሳብ አንቀበልም። እቃ ስንገዛ የተወደደው እቃ ሁሌም ከረከሰው የተሻለ ይመስለናል፤ በወረፋ ካልተሰለፍን በቀር የምናገኘው አገልግሎት ጥራት ያለው አይመስለንም።

ተሻምተን ካላገኘናቸው በቀር ነጻ ለምናገኛቸው ነገሮች ዋጋ አንሰጥም። እራሳችንን ለመለወጥ ስናስብም እንደዛው፤ በቀላሉ አስተሳሰባችንን በመቀየር ህይወታችንን መቀየር እንደምንችል አምነን መቀበሉ ይከብደናል። ሰው አስተሳሰቡን በመቀየር ኑሮውን መቀየር እንደሚችል ለብዙ መቶ አመታት ሲንገር የነበረ ቢሆንም፤ እኛ ግን ይህን ለመረዳት አልፎም በቀላሉ ስራ ላይ ለማዋል አልቻልንም።

እያንዳንድችን ስለራሳችን በአይምሮዋችን የምንቀርጸው ምስል አለ። ይህ ምስል መልካም ምስል ካልሆነ በኑሮዋችን ላይ የሚጸባረቁት እውነታዎችም ከዚህ ምስል የተለዩ አይሆኑም። በተቃራኒው ስለራሳችን ያለን አመለካከት ወይም በውስጣችን የምንስለው ምስል መልካም፤ጠንካራና አወንታዊ ከሆነ፤ በኑሮዋችን ላይ የሚንጸባረቁት እውነታዎች በሙሉ የአወንታዊው አመለካከታችን ነጸብራቆች ይሆናሉ።

ይህ ለራሳችን የምንሰጠው አመለካከትና ግምት ነው፤ በራሳችን ላይ የሚኖረንን እምነት የሚወስነው። በራስ መተማመናችን የሚበቅለው ለራሳችንን ባለን አመለካከት አፈር ላይ ነው።በትምህርትም ሆነ በስራ፤
በፍቅርም ሆነ በግል ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ውጤቶች ለራሳችን ካለን አመለካከት የሚመነጩ ናቸው።

ውብ አሁን
@lovefkrlove
@Lovefkr
2.2K viewsZizuye , 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:59:21 ባለትዳር ወንድ "እስቲ ላስብበት" ካለ ምን ማለቱ ነው?

ላስብበት (30%)
├ Adi
├ Mikias
├ Dõñ Ãbēňĩ
├ Grace Asefa
├ ሰራዊት ሰሜ
├ Dinberu Workineh
├ a
├ Alex Scarce
├ 𝓯𝓾𝓪𝓭
├ Şiś ýę 30 ✟ ✞ 6
├ Dami
├ sami Aklil
├ አብድሬ ye እናቱ ልጅ
├ prince teddy
├ Rich
├ ደስየ
├ Fa fi
├ Ⓗ ye Tewahedo Ligi
├ Melese Markos
├ Redina
├ Ŕòžì
├ medina medina
├ Mohammed kedir

├ Yèñé...
└ እሙ ሂባ

አልፈልግም (30%)
├ Mehabaw Bayu
├ Yoooo Mom
├ Birta
├ 𝓪𝓻𝓪𝓰𝓪𝔀 𝓫𝓪𝔂𝓾𝓱
├ Sindew Endris
├ Ramee Rami
├ ሁሉም ያለፋል
├ €sha €yob
├ Jack
├ Netsi
├ Asre unique
├ Emishaw Goshu
├ Yonas Berhanu
├ GERESU
├ Matthew T
├ Tilahun Abebe
├ ማክ ሰኞ
├ አሁን ገባኝ ገና የለቺም ከጎኔ
├ 𝓽𝓲𝓻𝓾
├ አቡ ኢምራን
├ zeleke Amare
├ Muhammed Nasir
├ Âbbï łøvê Âbbï
├ Geners
├ K̶e̶y̶ o̶f̶f̶ l̶i̶f̶e̶
└ "@.@ziz ⒷⓊteflica

ሚስቴን ላስፈቅድ (26%)
├ Mickey
├ H.
├ Ê&Ã Ñ ã` ĝ ñ
├ Homi
├ እናቴ
├ ነገ ሌላ ቀን ነው!!
├ Endash
├ ሰሚረ
├ ፋሲል ከነማ
├ laafaa Barriii Dukaan Hamataa Kasim
├ Të Ä
├ Zer hun
├ Getachew Selemon
├ Suhail Abdella
├ እመቤት
├ Abey Lex
├ Egzabher yimasgen
├ Arersa Abera
├ Habib Siraj
├ Kamaz_Master

└ Peace Loving

የተለየ አስተያየት አለኝ (14%)
├ ኡሙ ሂክማ ቢኢዚኒላህ
├ Kiddy
├ Shumie Anley
├ ተመስጌን ጌታቸዉ
├ ያሲን መሀመድ
├ መልሳሲስይ

├ beti tigist
├ Dj AD Ethio
├ 🇾 🇪 🇸 🇪 🇹 🇱 🇮 🇯 🇪
├ Erkyihun
└ ያአላህ ባሬያ ነኝ

86 pollrbot.com/p/HfHxjWMRYQ==
2.8K viewsBelay, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 21:48:15
  የደስታ ሁሉ ምንጭ አእምሮ ነው ፣ የመከራ የሥቃይ ምንጭም ራሱ አእምሮ ነው ፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በጥልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና የነፃነት ውጤት ማግኘት እንችላለን ፡፡

ወዳጄ ሆይ አንድን ነገር ለመረዳት ስትፈልግ ያንን ነገር መውደድ ይኖርብሀል ፣ስትወደው ሕይወት ቀላል ይሆናል። ከዚያ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ነገሮችን ማስተዋል እና መረዳት ትጀምራለህ።ሁሉንም ለመረዳት ግን መጀመርያ በልብህ ውስጥ ፍቅር ሊኖርህ ይገባል ፡፡

ማንነትህን ጠንቅቀህ ስትረዳ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ። አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

ይህን ባስተዋልክ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ ፣ፍቅር ሲኖርህ ደግሞ የማንም ትዕዛዝ ሳያስፈልግህ የሰዎችን ሥቃይ የሚያስታግስ መንገድ ትፈጥራለህ።

ውብ ምሽት ፍቅሮችዬ

@Lovefkrlove
@lovefkr
3.6K viewsZizuye , 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 21:29:20   የደስታ ሁሉ ምንጭ አእምሮ ነው ፣ የመከራ የሥቃይ ምንጭም ራሱ አእምሮ ነው ፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በጥልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና የነፃነት ውጤት ማግኘት እንችላለን ፡፡

ወዳጄ ሆይ አንድን ነገር ለመረዳት ስትፈልግ ያንን ነገር መውደድ ይኖርብሀል ፣ስትወደው ሕይወት ቀላል ይሆናል። ከዚያ ስሜት በሚነካ ሁኔታ ነገሮችን ማስተዋል እና መረዳት ትጀምራለህ።ሁሉንም ለመረዳት ግን መጀመርያ በልብህ ውስጥ ፍቅር ሊኖርህ ይገባል ፡፡

ማንነትህን ጠንቅቀህ ስትረዳ ዋጋህን ታውቀዋለህ ።የምትኖርበትን እና የምትኖርለትን ትለያለህ ።ወደ አዚች ምድር የመጣኧው ለምክንያት ነው ። አንተ የዚህች አለም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ ።ዋጋህን ባለመኖርህ አትተምን በመኖርህ እንጂ።የአንተ መኖር ለሌሎቹ ጡቦች ድጋፍ እንዲሁም ለግንባታው ውበት አስፈላጊ ነው።

ይህን ባስተዋልክ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ ፣ፍቅር ሲኖርህ ደግሞ የማንም ትዕዛዝ ሳያስፈልግህ የሰዎችን ሥቃይ የሚያስታግስ መንገድ ትፈጥራለህ።

#ውብ_ምሽት

@Lovefkrlove
@Lovefkr
4.9K viewsZizuye , 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ