Get Mystery Box with random crypto!

.' ከአንድ እርምጃ ቡኋላ እሾሁ ይታይሻል አይደል!? ታድያ ስለምን ለመራመድ ታኮበኩቢያለሽ?' ጠየ | ግጥም፥ ትረካ ፥የፍቅር ደብዳቤዎች

." ከአንድ እርምጃ ቡኋላ እሾሁ ይታይሻል አይደል!? ታድያ ስለምን ለመራመድ ታኮበኩቢያለሽ?" ጠየቀኝ

" መሄድ ስላለብኝ። ከመጣሁበት የጭቃ እሾህ መንገድ ይሄ ኢምንት መስሎ ስለታየኝ ወይ ደሞ እኔንጃ! ግን'ኮ ምናልባት ይህ እሾህ ቢወጋኝ እግሬን ነው የሚያደማው ፤ በርግጥም መርቅዞ ሲታከክ ሰላም የሚሰጥ ቁስል ይሆነኛል። እመነኝ! አትስጋ ፤ እሄዳለሁ። ይልቅ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ? የልብን ቁስል በየት በኩል ገብተው ቢያኩት ይሆን እረፍት የሚሰጠው?" አይኑን እያየሁ ጠየኩት። ትንፋሹን እንኳን ለመልስ'ነት አላቀረበልኝም። በቀስታ አቀፈኝ። ከቃሉ በላይ እቅፉ መልስ ሆነኝ መሰለኝ እኔ ቀጠልኩ።

" ታውቃለህ እጄን ከእጁ መፈልቀቄ አጥብቆ እንዲይዘኝ ነበር! ግራውን መርጬ ስሄድ መንገዴን እንዲወደው ነበር! ስገፋው እኮ እንዲፈልገኝ አጥብቄ መፈለጌ ነበር ! ራስ ወዳድ ነኛ!? የምርም ዝም ሲለኝ ምንምነቴን እየነገረኝ ይመስለኝ ነበር፤ በርግጥም ነው። ነፍሴን ሳቀርብለት ከሌለኝ ላይ ሞልቼ ቢሆንም ነፍሱን የሰጠኝ ግን የተረፈለትን ነበር። ምናልባት ለምን ብዬ አለመጠየቄ ስህተት ቢሆንም ማስመሰሉን እንዳይደግም ማድረጌ ግን ልክ ነበርኩ። በመሆን መጉደል ግን ምንኛ ህመም ነው!? " እቅፉ ሰላም ሰቶኛል፤ አልፌው እንዳልሄድ ጨርሶውኑ አድክሞኛል።

"የልብ ቁስል እንዴት ነበር የሚታከከው!?" ስለመንገዴ እያመነታሁ ጠየኩት
"እንደዚ" ደግሞ አቀፈኝ። ልቤ ውስጥ የማላውቀው እፎይታ ተሰማኝ
"እወድሃለሁ!" አልኩት
"አፈቅርሻለሁ!"

ዳግመኛ እጆቼን ያዛቸው፤ ሊለቀኝ አይፈልግም። አይኖቼ ውስጥ ምስሉን ፍለጋ ተተከለ ፤ ራሱን የማያውቀው ያህል ሊያጣው አይፈልግም። የተረፈ ነፍሴን ሳይሆን በእቅፉ አድሶ ሰላም የሰጣትን ነፍስ ያለማንም ከልካይ አስረኩብኩት።

ወትሮውኑም ያላየነው አንድ ማንም ነበር....!

ፍቅር ያሸንፋል