Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 88.32K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-11 21:47:49 ስለ ፍልስፍና
@Zephilosophy
@Zephilosophy

በአገራችን በፍልስፍና ምንነትና ፋይዳ ላይ እስከ ዛሬ ሲንፀባረቅ የቆየው አመለካከት አሉታዊነቱ የሚያመዝን
መሆኑ ከዚህ የእውቀት ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም እንዳናገኝ አድርጎናል። እናም ብዙዎች ስለፍልስፍና ያላቸውን አሳቤ ስንመስከት-ከፈጣሪ ጋር መጋጨት፣ ከእውነት ከመራቅ እንዲሁም ከእብደት ጋር የተያያዘ ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ ይህ የብዙዎች እምነት ይሁን እንጂ፣ ፍልስፍና ግን በተቃራኒው እውነትን ከመፈለግ- አልያም ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ ከመመርመር ባሻገር ስለፍትህ፣ ስለፖለቲካ፣ ስለ ስነ ውበት፣ ስለ መልካም ስነ-ምግባር አንዲሁም ስለመሰል የትምህርትና የአስተሳሰብ ዘርፎች እንደ የአቅጣጫው የሚያጠናና የሚመረምር አራሱን የቻለ ትልቅ የእውቀት ዘርፍ ነው።

ፍልስፍና ከራሱ አልፎ ለሌሎች ታላላቅ የእውቀት ዘርፎች መሰረት የሆነና የሰው ልጅ ዛሬ እዚህ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ አስተዋፅዖ ያደረገ ነው። ለሁሉም ሩጫ ፍልስፍና የጀርባ አጥንቱ ነው፡፡ ምሰሶ ከሌለው ጎጆ እንደማይቆም ሁሉ፤ ፍልስፍና ከሌለ እውቀትና እውነት አንደጉም ይተናሉ። ምናልባትም ሀገራችን በሌሎች የትምህርት ዘርፎች ያሳየችውን ትጋት ለፍልስፍናም አቋድሳው ቢሆን ኖሮ ፣ ሌሎች ቤት የሚያበራው ሻማ ፣ ጨለማ ውስጥ ሆነን ባላደነቅን ነበር ፣ፍልስፍና ዳቦ አያበላም እያልንም በፈላስፋው የተጋገረውን ዳቦ ተሻምተን ለመቋደስ ባልተገደድንም ነበር።

በአጠቃላይ ፍልስፍና ከጨለማ_ወደ ብርሀን፣ ካለማወቅ ወደማወቅ፣
ከባርነት ወደ ነፃነት፣ ከስህተት ወደ እውነት የሚያሻግር ድልድይ ነው።

ድንቅ የፍልስፍና ቻናል ይቀላቀሉ
Join Now

@Zephilosophy
@Zephilosophy
6.3K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-10 08:56:13 “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”

ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡

በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡

ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡

ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡

አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን?

መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች …

• ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት  ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡

• ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡  

• አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡

እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ?

ዶ/ር እዮብ ማሞ
6.7K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-05 11:35:53
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!!

    መልካም በአል!!
8.2K viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 13:36:33 "ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"
8.9K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 07:13:24 ያገዘፍከውና ያሳነስከው

የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡

የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡

ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡

የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ?

ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
13.1K views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 10:54:27
" ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች ”የለውጥ ኩርባ” አለችው።  አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ አሊያም ድርጊቱ የሚቀየርባት ። ወደ ዐዲስ  ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት። ለውጥ ወደ ተሻለ ማደግ ብቻ አይደለምና ኩርባውን ሲታጠፍ ውድቀትም ሊሆን ይችላል። ያች የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች ወይም ዐረፍተ ነገር ወይም አንዲት ቃል ምናልባት አንዲት መሳም ወይም የአንድት ደቂቃ መታቀፍ ወይም.... "

- ከ'ጠበኛ እውነቶች ' መጽሐፍ ገፅ  116

ደራሲ :- ሜሪ ፈለቀ
12.8K viewsedited  07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 08:13:13 ሰዓት ተሸካሚው

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ማዕድ
በጥበበኛው ሰለሞን

“አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”

ሰዓት ተሸክሞ የሚዞር አንድ ሰው፣ በመንገድ ያገኘውን አንድ ህጻን ልጅ ጠየቀ ...

ህጻኑም ያለማመንታት “አምስት ሳንቲምም አልከፍልም" አለ፡፡

ዳግም ሰዓት ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ተመልሶ መጣና ትናንት ህጻን የነበረውን የዛሬውን ወጣት ጠየቀው “አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”

“ቢበዛ አንድ ወይም ሁለት ብር” ወጣቱም መለሰ፣ ግድ በሌለው አኳሃን፡፡

ይህ ወጣት ሸምግሎ ለሞቱ አንድ ሐሙስ በሚጠባበቅበት ጊዜ ሰዓት ተሸካሚው ተመልሶ መጣ፡፡

“አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ  ‌ ምን ያህል ትከፍላለህ?”

"በባህር ውስጥ ያሉ እንቁዎችን፣ በሰማይ ላይ ያሉ ከዋክብትን ሁሉ እከፍላለሁ” ሽማግሌው መለሰ፡፡

ከፍልስፍና እሳቤዎች መኻል ላይ ልናነሳው የወደድነው ጊዜ ነው፡፡ የሰው ልጅ ስለ ሁለንተና ባወቀ እና ይበልጥ በተራቀቀበት መጠን፣ መልስ አልባ ጥያቄዎችን ያነሳል። ከየት መጣን? ጊዜ መጀመሪያ አለው? ጊዜስ በራሱ ምንድን ነው? በጊዜ መስመር ውስጥስ እንዳሻን ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መመላለስ ይቻለናል?

እነዚህን መልስ አልባ እንቆቅልሾችን ፍልስፍናዊ መልስ እንስጣቸው ብንል፣ ጊዜ በራሱ እንቅፋት ይኾንብናልና ለአሁኑ በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ ይቻላልን? ከተቻለስ ምን ይከሰታል እና ጊዜስ ምንድን ነው የሚሉትን ሃሳቦች ብቻ እናብላላለን፡፡

ጊዜ ሰዓታችን የሚለካው ነገር እንደሆነ እናስባለን፡፡ ምድር ላይ ያሉ ክስተቶችንም በቅደም ተከተል እናስቀምጥበታለን። እናም ጊዜ በእለት ተዕለት መንከላወሳችን ውስጥ ትልቅ ስፍራን ይይዛል፡፡ ጥድፊያችንንም ኾነ እርጋታችንን የሚወስነው ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም እንደምናስበው ወይም ይህ ነው ብለን እንደጠራነው አይነት ጊዜን በቀላሉ ፍቺ ሰጥተን አውቀነዋል ማለት አንችልም። ለብዙ ዘመናት ሳይንሳዊያን እና ፍልስፍናውያን በጊዜ ጉዳይ ሲጨቃጨቁ ኖረዋል።

ፈላስፎችን ብዙው ክርክራቸው የሚያተኩረው፣ አሁን፣ አላፊው ጊዜ እና የወደፊቱ ላይ ነው፡፡ የጊዜን የፍልስፍና እሳቤዎች በሶስት አጠቃለን መመልከት እንችላለን፡-

የአሁናዊነት (Presentism) ፍልስፍና አራማጆች የእውኑ ዓለም አሁንን እና አሁንን ብቻ ይይዛል ይሉናል፤ ትናንት አልፏል እና የእውነት አይደለም፤ ነገም አልደረሰምና የእውነት አይደለም፤ የእውነት የሆነ ነገር ቢኖር አሁን ብቻ ነው፡፡ ያለፈው ትዝታችን፤ ያልደረሰው የወደፊቱም እንዲሁ ትንበያ ብቻ ነው። እውነት የአሁን ቅጽበት ላይ ብቻ ትገኛለች።

በአንጻሩ የአላፊነት (growing-past) ፍልስፍና አቀንቃኞች እውነት አላፊው እና የአሁን ጊዜ ላይ ብቻ ትገኛለች ፤ ያልተከወነው የወደፊቱ ጊዜ የእውኑ ዓለምን አይወክልልንም ይላሉ፡፡ ዳይኖሰሮች የእውነት ናቸው፤ የአድዋ ጦርነት እውነት ነው ሆኖም ወደ ፊት መከሰቱ የማይቀረው የእኔ እና ያንተ ሞት ግን እውነት አይደለም።

ሶስተኛው የጊዜ እሳቤ የዘላለማዊነት(eternalism) ይሰኛል። በአሁን፣ በአላፊ እና በወደፊት ጊዜ መካከል የእውነትነት ልዩነት የለም ይለናል። ለምሳሌ የአዶልፍ ሂትለር በጀርመን መነሳት የአላፊ ጊዜን አይጠቁምም፤ ላንተ ያለፈ ጊዜ ቢሆንም ለአርስቶትል ገና ያልተከሰተ የወደፊት ክስተት ነው።

ሆኖም ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?

ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን፤ ህንዶች፣ ግብጾች እና ግሪካውያን ጊዜን በተለያዩ መንገዶች ይገልጹት ነበር። ጥንታውያኑ ሰዎች ስለጊዜ አላቂነት ወይም ዘላለማዊነት፣ ስለ ጊዜ እንዲሁ ፈሳሽነት አልያም ዙሮ ገጠምነት (ለምሳሌ ቀን ይደጋገማል፤ አመትም እንደ አዲስ ይጀምራል) የተለያዩ መላምቶች ነበሯቸው፡፡

ሬኒ ዴካርቴ 'ጊዜ ምን ማለት ነው?' ለሚለው ጥያቄ እንዲህ ይለናል:- “ቁስ አካሎች፣ ለምሳሌ አንተ ዘላለማዊ አይደለህም። እንዲያውም ከቅጽበታት ያለፈ እድሜ የለህም፡፡ በአንጻሩ እግዚአብሔር አንተን ጨምሮ ዓለምን በሙሉ በየቅጽበታቱ ይፈጥራል። ከአምስት ደቂቃ በፊት ያለው ዓለም እና አሁን ያለንበት ዓለም ይለያያል። ከቅጽበት በኋላም የሚኖረው ዓለም፣ አሁን ላይ ካለው ዓለም ይለያል። እናም የአሁኑን ቅጽበት ከቀጣዩ ቅጽበተ ዓለም የሚያቆራኘው ነገር ምን ይባላል?... ጊዜ። እግዜርም በእያንዳንዱ ቅጽበት አንተን እና ዓለምን ደጋግሞ ከጥቂት ልዩነቶች ጋር ይፈጥርሃል።”

ሁሉም እንስሳቶች ማለት ይቻላል አሁንን ነው የሚኖሩት፤ ሆኖም ሰው ትንኝ አይደለምና ትናንት ምን እንደነበር ያስታውሳል፤ ነገም እንደሚመጣ ያውቃል። ለጊዜም ያለን እይታም ከእንስሳት ለይቶናል፤ እናስባለን ... እናሰላስላለን እንወስናለን፡፡ ትናንት የረገጥነውን ፈንጂ ዛሬ ላይም መልሰን አንረግጠውም፡፡ ተፈጥሮ ጊዜን እንድናውቅ አድርጋናለች። ጊዜ የእውነት ያለ ነገር ነው? መስመሩስ እንዲሁ እንደ ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚፈስ ነውን? መጀመሪያ እና መጨረሻስ አለውን?

@Zephilosophy
@Zephilosophy
13.7K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 19:50:44 ከወሲብ ባሻገር

ኦሾ፣ አንተ ወሲብ የማይረባ ነገር መሆኑን ስትናገር ሰምተን እንደገና ሞክረነው ነገር ግን አልገባንም የማይረባ የሆነው ምኑ ላይ ነው?”


እየነገርኳችሁ የነበረው ስለ ሌላ ነገሮች ነው፡፡ እሺ እነሱን ሞከራችኋቸው፡፡ በየቀኑ ስለ መመሰጥ እነግራችኋለሁ ነገር ግን እያረዘማችሁ (ላለማድረግ እያዘገያችሁ) ወሲብን ግን ትሞክራላችሁ አያችሁ ይህ ነው እንግዲህ ቀሽምነታችሁን የሚያሳየው፡፡

ወሲብ የማይረባ አይደለም እናንተ ናችሁ የማትረቡት፡፡ ለዚህ ነው በእናንተ ምክንያት ተራ ወሲብ የማይረባ የማይሆነው፡፡ ማሳደግ ካልቻላችሁ፣ ንቁም ካልሆናችሁ ቀሽምነቱን ልትረዱት አትችሉም፡፡ በተመሳሳይ ደረጃ ሆናችሁ መገንዘብ አትችሉም፡፡

ወደ እብዶች ቤት ሂዱ አንድ እብድ ፈልጉና “እብድ ነህ" በሉት ነገር ግን ቅሉ ፍፁም ይናደድባችኋል፡፡ ማንም እብድ  መሆኑን አይቀበልም፡፡ "ምን እያወራችሁ ነው? ከእኔ በስተቀር አለም በሙሉ እብድ ነች" ይላችኋል፡፡ አንድ እብድ እብድነቱን አመነ ማለት በእርግጠኝነት ከእብድነት አለም እየወጣ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡


መመሰጥን ማግኘት ካልቻላችሁ የተሻለ መመልከት፣ ከተለየ አቅጣጫ መረዳት አትችሉምና የማይረባ መሆኑን ልትረዱት አትችሉም፡፡ አሁን እናንተ ምንም የምልከታ አቅጣጫ የላችሁም፡፡ ዝግ ናችሁ ዝግ፡፡
ወደ መስታውት ቅረቡ አፍንጫችሁ መስታወቱን እስኪነካ ድረስ፡፡ አስተውሉ በፍፁም ፊታችሁን ማየት አትችሉም፡፡ የመስታውቱ ችግር አይደለም፡፡ ከመስታወቱ ራቅ ስትሉና ቦታ ስትሰጡት አንፀባርቆ ፊታችሁን ያሳያችኋል ስለዚህ ከመስታውቱ ራቁ።

ወሲብ ትልቁ ተወዳጅ ነገር ይመስላል፡፡ ወንድ በሴት ይማረካል ሴትም በወንድ ትማረካለች፡፡ አንዱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ የወሲብ አጋሩ ያለው ይመስለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሁለቱንም ለማኝ ያደርጋቸዋል፡፡ ፍላጐታቸውን ሁሉ ከወሲብ ጥላ ጀርባ የሚያገኙት ይመስላቸዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ነገሮችን እንድትሰሩ የሚያደርጋችሁ ውስጣችው ያለው ሆርሞናችሁ ነው፡፡ ስነህይወታዊ ቀመር ነው፡፡ ምን እየሰራህ እንደሆነ፣ ለምን እየሰራኸው እንደሆነ ማየት ብትችል ለራስህ ይገርምሀል። ወሲብ በመፈፀምህ ያገኘኸው ነገር ምን ይሆን?፡፡ንቁ መንፈስ ውስጥ በምትገባበት ወቅት ምን እያወራሁ እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ነገር ግን ንቁ መንፈስህ ጥልቅነት የሌለው በመሆኑ እያደገ ይገድልሀል እናም ወደ ነበርክበት የስህተት ጐዳና ትመለሳለህ።

እንደገና ሞክረው ነገር ግን ስትሞክረው እያስተዋልክ እና እየተመሰጥክ ይሁን፡፡ ያን ጊዜ ወሲብን ፈፅመህ ላለማድረግ ትወስናለህ ወይም ተፈጥሯዊ አስገዳጅ ሀይል መሆኑን ትረዳለህ፡፡

እኔን ልትሸውዱኝ አትችሉም፡፡ እኔ ወሲብ የማይረባ ነው ስላልኳችሁ የፈፀማችሁት ይመስላችኋል?፡፡ ወሲብ በጣም ምርጥ ነው፣ ወሲብ በጣም የማይረባ ነገር ነው ብላችሁ አልያም ስለወሲብ አለመናገርን ብመርጥ እናንተ ከመፈፀም ወደኋላ አትሉም፡፡
ወደ አእምሯችሁ ተመልከቱ፡፡ እንዴት እራሳችሁን እያታለላችሁ እንደሆነ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ አለበለዚያ እኔ ምን እያወራሁ እንደሆነ የንቃት ደረጃችሁ ካላደገ ፈፅሞ ልትገነዘቡኝ አትችሉም፡፡ የበለጠ ነገር ለማየት ከፈለጋችሁ ከዚህ የበለጠ ማሻሻል (ማደግ) አለባችሁ፡፡

ለምሳሌ እኔ አንድ መንገድ ዳር ላይ ያለ ዛፍ ጫፉ ላይ ሆኜ እናንተ በመንገዱ ላይ እየሄዳችሁ ጋሪ እየመጣ ነው" ብላችሁ "ምንም ጋሪ አይታየኝም ጋሪ የለም ትሉኛላችሁ፡፡ ነገር ግን እኔ ጋሪውን ማየት የምትችሉት ወደ እናንተ በቀረበ ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አልፏችሁ ሲሄድ እንደገና ከእይታችሁ ውጪ ይሆናል፡፡

አሁንም ወደ በለጠ ከፍታ በወጣችሁ ቁጥር የተሻለ ማየት ትችላላችሁ፡፡ የከፍታ ቁንጮ ላይ ስትሆኑ ሁሉንም ነገር ታያላችሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለፈም ይሁን መጪ ጊዜ የለም ያለው አሁን ብቻ ነው፡፡ እውነታው ሲገባችሁ ወሲብ በጣም የማይረባ አና ለረጅም ጊዜ በባርነት የሚይዝ መሆኑን ትረዱታላችሁ፡፡ እያጣጣልኩት (እየነቀፍኩት) አይደለም ነገር ግን እውነታው ይህ ነው እኔም የተናገርኩት ያንኑ ነው፡፡ አያችሁ በውስጡ ዘልቃችሁ በመግባታችሁ በባርነት አስሮ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ እንኳን ማየት እንዳትችሉ ወደ ንቃት እንዳትመጡም አድርጓችኋል።

ወሲብ ከሚያሰክሩ (ስነህይወትህ) ውስጥ ነው፡፡ በደምስሮችህ ውስጥ የሚያሰራጨው ነገር በሱስ ተለክፈህ ምን እንደምትሰራ እንዳታውቅ እና ስሜቶችህን መቆጣጠር እንዲሳንህ ያደርጋል፡፡ በተደጋጋሚ እንድትፈፅመው የሚያስገድድህ ያልታወቀ ሀይል አለ እንደፈለጋችሁ ልትጠሩት ትችላላችሁ፡፡ በንቁ ጊዜያቶችህ ግን የማይረባ ነገር ስለምትረዳ "ምን እየሰራሁ ነበር? ለምን? ምን ነገርስ አገኘሁ?" በማለት ትጠይቃለህ፡፡ለዚህ ነው ብዙ ሴቶች ከወሲብ በኋላ የሚያለቅሱት እና የሚያዝኑት ምክንያቱም ሁሉም ነገር ትርጉም አልባ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ለጊዜው ስሜትን የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ቢደጋገምም የትም አያደርስም፡፡ ወንዱ ከወሲብ በኋላ ወዲያውኑ ይተኛል ምክንያቱ ደግሞ በተረጋጋ መንፈስ ስላደረገው ነገር ማሰብ አለመፈለጉነው ጧት ሲነሳ ሁሉንም ነገር ይረሳል፡፡

በርግጥ ይገበኛል ጥሩ ነው ብለህ አምነህ የምትኖርበትን ልምድ ሲያንቋሽሹብህ አትወድም። ማንም ጅል ሲባል ደስ አይለውም፡፡ የምትረበሸው ስለ ወሲብ ባለህ ጥያቄ ሳይሆን በህይወትህ በራሱ ነው፡፡ ጅል ከሆነ እና ከኖርክባት አንተም ጅል እየሆንክ ነው። በርግጥ ያስቆጣል ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ከሱ የተሻሉ መልካም ነገሮች በህይወት ውስጥ መኖራቸው መናገር ይኖርብኛል፡፡ወሲብ ጅማሮ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እጥብቀህ እስካልያስከው ድረስ እንደ መጀመሪያ ያህል ከተጠቀምክበት ምንም ችግር የለውም፡፡

ፍቅር ከሰራህ በኋላ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል በዜን እሳቤ ተቀመጥ ያን ጊዜ የምለው ይገባሀል፡፡ ወሲብ ጅል ነው የምለው ለምን እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ከወሲብ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ስለተፈጠረው ነገር አስብ፡፡ አውቀህ ነው ወይስ ስሜትህ አስገድዶህ? አውቀህ ከሆነ ጅል አይደለህም፡፡ ተገዢ ከነበርክ ግን ጅል መሆንህን ተረዳው ምክንያቱም እየደጋገምክ በመፈፀም ራስህን ለበለጠ ባርነት እየሰጠህ ነው፡፡
በተመስጦ ብቻ ነው ምን እያወራሁ እንደነበረ ሊገባህ የሚችለው፡፡ በክርክር የሚወሰን ጥያቄ አይደለም፡፡ በራስህ ንቃት፣ በራስህ ግንዛቤ እና በራስህ ተመሰጦ የሚወሰን መሆኑን ተገንዘብ፡፡

ኦሾ
የዜን መንገድ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
10.7K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 18:47:17
9.5K views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 18:30:31
8.9K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ